Get Mystery Box with random crypto!

የግርማ የሺጥላ አስከሬን ሽኝት በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው! የአማራ ክልል ብልጽግና ቅር | LEYU NEWS

የግርማ የሺጥላ አስከሬን ሽኝት በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው!

የአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ የነበሩት የግርማ የሺጥላ አስከሬን የክብር ሽኝት በወዳጅነት አደባባይ በመከናወን ላይ ይገኛል።በክብር ሽኝት ሥነ ስርዓቱ ላይም የፌደራል እና የክልል የሥራ ሃላፊዎች የግርማ የሺጥላ የሥራ ባልደረቦች፣ እንዲሁም ወዳጅ ቤተሰቦቹ የተገኙ ሲሆን፤ የአስክሬን ሽኝቱም በከፍተኛ ወታደራዊ ሥርዓት በመከላከያ እና በፌደራል ፓሊስ ማርች ባንድ አጃቢነት እየተካሄደ ነው፡፡

ሽኝቱ በወዳጅነት አደባባይ ከተካሄደ በኃላም በቤተሰቦቻቸው ጥያቄ መሰረት፤ የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በሰሜን ሸዋ ዞን መንዝ ጌራ መሃል ሜዳ ነገ ሰኞ ሚያዝያ 24/2015 ይፈጸማል፡፡ግርማ የሺጥላ ወ/ጻዲቅ ከእናታቸው ከወ/ሮ ዘውዴ ስመኝ እና ከአባታቸው የሺጥላ ወልደጻዲቅ በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሃገር በመንዝና ግሼ አውራጃ በጌራ ምድር ወረዳ መሃል ሜዳ ከተማ ህዳር 17/1967 መወለዳቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ከ25 ዓመታት በላይ በተለያዩ የመንግሥት የሥራ ሃላፊነት ቦታዎች ላይ በትጋትና በታማኝነት ያገለገሉት ግርማ፤ ሐሙስ ሚያዚያ 19/2015 ከመሃል ሜዳ ወደ ደብረ ብርሃን በመጓዝ ላይ ሳሉ በታጣቂዎች በተከፈተባቸው ተኩስ በተወለዱ በ48 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ግርማ የሺጥላ ባለትዳር ሲሆኑ የሦስት ሴት እና የአራት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ፡፡

[Addis Maleda]

@Leyu_News
@Leyu_News