Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-26 21:00:05
በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ በደረሰው አደጋ የ11 ሰው ህይወት ጠፋ!

በዛሬው እለት ጠዋት ከምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አረርቲ ከተማ በመነሳት ወደ አዳማ በመጓዝ ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት መኪና ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ  አደጋ ከ11ሰው በላይ ህይወት በማለፉ የሞረትና ጅሩ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
588 views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 17:18:29
በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን በምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ እና ሾኔ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ላለፉት ሦስት ወራት ደሞዝ ባለመግኘታችን ተቸገርን አሉ፡፡

ሠራተኞቹ በደሞዝ አጦት የተነሳ አንዳንዶቹ የሚበሉት በማጣት የቤት እቃዎቻቸውን እየሸጡ ፤ ከፊሎቹም ቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመጠጋት መገደዳቸውን ገልጸዋል።ክፍያው ሊፈጸም ያልቻለው የቀድሞው የወረዳው አመራሮች የመንግሥት ሠራተኞችን የደሞዝ በጀት በዋስትና በማስያዝ የወሰዱሱት የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ ባለመከፈሉ አሁን ላይ በዋስትና የተያዘው የደሞዝ በጀት ለአበዳሪው አካል ገቢ በመደረጉ ነው መባሉን ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
2.1K views14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 17:17:10
በሱዳን የተከሰተውን ግጭት በመሸሽ የተለያዩ ሀገር ዜጎች በመተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው
የተፈጠረውን አለመረጋጋት ሸሽተው የሚመጡ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በሰላም እያስተናገደች መሆኑ ተነገረ።

ሱዳን ላይ በተፈጠረው የውስጥ አለመረጋጋት ምክኒያት ጦርነቱን ሸሽተው ከካርቱም ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዩጵያ የሱዳን ዜጎችን ጨምሮ የ23 ሀገራት የተለያዪ ሃገራት ዜጎች እንደገቡና ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህም የምዕራብ ጎንደሯ መተማ ዮሃንስ ከተማ እንግዶቿን እያስተናገደች ሲሆን በቀን ከ15-20 የሚሆኑ መኪናዎች ወደ ጎንደር እየሄዱ ይገኛሉ ። በዚህ የጦርነት ስጋት ሽሽትም ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ይገኙበታል።

የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብአዊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሆነ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ገልፇል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.0K views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 12:18:45
ዛሬ ምሽት አራት ሰአት በኢትሃድ የዘንድሮውን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ መዳረሻ የሚጠቁም እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ በማንቸስተር ሲቲና አርሰናል መሀከል ይደረጋል። ሲቲ ከመሪው አርሰናል በአምስት ነጥብ አንሶ ሁለት ተስተካካይ ጨዋታዎች እያሉት እግር በግር አርሰናልን እየተከተለ ይገኛል።

አርሰናል ለመጨረሻ ግዜ ሲቲን ያሸነፈው በ 2020 በ ኤፍ ኤ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ነበር። ከዛ ቡኋላ በ ሁሉም ውድድሮች ሲቲን ማሸነፍ አልቻለም። ዛሬ በወሳኙ ጨዋታ ማን ድል ይቀናዋል? በጉጉት የሚጠበቅ ሆኗል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.8K viewsedited  09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 10:50:26
ስዊድን የተኮሰችው ሮኬት በስህተት ጎረቤቷን ኖርዋይን መታ!

የስዊድን ስፔስ ኮርፕ(ኤስኤስሲ) ከኢስራንጅ የስፔስ ማዕከል የተኮሰው ሮኬት 15 ኪ.ሜ ኖርዋይ ውስጥ ከተጓዘ በኋላ ተቀላሽቶ ተከስክሷል።በሙከራው ሮኬቱ 250 ኪ.ሜ በመጓዝ የመሬት ስበት ዜሮ በሆነበት እርቀት ላይ ደርሶ ነበር።

ኤስኤስሲ ኃላፊ ፊልፕ ኦህልሰን እንደገለጹት አንድ ሺ ሜትር ከፍታ ባለው ተራራማ ቦታ አርፏል።ኃላፊው እንዲህ አይነት ችግር ሊያጋጥም እንደሚችል እና ሁነቱን ለስዊድን እና ለኖርዋይ መንግስት ማሳወቃቸውን ተናግረዋል።

ኤስኤስሲ ሮኬቱ ለምን በተሳሳተ አቅጣጫ እንደሄደ ለማወቅ ምርመራ ተጀምሯል ብሏል።የኖርዎይን ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ በኖርዎይ ድንበር በኩል የሚደረጉ እውቅና የሌላቸው እንቅስቃሴዎችን በጥብቅ እንደሚከታተሏቸው ገልጸዋል።

የድንበር ጥሰት ሲያገጥም ኃላፊነት ያለባቸው የኖርዎይ የውጭ ጉዳይን ጨምሮ ለሚመለከታቸው አካለት ማሳወቅ እንዳለባቸው ሮይተርስ ዘግቧል።በጉዳዩ ላይ ከስዊድን ባለስልጣናት በይፋ እንዳልተነገረው የኖሮዎይ ውጭ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

[Alain]

@Leyu_News
@Leyu_News
2.9K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 10:45:34
በአጣየ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ በአርሶ አደሮች ላይ ጉዳት ደረሰ

በአጣዬ ዙሪያ አርሶአምባ እና አላላ በሚባሉ አካባቢዎች ታጣቂዎች ሰሞኑን እርሻ ላይ በነበሩ አርሶአደሮች ላይ በከፈቱት ተኩስ ሰባት ሰዎች ቆስለዋል። ከብቶችንም ነድተው ወስደዋል።

ይህ የሆነው ልዩ ሀይሉ ከአካባቢው ከወጣ በኋላ ነው ተብሏል። አካባቢው አሁን ላይ በኮማንድ ፖስት ስር እንደሆነ ይታወቃል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.6K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 10:43:23 #መረጃ
የባልደራስ ፓርቲ መስራች አባልና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከባልደራስ በፍቃዳቸው ለመሰናበት በመልቀቂያ ደብዳቤ ሊጠይቁ መሆኑ ከፓርቲው የውስጥ ምንጮች መረጃዉ ተሰማ።

            ሚያዚያ 18/2015
                ኢትዮጵያ

"አማራነት በመቱት ቁጥር ይበልጥ ስሜቱ እየገባን መጥቷል ብለዋል።

አንጋፋው ፖለቲከኛ የባልደራስ ፓርቲ  ሥራ አስፈጻሚ አባልና የድ/ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በቅርብ ጊዜ ከእስር የተፈቱ ሲሆን  የፖለቲካ አቅጣጫ ለውጥ ለማድረግ ማሰባቸው ከፓርቲዉ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መረዳት ችለናል።

በአሁኑ ጊዜ በአማራ ሕዝብ የታወጀው ጦርነት አጥፍቶ የመጥፋት ቅስቀሳ የለየለት ውንብድና አማራን አጥፍቶ ሀገር ለመበትን መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው የሚሉት አቶ ስንታየሁ  አማራ በህልውና አደጋ የአዲስ አበባ ነዋሪ በጠቅላይነት ባርነት ውስጥ በወደቁበት ወቅት በምርጫ ጠባቂ  ቆሞ ቀር አጃቢ የቢሮ ፖለቲካ አሁን አይሰራም ሲሉ ሁሉም ሰዉ በህልውና ሕዝባዊ ትግል ብቻ ነው ነጻነቱን የሚያረጋግጠው በማለት የፖለቲካ መስመር የትግል ለውጥ ለማድረግ ከፓርቲዉ ሃላፊነት በፍቃዳቸው ለመልቀቅ መጠየቃቸው ተሰምቷል።

ከባለአደራው ጀምሮ ባልደራስ ፓርቲን በአዲስ አበባ ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር በማቋቋም ከምሥረታዉ ጀምረው የድርጅቱ የጀርባ አጥንት አምዕድ በመሆን ሲታገሉ የምናቃቸው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በተደጋጋሚ በኦህዴድ/ብልፅግና መንግስት በአማራነታቸው ሲንገላቱ መቆየታቸው ይታወቃል። ስልጣን ላይ ባለው የዐቢይ አህመድ አገዛዝ በአዲስ አበባ ነዋሪ በተለይ በአማራ ሕዝብ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ከፍተኛ አደጋና መፈናቀል ቀድመው በመተንበይ በርካታ የማንቃት ስራዎችን ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር በመስራት ለነዋሪዉ ቢደክሙም የተረዳቸው ሕዝብ ባለመኖሩ ዛሬ የተደረሰበት ውጥንቅጥ የኦህዴድ ተረኛነት ፖለቲካ ነዋሪዎን ለከፋ ችግር እንደዳረገው በስፋት እየተገለፀ ይገኛል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ላለፋት  ለ22 አመታት በሰላማዊ ትግል ሲታገሉ መቆየታቸውና ከአስር አመታት በላይ በተደጋጋሚ በተለያዩ ቦታዎች መታሰራቸው ይገለጻል።
 
@Leyu_News
@Leyu_News
2.6K views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 10:43:09
2.5K views07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 08:08:33
በሚኒባስ ተሽከርካሪ ውስጥ ባዶ ፍራሽ አንጥፈው የኩላሊት ታማሚ የተኛ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 4 ግለሰቦች ተያዙ

ግለሰቦቹ የማታለል ድርጊቱን ሲፈፅሙ የተገኙት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሲኒማ ራስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው አራት ተጠርጣሪዎች የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 43018 ኦሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ውስጥ ባዶ ፍራሽ በማንጠፍ ፣ በፍራሹ ላይ የኩላሊት በሽታ ታማሚ የተኛ በማስመሰል እና የግለሰብ ፎቶ በባነር አሳትመው በመስቀል በስፒከር እየቀሰቀሱ በህክምና ወጪ ሰበብ ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲሰበስቡ የፖሊስ አባላት በጥርጣሬ ባከናወኑት የማረጋገጥ ስራ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል፡፡

መደጋገፍና መረዳዳት ከኢትዮጵያውያን መገለጫዎቻችን አንዱ ቢሆንም በአቋራጭ ለመበልፀግ ህብረተሰቡን በማታለል እንዲህ አይነት ህገ ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ግለሰቦች መኖራቸውን በመገንዘብ እውነተኛ ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎችን ማገዝ እንደተጠበቀ ሆኖ በህክምና ሰነዶች እና በሌሎች ሁኔታዎች የማረጋገጥ ስራ በመስራት አታላዮችን ማጋለጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ኢንስፔክተር ተዘራ አብሽር
 
@Leyu_News
@Leyu_News
3.1K views05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 23:10:22
ሰበር ዜና
በታንዛኒያ ዛንዚባር ደሴት በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ውይይት ዛሬ ተጀመረ።

በታንዛኒያ የሰላም ድርድር ዛሬ ማለዳ መጀመሩን በስፍራው የነበሩ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ስድስት ሰዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በመንግስት በኩል ወደ ታንዛኒያ የተጓዘው የልዑካን ቡድን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ እንደሚገኙበት ቢቢሲ ዘግበዋል።

በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በኩል አንጋፋው የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰን እና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዋና አዛዥ አማካሪ ሚስተር ጂሬኛ ጉዳታ እና አቶ አብዲ ጠሃ እና ሌሎችም መገኘታቸውን ፋስት መረጃ ከቢቢሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ሁለቱም ተደራዳሪ አካላት ንግግር ስለመጀመሩ ማረጋገጫ ቢሰጡም ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረጉም ፤ የታንዛኒያ ባለስልጣናትም ስለድርድሩ የተለየ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።


@Leyu_News
@Leyu_News
3.7K views20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ