Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን በምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ እና ሾኔ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ላለፉ | LEYU NEWS

በደቡብ ክልል ሃድያ ዞን በምሥራቅ ባድዋቾ ወረዳ እና ሾኔ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ላለፉት ሦስት ወራት ደሞዝ ባለመግኘታችን ተቸገርን አሉ፡፡

ሠራተኞቹ በደሞዝ አጦት የተነሳ አንዳንዶቹ የሚበሉት በማጣት የቤት እቃዎቻቸውን እየሸጡ ፤ ከፊሎቹም ቤት ኪራይ መክፈል ባለመቻላቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመጠጋት መገደዳቸውን ገልጸዋል።ክፍያው ሊፈጸም ያልቻለው የቀድሞው የወረዳው አመራሮች የመንግሥት ሠራተኞችን የደሞዝ በጀት በዋስትና በማስያዝ የወሰዱሱት የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ ባለመከፈሉ አሁን ላይ በዋስትና የተያዘው የደሞዝ በጀት ለአበዳሪው አካል ገቢ በመደረጉ ነው መባሉን ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News