Get Mystery Box with random crypto!

በሱዳን የተከሰተውን ግጭት በመሸሽ የተለያዩ ሀገር ዜጎች በመተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ | LEYU NEWS

በሱዳን የተከሰተውን ግጭት በመሸሽ የተለያዩ ሀገር ዜጎች በመተማ ዮኋንስ ከተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው
የተፈጠረውን አለመረጋጋት ሸሽተው የሚመጡ የተለያዩ የውጭ ሀገር ዜጎችን የምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮኋንስ ከተማ በሰላም እያስተናገደች መሆኑ ተነገረ።

ሱዳን ላይ በተፈጠረው የውስጥ አለመረጋጋት ምክኒያት ጦርነቱን ሸሽተው ከካርቱም ወደ ጎረቤት ሀገር ኢትዩጵያ የሱዳን ዜጎችን ጨምሮ የ23 ሀገራት የተለያዪ ሃገራት ዜጎች እንደገቡና ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እየሄዱ ይገኛሉ።

በዚህም የምዕራብ ጎንደሯ መተማ ዮሃንስ ከተማ እንግዶቿን እያስተናገደች ሲሆን በቀን ከ15-20 የሚሆኑ መኪናዎች ወደ ጎንደር እየሄዱ ይገኛሉ ። በዚህ የጦርነት ስጋት ሽሽትም ህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ይገኙበታል።

የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላትም ዜጎች ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብአዊ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሆነ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ገልፇል።

@Leyu_News
@Leyu_News