Get Mystery Box with random crypto!

#መረጃ የባልደራስ ፓርቲ መስራች አባልና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከባልደ | LEYU NEWS

#መረጃ
የባልደራስ ፓርቲ መስራች አባልና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ቸኮል ከባልደራስ በፍቃዳቸው ለመሰናበት በመልቀቂያ ደብዳቤ ሊጠይቁ መሆኑ ከፓርቲው የውስጥ ምንጮች መረጃዉ ተሰማ።

            ሚያዚያ 18/2015
                ኢትዮጵያ

"አማራነት በመቱት ቁጥር ይበልጥ ስሜቱ እየገባን መጥቷል ብለዋል።

አንጋፋው ፖለቲከኛ የባልደራስ ፓርቲ  ሥራ አስፈጻሚ አባልና የድ/ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በቅርብ ጊዜ ከእስር የተፈቱ ሲሆን  የፖለቲካ አቅጣጫ ለውጥ ለማድረግ ማሰባቸው ከፓርቲዉ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መረዳት ችለናል።

በአሁኑ ጊዜ በአማራ ሕዝብ የታወጀው ጦርነት አጥፍቶ የመጥፋት ቅስቀሳ የለየለት ውንብድና አማራን አጥፍቶ ሀገር ለመበትን መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው የሚሉት አቶ ስንታየሁ  አማራ በህልውና አደጋ የአዲስ አበባ ነዋሪ በጠቅላይነት ባርነት ውስጥ በወደቁበት ወቅት በምርጫ ጠባቂ  ቆሞ ቀር አጃቢ የቢሮ ፖለቲካ አሁን አይሰራም ሲሉ ሁሉም ሰዉ በህልውና ሕዝባዊ ትግል ብቻ ነው ነጻነቱን የሚያረጋግጠው በማለት የፖለቲካ መስመር የትግል ለውጥ ለማድረግ ከፓርቲዉ ሃላፊነት በፍቃዳቸው ለመልቀቅ መጠየቃቸው ተሰምቷል።

ከባለአደራው ጀምሮ ባልደራስ ፓርቲን በአዲስ አበባ ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር በማቋቋም ከምሥረታዉ ጀምረው የድርጅቱ የጀርባ አጥንት አምዕድ በመሆን ሲታገሉ የምናቃቸው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በተደጋጋሚ በኦህዴድ/ብልፅግና መንግስት በአማራነታቸው ሲንገላቱ መቆየታቸው ይታወቃል። ስልጣን ላይ ባለው የዐቢይ አህመድ አገዛዝ በአዲስ አበባ ነዋሪ በተለይ በአማራ ሕዝብ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ከፍተኛ አደጋና መፈናቀል ቀድመው በመተንበይ በርካታ የማንቃት ስራዎችን ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር በመስራት ለነዋሪዉ ቢደክሙም የተረዳቸው ሕዝብ ባለመኖሩ ዛሬ የተደረሰበት ውጥንቅጥ የኦህዴድ ተረኛነት ፖለቲካ ነዋሪዎን ለከፋ ችግር እንደዳረገው በስፋት እየተገለፀ ይገኛል።

አቶ ስንታየሁ ቸኮል ላለፋት  ለ22 አመታት በሰላማዊ ትግል ሲታገሉ መቆየታቸውና ከአስር አመታት በላይ በተደጋጋሚ በተለያዩ ቦታዎች መታሰራቸው ይገለጻል።
 
@Leyu_News
@Leyu_News