Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-01 19:59:31 እናት ፓርቲ ፌደራል መንግሥቱ በአማራ ክልል ውስጥ የጀመረውን "የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ፣ የድርጅቶችና ግለሰቦችን የገንዘብ እንቅስቃሴ የማገድ ሂደት" እንዲያቆም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ፓርቲው፣ መንግሥት "በማንአለብኝነት አካሄዱ ቀጥሎ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ውድመት ከተጠያቂነት አያመልጥም" በማለት አስጠንቅቋል።

ፓርቲው፣ በአንዳንድ ክልሎች በገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናት ላይ በተፈጸሙ ግድያዎች ላይ "ምርምራ ባልተካሄደበትና ጥፋተኞች ባልተለዩበት ኹኔታ" ይደረጋሉ ያላቸው ፍረጃዎች "የፍትህ አሰጣጡን እንደሚያዛቡ" በመግለጽም በመግለጫው ተችቷል።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.1K views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 19:52:00
የሚዲያ ባለሙያዉ ሰይፉ ፋንታሁን ፤ በድሬዳዋ ትራፊክ ፖሊስ ላይ በመቀለዱ ይቅርታ ጠየቀ!

እዉቁ የቴሌቪዥን እና ራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጁ ሰይፉ ፋንታሁን ፤ በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ በድሬዳዋ ትራፊክ ፖሊስ ላይ በመቀለዱ ይቅርታ ጠይቋል። ሰይፉ ፤ በፕሮግራሙ ከተመልካቾች ተላከ ባለዉ እና ባቀረበዉ መልዕክት ነዉ የድሬዳዋ ፖሊስን ይቅርታ እንዲጠይቅ የተደረገዉ።

የፕሮግራም አዘጋጁ አግባብ የሌለዉና የከተማዋን ፖሊስ ስም ያጠፋ ተግባር መፈጸሙን የድሬዳዋ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነትና የለዉጥ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ገመቹ ታቻ ለዳጉ ጆርናል ተናግረዋል።የከተማዉ ፖሊስ መምሪያ ተፈጽሞብኛል ያለዉን የስም ማጥፋት በሚመለከት ከግለሰቡ ጋር ከተነጋገረ በኋላ በትናንትናው እለት በነበረዉ ፕሮግራሙ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል ብለዋል ኮማንደር ገመቹ።

የከተማዉ ፖሊስ የአሰራርም ሆነ ሌሎች ለዉጦችን ማካሄዱን ኮማንደሩ ያነሱ ሲሆን ፤ ግለሰቡ በሚዲያ ያሰራጨዉ መልዕክት ቀልድ ብቻ ሳይሆን ስም ማጥፋት እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም ግለሰቡ በትናንትናው ፕሮግራሙ ይቅርታ መጠየቁን ፖሊስ መምሪያዉ ትልቅነት ነዉ በሚል መቀበሉን አክለዋል።ኮማንደሩ በመልዕክታቸዉ ፤ የሚዲያ ሰዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በሚዲያዎች ላይ የሚያስተላልፉት መልዕክት ጥንቃቄ የተሞላዉ ሊሆን እንደሚገባ ጨምረው ለዳጉ ጆርናል ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል/

@Leyu_News
@Leyu_News
1.2K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 13:07:51 ሰበር መረጃ

በማጀቴ ከተማ ተኩስ የተከፈተ ሲሆን በከባድ መሳሪያ በታገዘ መልኩ ልውውጥ እየተደረገ ነው!!

@Leyu_News
@Leyu_News
3.1K views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 11:48:39
የአይ ኤስ መሪ አልቁረይሺ መገደሉን የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ተናገሩ!

በሶሪያ የኢስላሚክስ ስቴት (አይ ኤስ) መሪ አልቁረይሺ በቱርክ ኃይሎች መገደሉን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶዋን ተናገሩ።አቡ ሑሴይን አልቁረይሺ በሚል ሙሉ ስሙ የሚታወቀው የአይ ኤስ መሪ መገደሉን ኤርዶዋን ይፋ ያደረጉት ለቲአርቲ ሚዲያ ነው።ይህን እርምጃ የወሰዱት ደግሞ የቱርክ የስለላ እና ደኅንነት አባላት መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል።

ኢስላሚክ ስቴት (አይ ኤስ) እስከ አሁን ዜናውን አላስተባበለም።ቢቢሲ የኤርዶዋንን ቃል ከሌላ ገለልተኛ አካል አላጣራም።የቱርክ የስለላ እና ደኅንነት መሥሪያ ቤት ቁራይሺን ረዘም ላለ ጊዜ ሲከታተለው እንደነበር ኤርዶዋን አብራርተዋል።

“ከአሸባሪዎች ጋር የምናደርገው ትግል አሁንም ይቀጥላል” ሲሉም ተናግረዋል።ሮይተርስ ያነጋገራቸው በሶሪያ የሚገኙ ምንጮች በበኩላቸው ይህ ኦፕሬሽን የተደረገው ከቱርክ ድንበር አቅራቢያ ጃንዳሪስ በምትባል ትንሽ ከተማ ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።

[BBC]

@Leyu_News
@Leyu_News
3.4K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 11:47:25 ወልድያ

በአሁኑ ሰዓት ይሰራ የነበረው የባለ ገመዱ WIFI ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መቋረጡን አረጋግጠናል!!

ለምን ??? የኢንተርኔቱ መዘጋቱ ባይበቃ ይሄን ጨምሮ መዝጋቱ ጥቅሙ ምኑ ላይ ነው??

የወልድያንና አካባቢዋን ህዝብ ለይቶ እንደዚህ ማድረጉ ተገቢ አይመስ

@Leyu_News
@Leyu_News
3.1K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:21:16
ከአቶ ግርማ የሺጥላ ጋር የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 6 ደረሰ!

በተኩስ ልውውጡ አቶ ግርማ የሽጥላን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ከ14 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተገለፀ።

አቶ ግርማ የሺጥላን ሲጠብቁ ከነበሩ አራት ጠባቂዎች ውስጥ ሁለቱ ከባድ የመቁሰል አደጋ፣ ሁለቱ ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተኩስ ልውውጡ

ዋና ሳጅን በላይ አስማማው  በመንዝ ጌራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የግንዛቤ ማስጨበጫ ንዑስ ክፍል ኀላፊ የነበሩት

ረዳት ሳጅን አስማረ አንተነህ፣ በመንዝ ጌራ ወረዳ ፖሊስ ኦፊሰር ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩት 

ድምር ከተማ ከለለው በመንዝ ጌራ ወረዳ የጸጥታ መዋቅረ ውስጥ ሲሠሩ የቆዩ፣

ከበደ አሰፋ መንዝ ጌራ ወረዳ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ንብረት ክፍል ባለሙያ፣

ሾፌር ልየው መንጌ፣ አብረው መሰዋታቸውን ጠቁመዋል።

ግለሰቦቹ አቶ ግርማ የሺጥላን ወደሌላ ወረዳ እየሸኙ በነበረበት ሰዓት በተከፈተ ተኩስ መሰዋታቸውን ተናግረዋል። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በተወለዱበት አካባቢ መፈጸሙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያሳያል።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.6K views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 20:20:51
የብልጽግና አገዛዝ አገር በማፍረስ ወንጀል” እፈልጋቸዋለሁ ሲል የአፋልጉኝ ማስታወቂያ አውጥቷል። በወንጀል እፈልጋቸዋለሁ ካላቸው ውስጥ

1. ከሀገር ውስጥ

ጎበዜ ሲሳይ
ምህረት ወዳጆ (ምሬ ወዳጆ)
በለጠ ጋሻው እና
ሙሉጌታ አንበርብር

2. ከሐገር ውጪ

ሀብታሙ አያሌው፣
ምንአላቸው ስማቸው፣
ብሩክ ይባስ እና
እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ 
ዘመድኩን በቀለ
ልደቱ አያሌው
መሳይ መኮንን ናቸው

@Leyu_News
@Leyu_News
4.1K views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:25:43
ሰበር ዜና!

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም በፌደራል ፖሊሶችና የደህንነት አባላት እስከ አራስ ጨቆላዋ ጋር ወደ ሜክስኮ ፓሊስ መምሪያ ወስደዋታል።

@Leyu_News
@Leyu_News
4.2K views16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:18:09 የመከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል ቆቦ ወረዳ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተገለጸ

ማምሻውን ጀምሮ መከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ በነዋሪዎች ላይ የቤት ለቤት ፍተሻ እያደረገ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከሥፍራው ነዋሪዎች አረጋግጣለች፡፡

<<የአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላን የገደላችሁት እናንተ ናችሁ።>> በማለት ፋኖዎች እየተሳደዱ እና ቤተሰቦቻቸውም እየታሰሩ መሆኑን ነው ነዋሪዎች የገለጹት፡፡

በዚህም፤ ከአርብ ዕለት ጀምሮ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ከቆቦ ወደ አላማጣም ይሁን ወደ ወልድያ ለመሄድ መንገድ ተዘግቶ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎች፤ ከቀናት በፊት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በሽምግልና ታርቀው ወደማህበረሰቡ የተቀላቀሉ የፋኖ አባላትም እየተሳደዱ ነው ብለዋል፡፡

ከአስር በላይ የፋኖ አባላት ቤተሰቦች ለእስር እንደተዳረጉም ጠቅሰው፣ ሌሊት በሚደረገው የቤት ለቤት ፍተሻ በተለይ ሴቶች እየተሳቀቁ እንደሆነ ተናግረዋል።

<<ሰውዬው የተገደሉት ሰሜን ሸዋ ሆኖ ሳለ ገዳዮቹ ቆቦ ውስጥ ናቸው ብሎ ማህበረሰቡን ሰላም መንሳት ተገቢ አይደለም።>> ያሉት ነዋሪዎቹ እየተደረገ ያለው ነገር ህዝብን ለአመጽ ከማነሳሳት ውጭ ፋይዳ የለውም ብለዋል፡፡

<<እንደ ሸኔ ያሉ ታጣቂ ኃይሎች ዜጎችን ከቀያቸው እያፈናቀሉ እና መንገድ ላይ እያገቱ ብዙ ጥፋት የሚያደርሱ ኃይሎችን ችላ በማለት፤ ምንም ባልተፈጠረበት ቆቦ ላይ ይህን ሁሉ ግርግር መፍጠር የመንግሥት አካሄድ ፍትሃዊነት የጎደለው አገዛዝ መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው።>> ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በዚህ ወቅት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፍተው መደበኛ እንቅስቃሴ የቀጠለ ቢሆንም ማህበረሰቡ አሁንም መደናገጥና ስጋት ላይ ነው ተብሏል።

ከአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ መገደል በኋላ፤ የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአማራ ክልል ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰድኩኝ ነው ሲል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ግብረ ኃይሉ ‹‹ፅንፈኛ ኃይሎች›› ብሎ የሚጠራቸው አካላት የአማራ ሕዝብ የልማትና የሰላም ተጠቃሚ እንዳይሆንና የተረጋጋ ሕይወት እንዳይኖረው እንዲሁም በመንግሥት የሚወሰኑ ውሳኔዎች እንዳይተገበሩ እንቅፋት ሲፈጥሩ መቆየታቸን ነው የገለጸው፡፡

ይሁን እንጂ በተለይ ግብረ ኃይሉ በክልሉ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ካሳወቀ በኋላ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ግራ መጋባት መፈጠሩን አዲስ ማለዳ ተገንዝባለች፡፡

ብዙዎች <<ምን እየተካሄደ ነው>> የሚል ጥያቄ እያነሱ ሲሆን፤ ጽንፈኛ ተብለው የሚጠሩ አካላትም እነማን እንደሆኑ መንግሥት በግልጽ እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል፡፡ 

መንግሥት ሰበብ ፈልጎ የፋኖ አባላትን ለመምታት እንዲሁም ክልሉን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ የታሰበ ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው የሚሉም በርካታ ቅሬታዎች እየተነሱ ይገኛል፡፡(አዲስ ማለዳ)

@Leyu_News
@Leyu_News
3.9K views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:17:52
3.5K views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ