Get Mystery Box with random crypto!

እናት ፓርቲ ፌደራል መንግሥቱ በአማራ ክልል ውስጥ የጀመረውን 'የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘ | LEYU NEWS

እናት ፓርቲ ፌደራል መንግሥቱ በአማራ ክልል ውስጥ የጀመረውን "የጅምላ እስር፣ የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ፣ የድርጅቶችና ግለሰቦችን የገንዘብ እንቅስቃሴ የማገድ ሂደት" እንዲያቆም ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ፓርቲው፣ መንግሥት "በማንአለብኝነት አካሄዱ ቀጥሎ በአገርና በሕዝብ ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ዓይነት ጥፋትና ውድመት ከተጠያቂነት አያመልጥም" በማለት አስጠንቅቋል።

ፓርቲው፣ በአንዳንድ ክልሎች በገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናት ላይ በተፈጸሙ ግድያዎች ላይ "ምርምራ ባልተካሄደበትና ጥፋተኞች ባልተለዩበት ኹኔታ" ይደረጋሉ ያላቸው ፍረጃዎች "የፍትህ አሰጣጡን እንደሚያዛቡ" በመግለጽም በመግለጫው ተችቷል።

@Leyu_News
@Leyu_News