Get Mystery Box with random crypto!

የሚዲያ ባለሙያዉ ሰይፉ ፋንታሁን ፤ በድሬዳዋ ትራፊክ ፖሊስ ላይ በመቀለዱ ይቅርታ ጠየቀ! እዉቁ | LEYU NEWS

የሚዲያ ባለሙያዉ ሰይፉ ፋንታሁን ፤ በድሬዳዋ ትራፊክ ፖሊስ ላይ በመቀለዱ ይቅርታ ጠየቀ!

እዉቁ የቴሌቪዥን እና ራዲዮ ፕሮግራም አዘጋጁ ሰይፉ ፋንታሁን ፤ በቴሌቪዥን ፕሮግራሙ ላይ በድሬዳዋ ትራፊክ ፖሊስ ላይ በመቀለዱ ይቅርታ ጠይቋል። ሰይፉ ፤ በፕሮግራሙ ከተመልካቾች ተላከ ባለዉ እና ባቀረበዉ መልዕክት ነዉ የድሬዳዋ ፖሊስን ይቅርታ እንዲጠይቅ የተደረገዉ።

የፕሮግራም አዘጋጁ አግባብ የሌለዉና የከተማዋን ፖሊስ ስም ያጠፋ ተግባር መፈጸሙን የድሬዳዋ ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነትና የለዉጥ ስራዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ገመቹ ታቻ ለዳጉ ጆርናል ተናግረዋል።የከተማዉ ፖሊስ መምሪያ ተፈጽሞብኛል ያለዉን የስም ማጥፋት በሚመለከት ከግለሰቡ ጋር ከተነጋገረ በኋላ በትናንትናው እለት በነበረዉ ፕሮግራሙ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል ብለዋል ኮማንደር ገመቹ።

የከተማዉ ፖሊስ የአሰራርም ሆነ ሌሎች ለዉጦችን ማካሄዱን ኮማንደሩ ያነሱ ሲሆን ፤ ግለሰቡ በሚዲያ ያሰራጨዉ መልዕክት ቀልድ ብቻ ሳይሆን ስም ማጥፋት እንደነበር ገልጸዋል። በዚህም ግለሰቡ በትናንትናው ፕሮግራሙ ይቅርታ መጠየቁን ፖሊስ መምሪያዉ ትልቅነት ነዉ በሚል መቀበሉን አክለዋል።ኮማንደሩ በመልዕክታቸዉ ፤ የሚዲያ ሰዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በሚዲያዎች ላይ የሚያስተላልፉት መልዕክት ጥንቃቄ የተሞላዉ ሊሆን እንደሚገባ ጨምረው ለዳጉ ጆርናል ተናግረዋል።

[ዳጉ ጆርናል/

@Leyu_News
@Leyu_News