Get Mystery Box with random crypto!

ከአቶ ግርማ የሺጥላ ጋር የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 6 ደረሰ! በተኩስ ልውውጡ አቶ ግርማ የሽጥላን ጨ | LEYU NEWS

ከአቶ ግርማ የሺጥላ ጋር የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 6 ደረሰ!

በተኩስ ልውውጡ አቶ ግርማ የሽጥላን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ከ14 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተገለፀ።

አቶ ግርማ የሺጥላን ሲጠብቁ ከነበሩ አራት ጠባቂዎች ውስጥ ሁለቱ ከባድ የመቁሰል አደጋ፣ ሁለቱ ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተኩስ ልውውጡ

ዋና ሳጅን በላይ አስማማው  በመንዝ ጌራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የግንዛቤ ማስጨበጫ ንዑስ ክፍል ኀላፊ የነበሩት

ረዳት ሳጅን አስማረ አንተነህ፣ በመንዝ ጌራ ወረዳ ፖሊስ ኦፊሰር ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩት 

ድምር ከተማ ከለለው በመንዝ ጌራ ወረዳ የጸጥታ መዋቅረ ውስጥ ሲሠሩ የቆዩ፣

ከበደ አሰፋ መንዝ ጌራ ወረዳ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ንብረት ክፍል ባለሙያ፣

ሾፌር ልየው መንጌ፣ አብረው መሰዋታቸውን ጠቁመዋል።

ግለሰቦቹ አቶ ግርማ የሺጥላን ወደሌላ ወረዳ እየሸኙ በነበረበት ሰዓት በተከፈተ ተኩስ መሰዋታቸውን ተናግረዋል። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በተወለዱበት አካባቢ መፈጸሙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያሳያል።

@Leyu_News
@Leyu_News