Get Mystery Box with random crypto!

የአይ ኤስ መሪ አልቁረይሺ መገደሉን የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ተናገሩ! በሶሪያ የኢስላሚክስ ስ | LEYU NEWS

የአይ ኤስ መሪ አልቁረይሺ መገደሉን የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ተናገሩ!

በሶሪያ የኢስላሚክስ ስቴት (አይ ኤስ) መሪ አልቁረይሺ በቱርክ ኃይሎች መገደሉን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶዋን ተናገሩ።አቡ ሑሴይን አልቁረይሺ በሚል ሙሉ ስሙ የሚታወቀው የአይ ኤስ መሪ መገደሉን ኤርዶዋን ይፋ ያደረጉት ለቲአርቲ ሚዲያ ነው።ይህን እርምጃ የወሰዱት ደግሞ የቱርክ የስለላ እና ደኅንነት አባላት መሆናቸውን ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል።

ኢስላሚክ ስቴት (አይ ኤስ) እስከ አሁን ዜናውን አላስተባበለም።ቢቢሲ የኤርዶዋንን ቃል ከሌላ ገለልተኛ አካል አላጣራም።የቱርክ የስለላ እና ደኅንነት መሥሪያ ቤት ቁራይሺን ረዘም ላለ ጊዜ ሲከታተለው እንደነበር ኤርዶዋን አብራርተዋል።

“ከአሸባሪዎች ጋር የምናደርገው ትግል አሁንም ይቀጥላል” ሲሉም ተናግረዋል።ሮይተርስ ያነጋገራቸው በሶሪያ የሚገኙ ምንጮች በበኩላቸው ይህ ኦፕሬሽን የተደረገው ከቱርክ ድንበር አቅራቢያ ጃንዳሪስ በምትባል ትንሽ ከተማ ውስጥ መሆኑን ተናግረዋል።

[BBC]

@Leyu_News
@Leyu_News