Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 38

2023-03-24 15:37:07
ካህኑ በድንጋይ ተወግረው መገደላቸው ተሰማ

አርብ መጋቢት 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ትናንት መጋቢት 14/2015 ቀሲስ ዐባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ እንዳሉ በድንጋይ ተወግረው ሕይወታቸው ማለፉን የዐይን እማኞች አረጋግጠውልኛል ሲል የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የነበሩት ቀሲስ ዐባይ መለሰ ሕይወታቸው ሲያልፍ ችግሩ ታወቀ እንጂ አስቀድሞ በአካባቢው አገልጋዮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስ እንደነበር መረጃ ሰጭዎች ተናግረዋል።

ካህኑ በድንጋይ ተደብድበው እያሉ ምስልና ቪዲዮ ለማስረጃ ለመያዝ ቢሞክሩም በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ሞባይል እየተሰበሰበ መሰረዙም ተሰምቷል።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.2K views12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 14:57:38 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ ከጉራጌ ዞን ተወካዮች ጋር በነገው ዕለት በወልቂጤ ከተማ ውይይት ሊያደርጉ ነው!

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ ከደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ወረዳዎች እና ከተሞች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ነገ ቅዳሜ መጋቢት 16፤ 2015 በወልቂጤ ከተማ ውይይት ሊያደርጉ ነው። የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ወልቂጤ ከተማ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ነዋሪዎች እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የዞኑ አመራር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ነገ በጉራጌ ባህል አዳራሽ በሚደረገው ውይይት፤ በጉራጌ ዞን የሚገኙ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ የዞኑ ተወላጆች ጥሪ ተደርጎላቸዋል።በጉራጌ ዞን ከሚገኙ በ16 ወረዳዎች ውስጥ የአንዱ አስተዳዳሪ የሆኑ አመራር ለነገው ውይይት ጥሪ እንደተደረገላቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል። የውይይቱ ዋና አጀንዳ የ“ክልል አደረጃጃት” እንደሚሆን ተናግረዋል። 

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሌላ የጉራጌ ዞን አመራር በበኩላቸው፤ የውይይቱ አጀንዳ “በዞኑ ከነበረው ተቃውሞ” ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከነገው ውይይት አስቀድመው ከጉራጌ ተወላጅ ባለሃብቶች እና ምሁራን ጋር በትላንትናው ዕለት ባደረጉት ውይይት ዋነኛ አጀንዳ የነበረው፤ የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ መሆኑን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ገልጸዋል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የጉራጌ ህዝብ ከልዩነት ይልቅ አንድ መሆን እንደሚገባው መናገራቸው ምንጮች አክለዋል። በወልቂጤ ከተማ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ከተሰቀሉ ባነሮች ውስጥ የተወሰኑት፤ ይህንኑ “የጉራጌ ህዝብን አብሮ የመኖር እሴት የሚሰብኩ” እንደሆኑ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።በከተማዋ አደባባዮች እና አውራ ጎዳናዎች ላይ ከተሰቀሉት ባነሮች አብዛኞቹ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስል የታተሙባቸው ለእርሳቸው “የእንኳን ደህና መጡ” መልዕክት የሚያስተላልፉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

Via Ethiopia Insider


@Leyu_News
@Leyu_News
1.2K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 14:20:39
የአሜሪካዋ ዩታህ ግዛት አዳጊዎች ፌስቡክን፣ ቲክቶክ እና ኢነስታግራምን የመሰሉ ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማቸው ላይ ገደብ በመጣል የመጀመሪያዋ ግዛት ሆነች።

የዩታህ ገዢ እንዳሉት የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎት አቅራቢ ኩባንያዎች ለልጆች አገልግሎቱን ከማቅረባቸው በፊት የወላጆችን ይሁንታ ማግኘት ይኖርባቸዋል።

መተግበሪያዎቻቸውም ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ አዳጊዎች ያለ ወላጅ ይሁንታ እንዳይከፍቱ ያደረጋሉ።

በዚህ ረቂቅ መሠረት ኩባንያዎቹ የአዳጊዎቹን የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም፣ ታሪክ፣ የለጠፏቸውን እና በግል የተጻጻፏቸውን መልዕክቶች ሁሉ ለወላጆች መስጠት ይገደዳሉ።

ይህን እርምጃ መውሰድ ያስፈለገው ማኅበራዊ የትስስር መድረኮች በልጆች የአእምሮ ጤና ላይ ከፍ ያለ መረበሽን እያደረሱ መሆኑ ከተደረሰበት በኋላ ነው።

ሐሙስ መጋቢት 14/2015 ዓ.ም. በጸደቀው በዚህ ደንብ መሠረት ወላጅ ወይም አሳዳጊ ልጆቹ ኢኒስታግራም፣ ፌስቡክ እና ቲክቶክ ከመክፈቱ በፊት የወላጅ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል።

ከዚህ ሌላ አዳጊዎች እነዚህን ማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋት 12፡30 ድረስ መጠቀም እንዳይችሉ ይደነግጋል።

[BBC]

@Leyu_News
@Leyu_News
1.1K viewsedited  11:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 13:11:51
ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በክልሉ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም መግለጫቸው ፤ " የትግራይ ህዝብ እራሱን ከጥፋትና ውድመት ለማዳን ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት ከፍሏል። " ያሉ ሲሆን " ጊዜያዊ አስተዳደሩም የትግራይ ህዝብ የታገለለትንና መስዋእትነት የከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት ይሰራል " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው አስተዳደራቸው የትግራይን ግዛታዊ አንድነትን ማረጋገጥ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቄያቸው መመለስ እና የህዝቡን ሁለንተናዊ ችግሮች በፍጥነት መፍታት ዋነኛው አላማው አድርጎ እንደሚሰራ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን እንዲመሩ በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ አብላጫ ድምፅ አግኝተው ከተመረጡ በኃላ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ክልሉን እንዲያስተዳድሩ ርዕሰ መስተዳደር አድርገው እንደሾሟቸው ትላንት የጠ/ሚ ፅ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.3K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 12:25:53
ሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር ተሸካሚ የውሃ ውስጥ ድሮን ሙከራ አደረገች!!

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ኒውክሌር የመሸከም አቅም ያለው የውሃ ውስጥ ሰው አልባ አነስተኛ አውሮፕላን (ድሮን) ሙከራ ማካሄዳቸውን የሀገሪቱ የዜና ጣቢያ ገለጸ፡፡

የውሃ ውስጥ ድሮኑ ከ80 እስከ 150 ሜትር ባለ ጥልቀት ውስጥ በውሃ ውስጥ ከ59 ሰአታት በላይ ከተጓዘ በኋላ በምስራቃዊ የባህር ዳርቻ መፈንዳቱን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል። ድሮኑ በውሃ ውስጥ ከተተኮሰ በኋላ “የራዲዮአክቲቭ ማዕበል” ሊያስነሳ የሚችል መሆኑንም ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ይህንን ሙከራ በበላይነት የመሩ ሲሆን አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ “የሰሜን ኮሪያ ያልተገደበ የኒውክሌር ጦርነትን የመከላከል አቅም በከፍተኛ ፍጥነት እየተጠናከረ መሆኑን እንዲገነዘቡ” ማስጠንቀቂያ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ፖሲዶን ከተሰኙት የሩሲያ የውሃ ውስጥ ተተኳሾች ጋር እንደሚመሳሰሉ የተነገረላቸው የሰሜን ኮሪያ የቅርብ ጊዜ መሳሪያዎች የባሕር ላይ ማዕበል በማስነሳት በአሜሪካ የባህር ዳርቻ ከተሞችን ሊያወድሙ ይችላሉም ነው የተባለው።

“ሚስጥራዊው መሳሪያ” ማክሰኞ ከደቡብ ሃምጊዮንግ ግዛት ወጣ ብሎ በሚገኘው ውሃ ውስጥ መቀመጡም ነው የተነገረው።

“ሃኤይል” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የጦር መሳሪያ የጠላት መርከቦችን እና ወደቦችን በከፍተኛ የራዲዮአክቲቭ ሞገድ ለማጥቃት ታስቦ የተነደፈ መሆኑንም ተሰምቷል፡፡

አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ በአምስት ዓመታት ውስጥ ትልቅ የተባለ የጋራ ልምምዳቸውን ባለፈው ረቡዕ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ በኮሪያ ልሳነ ምድር ዳግም ውጥረት መንገሱ ይነገራል። ይሁንና የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ-ዮል÷ ሰሜን ኮሪያ በግዴለሽነት ለምታደርገው ትንኮሳ ዋጋ ትከፍላለች ሲሉ ተደምጠዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.3K views09:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 10:48:58 የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኦስማን ሳለህ እና የፕሬዝዳንት ኢሳያስ የፖለቲካ አማካሪ የማነ ገ/አብ ወደ ሩሲያ አቅንተው ከአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር መወያየታቸውን የኤርትራ ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል። ኦስማን እና ላቭሮቭ ሶቺ ከተማ ውስጥ፣ በሁለትዮሽና የዩክሬኑን ጦርነት ጨምሮ በዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደተወያዩ ከውይይታቸው በኋላ በሰጡት መግለጫ መግለጣቸውን የማነ ገልጸዋል። ላቭሮቭ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኤርትራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.3K views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 07:07:05
#አብን #ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሀገራዊ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ዙር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ አስታውቀዋል።

በቀጣይም
#በሚያግባቡ_ሀገራዊ_ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ለማድረግና #የጋራ_አቋም ለመያዝ ከስምምነት ላይ መደረሳቸውንም ገልፀዋል።

ሁለቱ ፓርቲዎች የ " ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት " ን ከሽብርተኝነት መዝገብ መሰረዝን በቅድሚያ የተቃወሙ ፓርቲዎች ናቸው።

ፓርቲዎቹ ተቃውሟቸውን በየተናጠል ባወጡት በመግለጫ አሳውቀዋል።

ይህ ከተሰማ ከሰዓታት በኃላ ነው ሁለቱ ፓርቲዎች በሚያግባቡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ለማድረግና የጋራ አቋም ለመያዝ ከስምምነት ላይ እንደደረሱ የተነገረው።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.6K viewsedited  04:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 19:47:33 ከአዲስ አበባ ዙሪያ ወደ ደብረብርሃን ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች መምጣታቸዉ ተገለጸ

ከአዲስ አበባ ዙሪያ ከ3 ሺ በላይ ቤት ንብረታቸው የፈረሰባቸው ተፈናቃዮች ወደ ደብረብርሃን ከተማ ቢጓዙም በከተማው ያሉት ተፈናቃዮች በርካታ በመሆናቸው መቀበል አልቻልንም ሲሉ የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ጌታቸው በላይነህ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ በአንዳንድ አካባዎች ህገ ወጥ መኖሪያ ቤቶች ናቸዉ በሚል በርካታ ነዋሪዎች ከኖሩበት አካባቢ ቤት  እንደፈረሰባቸው የሚወቅ ሲሆን መጠለያ በማጣታቸው ወደ ተለያዩ ክልል ከተሞች  ተፈናቅለው እየገቡ  መሆኑ ተገልፆል፡፡በደብረብርሃን ከተማ ከ24 ሺ 129 በላይ ተፈናቃች በስድስት መጠለያ ጣቢያች የሚገኙ ሲሆን በየእለቱ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል።

ለተፈናቃዮቹ የምግብ ፣የመጠለያ እርዳታ በአፋጣኝ እንደሚያስፈልግ እና የተፈናቃዮች ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ካለ ከፍተኛ ችግር ሊፈጠር ይችላል ተብሏል።በመሆኑም በመጠለያ ጣቢያዎች  ህፃናት ፣ነብሰጡር እናቶች፣ አዛውንቶች እና አካል ጉዳተኞች የሚገኙ ሲሆን ድጋፍ እየመጣ ቢሆን ከተፈናቃዮች ቁጥር አንፃር አነስተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ አሁንም አፋጣኝ ድጋፍ  የሚሻ በመሆኑ መንግስታዊ ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የረድኤት ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ጌታቸው በላይነህ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር በደብረብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
2.0K views16:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 15:50:05
አየር መንገዱ ከየትኛውም ሠራተኞችን ለቅጥር ከሚያቀርብ ድርጅት ጋር የሥራ ስምምነት እንደሌለው አስታወቀ

ሐሙስ መጋቢት 14 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ እራሱን “እንቻለው ልጥገብ የአቪዬሽን ተቋም” ብሎ የሚጠራ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሠራተኞችን ለቅጥር እንዲያቀርብ ከአየር መንገዱ ፍቃድ የሰጠው በማስመሰል ሰዎችን በማሳሳት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የከፈተውን የሂሳብ አካውንት በመጠቀም ገንዘብ በመቀበል ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከተጠቀሰው ድርጅትም ይሁን ከየትኛውም ሠራተኞችን ለቅጥር ከሚያቀርብ ድርጅት ጋር የሥራ ስምምነት እንደሌለው የገለጸ ሲሆን፤፡ አየር መንገዱ ሠራተኞችን የሚቀጥረው በራሱ ዌብሳይት በመግለጽ ሲሆን ከተቀጣሪዎች ምንም አይነት ክፍያ እንደማይቀበል አስታውቋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
2.1K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 12:20:43
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አድርገው ሾሙ።

የኢፌዴሪ የፌዴሬሸን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት፣ እንዲሁም በኢፌዴሪ መንግስት እና በህወሓት መካከል ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና ግጭትን ለማስቆም በፕሪቶርያ ደቡብ አፍሪካ በተደረገው የሰላም ስምምት አንቀጽ (10)መሰረት አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋም በማስፈለጉ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመጋቢት 9፣2015 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ “የትግራይ ክልል አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር ደንብን አጽድቋል፡፡

በዚሁ ደንብ አንቀጽ 3(2) መሰረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አድርገው ሾመዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎችን ውክልና የሚያረጋገጥ እና አካታች የሆነ አስተዳደር በማዋቀር የክልሉን አስፈጻሚ አካል የመምራት እና የማስተባበር ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.2K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ