Get Mystery Box with random crypto!

ከአዲስ አበባ ዙሪያ ወደ ደብረብርሃን ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች መምጣታቸዉ ተገለጸ ከአዲ | LEYU NEWS

ከአዲስ አበባ ዙሪያ ወደ ደብረብርሃን ከተማ ከ3 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች መምጣታቸዉ ተገለጸ

ከአዲስ አበባ ዙሪያ ከ3 ሺ በላይ ቤት ንብረታቸው የፈረሰባቸው ተፈናቃዮች ወደ ደብረብርሃን ከተማ ቢጓዙም በከተማው ያሉት ተፈናቃዮች በርካታ በመሆናቸው መቀበል አልቻልንም ሲሉ የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ጌታቸው በላይነህ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ በአንዳንድ አካባዎች ህገ ወጥ መኖሪያ ቤቶች ናቸዉ በሚል በርካታ ነዋሪዎች ከኖሩበት አካባቢ ቤት  እንደፈረሰባቸው የሚወቅ ሲሆን መጠለያ በማጣታቸው ወደ ተለያዩ ክልል ከተሞች  ተፈናቅለው እየገቡ  መሆኑ ተገልፆል፡፡በደብረብርሃን ከተማ ከ24 ሺ 129 በላይ ተፈናቃች በስድስት መጠለያ ጣቢያች የሚገኙ ሲሆን በየእለቱ የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል።

ለተፈናቃዮቹ የምግብ ፣የመጠለያ እርዳታ በአፋጣኝ እንደሚያስፈልግ እና የተፈናቃዮች ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ካለ ከፍተኛ ችግር ሊፈጠር ይችላል ተብሏል።በመሆኑም በመጠለያ ጣቢያዎች  ህፃናት ፣ነብሰጡር እናቶች፣ አዛውንቶች እና አካል ጉዳተኞች የሚገኙ ሲሆን ድጋፍ እየመጣ ቢሆን ከተፈናቃዮች ቁጥር አንፃር አነስተኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ አሁንም አፋጣኝ ድጋፍ  የሚሻ በመሆኑ መንግስታዊ ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት የረድኤት ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ሲሉ የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ጌታቸው በላይነህ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር በደብረብርሃን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News