Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2023-04-01 16:21:48
279 views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 13:40:21
የፌደራል መንግስት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ መላክ ሊጀምር ነው

የፌደራል መንግስት ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ለትግራይ ክልል የበጀት ድጎማ መልቀቅ እንደሚጀምር የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ተናገሩ። ለክልሉ የሚለቀቀው በጀት፤ ለሌሎች ክልሎች እንደሚደረገው ሁሉ በወራት ተከፋፍሎ የሚላክ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ይህን የተናገሩት፤ ለመንግስት ቅርበት ካለው ፋና ቴሌቪዥን ጋር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን አስመልክቶ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወቅት ነው። የፌደራል መንግስት ለትግራይ በጀት ለማስተላለፍ ከስምምነት ላይ መድረሱን በተመለከተ አቶ ጌታቸው ረዳ ከቀናት በፊት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የሰጡትን ቃል፤ ሚኒስትር ዲኤታው ትላንት አርብ መጋቢት 22፤ 2015 ምሽት በተሰራጨው ቃለ ምልልሳቸው አረጋግጠዋል።

ባለፈው ሳምንት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተሾሙት አቶ ጌታቸው፤ የፌደራል መንግስት በጀት መፍቀዱን፤ ሆኖም የገንዘብ መጠኑን በተመለከተ ግን “ገና እንነጋገራለን” ማለታቸው ይታወሳል። የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው በበኩላቸው፤ የትግራይ ክልል በጀት “የሚታወቅ” መሆኑን ገልጸዋል። የፌደራል መንግስት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እስኪቋቋም የበጀት ድጎማ ሳይለቅቅ ቢቆይም፤ በክልሉ ውስጥ ያሉ የፌደራል ተቋማትን ግን አስቀድሞ “ወደ ስራ ማስገባቱን” ዶ/ር እዮብ ተናግረዋል። ለዚህም በምሳሌነት የጠቀሱት የመብራት እና የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እንዲሁም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ነው።
@Leyu_News
  @Leyu_News
781 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 12:50:17 በደራ ወረዳ የ14 ዓመት ታዳጊ አግተው 100 ሺህ ብር የተቀበሉት ግለሰቦች በገንዘብ ክፍፍል ተጣልተው በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ በርበሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጋምቤላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ14 ዓመት ታዳጊ በማገት 100 ሺህ ብር ቢቀበሉም በገንዘብ ክፍፍል ባለመስማማት በመካከላቸው በተፈጠረ ግጭት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ወንጀል ምረመራ ፍትህ ማስፈጸም ዲቪዥን ረዳት ኢንስፔክተር  በላይ ከተማ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አቶ ቃሲም ሱሌማን የተባሉ በአካባቢው የታወቁ ግለሰብ ሲሆኑ ውጪ ሀገር  ካሉ ልጆቻቸው  ገንዘብ እንደተላከላቸው በማጣራት አብሯቸው የሚኖረውን የ14 ዓመት ታዳጊ ልጃቸውን የድርጊቱ ፈፃሚዎች ያግታሉ። ከውጪ ከተላከው ገንዘብ  150 ሺህ ብር እንዲሰጧቸው ካልሆነ ልጁን እንደሚገሉት አቶ ቃሲም ላይ ይዝቱባቸዋል።

በዚህም የተጨነቀው ቤተሰብ ከልጁ ህይወት አይበልጥም በማለት በድርድር 100ሺህ ብር ለመክፈል በመስማማት ለፖሊስ ሳያሳድቅ ገንዘቡን በመስጠት ልጃቸውን ያስመልሳሉ፡፡ ይሁን እና ገንዘቡን ከተቀበሉ በኋላ ዘነበ የተባለው አንደኛ  ተከሳሽ  88 ሺህ ብር በመያዝ ለሁለተኛ ተከሳሽ አርቀው 12 ሺህ ብር ብቻ በመስጠት ይሄ ብቻ ነው የሚገባህ በሚል መጠጥ ቤት ውስጥ ይጋጫሉ፡፡

መጠጥ  ቤት ውስጥ በመካካላቸው በተፈጠረ ግጭት ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል። ተጠርጣሪዎቹ ፖሊስ በቁጥጥር ስር በማዋል ጉዳዩን እየመረመረ መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር በላይ ከተማ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
877 views09:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 07:34:23
የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት መመስረቻ ስምምነት ፈራሚዋ ደቡብ አፍሪካ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ለ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ ሲሄዱ እንደምታስተናግዳቸው ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ናለዲ ፓንዶር በኩል አስታውቃለች።

የዓለማቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፑቲን በዩክሬን "የጦር ወንጀል ፈጽመዋል" በማለት የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ፣ በቀጣዩ ነሐሴ የ"ብሪክስ" አገራት የመሪዎች ጉባኤ አዘጋጇ ደቡብ አፍሪካ አቋሟ ምን እንደሚኾን በጉጉት ሲጠበቅ ነበር። ደቡብ አፍሪካና ሩሲያ በሌሎች አገራት ግፊት በድንገት ጠላት ሊኾኑ አይችሉም ያሉት ፓንዶር፣ ፑቲንን በጉባኤው እንዲገኙ እንደተጋበዙ ተናግረዋል። በዓለማቀፉ ፍርድ ቤት ስምምነት መሠረት፣ ደቡብ አፍሪካ ፑቲን ግዛቷን ከተረገጡ አስራ ለፍርድ ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባት። "ብሪክስ" በፍጥነት በማደግ ላይ ያሉት ኃያላኑ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድና ብራዚል የመሠረቱተ ቡድን ነው።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.3K views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 21:13:40 በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት እርምጃ ጋር በተያያዘ የአንድ ሰው ህይወት ህልፈት ሪፓርት እንደደረሰው ኢሰመኮ አስታወቀ።

በቤት ማፍረስና በግዳጅ ማንሳት እርምጃ ለተጎዱ ሰዎች በሕጋዊ መንገድ የመኖሪያ ቤት የሚያገኙበትና ለደረሰባቸው የንብረት ውድመት ሊካሱ የሚችሉበት መንገድ በአፋጣኝ ሊመቻች እንደሚገባ አሳስቧል፡፡ 

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተካሄደ ያለው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ ማስነሳት እርምጃ የመኖሪያ ቤት አልባነትን አባብሷል ብሏል።

ኢሰመኮ በጉዳዩ ዙሪያ በለገጣፎ ለገዳዲ፣ በሰበታ  አካባቢ ፉሪ እና ለቡ ተክለሃይማኖት እንዲሁም በቡራዩ ገፈርሳ ኖኖ አካባቢዎች በመዘዋወር ቀደም ሲል የፈረሱ እና የማፍረስ ተግባሩ እየተከናወነ የነበረባቸውን አካባቢዎች ተመልክቻለሁ ነው ያልው፡፡

ኮሚሽኑ በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለ ከተማ በመገኘት
እየፈረሱ የነበሩ ቤቶችንም ለመመልከት ችሏል።

በምልከታው የቤት ማፍረሱ እና በግዳጅ ማስነሳቱ በግብረ ኃይል እየተከናወነ እንደነበረ እና በቦታው ከፖሊስ፣ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ አባላት በተጨማሪ ሌሎች ዱላ የያዙ ሲቪል ሰዎች እንደነበሩም መመልከቱን ነው ያሳወቀው።

በዘመቻ ቤት የማፍረሱ ሂደት ተገቢ ልየታ ያልተደረገበት ስለመሆኑ  ፣ አድሏዊ አሰራሮች መኖራቸውና ይህም ከብሔር ማንነት ጋር የተገናኘ መሆኑን፣ እና በቂ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ ቤቶች እንደሚፈርሱ መረዳቱን ገልጿል።

እስር፣ የአካል እና የስነልቦና ጉዳት መድረሱንም በሪፓርቱ ኢሰመኮ አትቷል።

ፊሊዶሮ በተባለ ቦታ ላይ በተደረገው የቤት ፈረሳ የሰው ሕይወት ማለፉን ኢሰመኮ መረጃ የደረሰው ሲሆን ይህን በተመለከተ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አስታውቋል። 

ኢሰመኮ ከአቤቱታ አቅራቢዎች እና ተገቢነት ካላቸው የመንግሥት አካላት ባሰባሰበው መረጃ እና ማስረጃ መሠረት የማፍረስና በግዳጅ የማንሳት እርምጃው በርካታ ቤተሰቦችን ለከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ቀውስ ዳርጓል፤ ተማሪዎች ከትምህርታቸው ለማቋረጥ ተገደዋል፤ በርካታ ቤተሰቦች የእለት ተእለት ተግባራቸውን ማከናወን የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል፤ በርካታ ቤተሰቦች ተፈናቅለው ወደ ሌሎች ቦታዎች ለመሄድ ተገደዋል፤ ከፊሎቹም መንገድ ላይ ወድቀዋል ወይም በተለያዩ የሀገር ውስጥ መጠለያ ጣቢያ በመሰብሰብ የመንግሥት እርዳታ ለመጠባበቅ ተገደዋል" ነው ያለው፡፡ 

የክልሉ መንግሥትና የከተማ አስተዳደሩ የማፍረስና በግዳጅ የማንሳት እርምጃውን ተግባራዊ ከማድረግ በፊት ቤቶቹ እንደተገነቡበት የይዞታ ዓይነትና ሁኔታ፣ ለብዙ ዓመታት የመብራት እና የውሃ እንዲሁም ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን እየሰጠ እና ነዋሪዎቹ የማኅበራዊ ሕይወት እንዲመሠርቱ ሲያደርግ የቆየ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት አማራጭ መፍትሔዎችን በማመቻቸት የሰብአዊ መብቶች መከበራቸውንና መጠበቃቸውን ሊያረጋግጥ ይገባ እንደነበር አስገንዝቧል፡፡ 

በቤት ማፍረስና በግዳጅ ማንሳት እርምጃ ለተጎዱ ሰዎች በሕጋዊ መንገድ የመኖሪያ ቤት ሊያገኙ የሚችሉበት መንገድና ለደረሰባቸው የንብረት ውድመት ሊካሱ የሚችሉበት መንገድ በአፋጣኝ ሊመቻች እንደሚገባ አሳስቧል፡፡ 

የኢሰመኮ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ብራይትማን ገብረሚካኤል “ኢመደበኛ ይዞታዎቸን መከላከል የመንግሥት ኃላፊነት ቢሆንም የማፍረስና በግዳጅ የማንሳት እርምጃዎች ሰዎች ሕይወታቸው እንዲናጋ እና ቤተሰብ እንዲበተን የሚያደርግ መሆን የለበትም፤ ይልቁንም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች የተከበሩበት አሠራር መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል” ብለዋል፡፡ 

@Leyu_News
@Leyu_News
876 views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 20:26:06 በሱዳን የሚገኙ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸዉ መሆኑን ቢናገሩም የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሱዳን አሁንም በርካታ ኢትዮጵያውያን በሰላም የሚኖሩባት ሀገር ናት ብሏል

የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ አለም በትላንትናዉ እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፤ ብስራት ራዲዮ በሀገሪቱ ስለሚኖሩ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው ስላሉ ዜጎች ጥያቄ አቅርቦላቸዉ ነበር።አምባሳደሩ በምላሻቸዉ ፤ ሱዳን አሁንም በርካታ ኢትዮጵያውያን በሰላም የሚኖሩባት ሀገር ናት ሲሉ ተናግረዋል።

በሱዳን የሚኖሩ ዜጎችን ዋቢ አድርጎ በሰራዉ ዘገባ መሰረት በሰነድ አልባ ኢትዮጵያዉያን ላይ እስር እና በወህኒ ቤቶች ዉስጥ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል። ሰነድ አልባ የሆኑ ዜጎች ከሚፈጸምባቸዉ እስር በላይ በእስር ሳሉ ይፈጸምባቸዋል የተባለዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ይነሳል፡፡

"የትኛዉም ሀገር ላይ ህጋዊ ሰነድ ሳይኖር መንቀሳቀስ አይቻልም" ያሉት አምባሳደሩ፤ "የሱዳንን ህዝብ ዉለታ መብላት አይገባም" ሲሉም ተደምጠዋል።ካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፤ በሱዳን ከሚኖሩ ዜጎች በእስር ላይ ላሉ ሰዎች ተገቢዉን ጥበቃ እንዲያገኙ እያደረገ አይደለም በሚል ቅሬታ ቢነሳበትም ፤ አምባሳደሩ በምላሻቸዉ ችግሮች ሲከሰቱ ኤምባሲው ከሀገሪቷ መንግስት ጋር በመነጋገር እንዲፈቱ ይሰራል ብለዋል።

በሀገሪቷ የሚገኙ ሰነድ አልባ ዜጎች በእስርቤቶች ዉስጥ የአስገድዶ መድፈር ፣ የግዳጅ የጉልበት ስራ ፣ የምግብ ክልከላ እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተፈጸመባቸው መሆኑን መናገራቸዉ ይታወሳል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
1.0K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 16:56:33
አሳዛኝ መረጃ

በቻግኒ ተማሪዎችን ለጉብኝት ይዞ ሲጓዝ በነበረ መኪና ላይ በደረሰ አደጋ የ4 ህጻናትና የ1 መምህርት ህይወት አለፈ።

በአዊ ብሔረሰብ አሰተዳደደር በባንጃ ወረዳ የዳሳሽ አካዳሚ ት/ት ቤት ተማሪዎችን ወደቻግኒ ታሪካዊ ቦታዎችን ለማስጎብኘት ይዞ በመጓዝ ላይ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 4 ህፃናትና የአንድ መምህርት ህይወት ማለፉ ተገልጿል።

አደጋው የደረሰው በባንጃ ወረዳ ዚቅ ጎመርታ ቀበሌ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ላይ ሲሆን 3 የህፃናት ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ አንድ ህፃንና እና የአንዲት መምህር ወደህከምና እንደደረሱ ህይወታቸው ማለፉን ወረዳው አስታውቋል።
@Leyu_News
@Leyu_News
1.5K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 13:50:38
የኤርትራ ወታደሮች ከተቆጣጠራቸው የኢሮብ ወረዳ አካባቢዎች እንዳልወጡ የወረዳዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትና መሠረታዊ አገልግሎቶች እያገኘን አይደለም ብለዋል።ከኢሮብ ወረዳ ረዥም ርቀት በእግራቸው ተጉዘው የስልክ አገልግሎት ወዳለበት ዓዲግራት የመጡ የብሔረሰቡ ተወላጆች እንደሚሉት፣ የኤርትራ ጦር ተቆጣጥሯቸው ባሉ የኢሮብ ወረዳ አካባቢዎች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ግፍ ይፈፀማል፣ ረሀብ አለ፣ የተለያዩ ማሕበራዊ ቀውሶችም ተከስተዋል።

[DW]

@Leyu_News
@Leyu_News
1.7K views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 10:54:02
የ2024ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የሚካሄድበት ቀን ይፋ ሆነ!!

በኮትዲቯር አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2024ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የሚካሄድበት ወር እና ቀናቶች በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ይፋ ተደርገዋል፡፡

ካፍ በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው÷ የ2024ቱ የአፍሪካ ሀገራት እግር ኳስ ውድድር ከፈረንጆቹ ጥር 13 እስከ የካቲት 11 ቀን 2024 ይካሄዳል፡፡

እስካሁን ባለው የሀገራቱ የማጣሪያ ውድድር አልጀሪያ፣ ሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሴኔጋል ከአስተናጋጇ ኮትዲቯር ጋት ለውድድሩ ቀድመው ማለፋቸውን ያረጋገጡ ቡድኖች ናቸው።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.8K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 08:51:34
ሰበር ዜና

የክልል ልዮ ሀይል የተባለው ወታደራዊ አደረጃጀት መሉ በሙሉ እንዲፈርስ ትዕዛዝ ተላልፏል። ልዮ ሀይሉ ሲፈርስ ወደ መደበኛ መከላከያ ስራዊት የሚቀላቀሉ ሲሆን የቀረው መደበኛ ፖሊስ ሆኖ ይቀጥላል። ልዮ ሀይሉ የያዛቸውን የስራ ድርሻ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ስራዊት ይረከባቸዋል።
አንድ ፖሊስ ( በፌደራል ፖሊስ ዕዝ የሚመራ) አንድ የኢትዮዽያ መከላከያ ስራዊት ብቻ ሆነው ይቀጥላሉ።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.9K views05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ