Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 32

2023-03-31 08:21:02 ትራምፕ ለወሲብ ፊልም ተዋናይቷ በዝግ የገንዘብ ክፍያ በመፈፀማቸው ሊከሰሱ ነው

በ235 ዓመታት የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ታሪክ የወንጀል ክስ የቀረበባቸው የመጀመሪያው ትራምፕ ይሆናሉ።


ክሱ የሚያተኩረው ከ2016 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በፊት ትራምፕን ወክለው ጠበቃቸው በኩል ለወሲብ ፊልም ተዋናይ ለሆነችው ስቶርሚ ዳኒልስ ዝምታን እንድትመርጥ ገንዘብ ተሰጥቷታል በሚል ነው። በጁላይ 2006 በተካሄደው የበጎ አድራጎት የጎልፍ ውድድር ላይ ትራምፕን እንዳገኘቻቸው የምትናገረው ዳኒልስ በካሊፎርኒያ እና ኔቫዳ መካከል ባለው የመዝናኛ ስፍራ በታሆ ሀይቅ በሚገኘው ሆቴል ክፍል ውስጥ የግብረስጋ ግንኙነት መፈፀማቸውን ተናግራለች።

ዶናልድ ትራምፕ ለቀድሞ የወሲብ ፊልም ኮከብ ስቶርሚ ዳኒልስ ከግኝኑነቱ በኃላ ዝም እንድትል ክፍያ መፈፀማቸው ለክሱ ምክንያት ሆኗል።ትራምፕ ላይ የሚቀርበው የክስ ዝርዝር ግን እስካሁን ግልፅ አይደለም። ስቶርሚ ዳንኤል ከቀድሞው ፕሬዝደንት ጋር አመንዝራ እንደነበረች ተናግራለች፣ እናም ዝም እንድትል ክፍያ እንደተፈፀመላት ተናግራለች።

በ235 ዓመታት የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች ታሪክ ውስጥ የወንጀል ክስ የቀረበባቸው የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይሆናሉ።አንዳንድ የዴሞክራቲክ ህግ አውጭዎች የትራምፕ ፐክስ ዜና ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈጣን ሆነዋል። የቀድሞው ፕሬዚዳንት በመጨረሻም ለድርጊታቸው ተጠያቂ በመሆን ለእስር ይዳረጋሉ ሲሉ የካሊፎርኒያ የዲሞክራት ተወካይ አዳም ሺፍ ተናግረዋል።

የሪፐብሊካኑ አባላት በበኩላቸው ከትራምፕ ጎን መሆናቸውን እየገለፁ ይገኛል። ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ከኤቢሲ ዜና  በስልክ ባደረጉት ቆይታ ክሱ "በአገራችን ላይ የተፈፀመ ጥቃት" እና "ፖለቲካዊ " ነው ብለዋል። "በቀጣዩ ምርጫ ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር እየሞከሩ ነው" ሲሉ አክለዋል።


ትራምፕ በ2024 ውድድር እንደገና ለፕሬዚዳንትነት እጩ ሆነው ቀርበዋል። የትራምፕ ጠበቆች ሱዛን ኔቸሌስ እና ጆሴፍ ታኮፒና በሰጡት መግለጫ “ፕሬዚዳንት ትራምፕ ተከሰዋል ግን ምንም አይነት ወንጀል አልሰሩም፤ ይህንን የፖለቲካ ክስ በፍርድ ቤት አጥብቀን እንታገላለን” ሲሉ ተናግረዋል
#ዳጉ_ጆርናል

@Leyu_News
@Leyu_News
1.7K viewsedited  05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 08:21:02
1.6K views05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 21:17:07
#Update

" ከእስር ተፈተው ወደ ቤታቸው ገብተዋል "

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ ከእስር ተፈቱ።

በዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እና በሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ መዝገብ ተከስሰው በእስር ላይ የነበሩ የህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21፤ 2015 አመሻሽ ላይ ከእስር መፈታታቸውን የተከሳሾቹ ጠበቆች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሃፍቶም ከሰተ ተናግረዋል።

ጠበቃው ይህን የተናገሩት ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ ነው።

በዛሬው ዕለት ከእስር ተለቅቀው ወደ ቤታቸው መግባታቸው ከተረጋገጡ ተከሳሾች ውስጥ ፦ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እና ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ እንደሚገኙበት ጠበቃው አረጋግጠዋል።

#ኢትዮጵያ_ኢንሳይደር

@Leyu_News
@Leyu_News
2.0K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 21:17:07
1.8K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 19:23:38
በህወሓት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ላይ የተመሰረተው ክስ ተቋረጠ

በወንጀል ተጠርጥረው ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ክሳቸው መቋረጡን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የፍትህ ሚኒስቴር ዛሬ ሐሙስ መጋቢት 21፤ 2015 ባወጣው መግለጫ፤ ከግጭቱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወንጀሎች ተጠያቂነት በተመለከተ በሽግግር ፍትህ ማዕቀፍ ሊታዩ እንደሚገባ ስምምነት መደረሱን ገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዚሁ መግለጫው በህወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ የተቋረጠው፤ በፌዴራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ በተፈረመው የሰላም ስምምነት መሰረት መሆኑን ጠቁሟል፡፡ (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@Leyu_News
@Leyu_News
2.0K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 19:17:45
ሰበር_ዜና

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።

በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል። (ምንጭ፣EOTCTV)

@Leyu_News
@Leyu_News
1.9K views16:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 13:24:22
ከ6ኛ ፎቅ ላይ በመዝለል ራስን የማጥፋት ሙከራ የፈጸመችው የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነርስ በሕይወት ተረፈች

ተጎጂዋ ከአደጋዉ በሕይወት ብትተርፍም ከባድ ጉዳት ደርሷባታል

ሐሙስ መጋቢት 21 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ዛሬ ሌሊት 10:30 በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዉስጥ አዋላጅ ነርስ የሆነች ዕድሜዋ 40 የተገመተ ነርስ ከሆስፒታሉ ከ6ኛ ፎቅ ላይ ዘላ ወደ ምድር በመዉደቋ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባት የእሳት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል፡፡

ከ6ኛ ፎቅ ላይ በመዝል ወደ ታችኛዉ ወለል ላይ የወደቀችዉን ተጎጂ ከወደቀችበት ለማንሳት ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ ለኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጥሪ መደረጉን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችም በመሰላልና በገመድ በመጠቀም ተጎጂዋን በሕይወት ማውጣት መቻላቸው ተነግሯል።

ተጎጂዋ በሆስፒታሉ ተረኛ አዋላጅ ነርስ ሆና ምሽቱን የተለመደ ሥራዋን ከባልደረቦቿ ጋር ስታከናዉን ቆይታ መስኮቱ ላይ ወንበር ካስቀመጠች በኋላ ዘላ ወደ ምድር መዉደቋን ንጋቱ ማሞ ጨምረዉ ለሬዲዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
2.1K views10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 12:08:17
የምጽአት ቀን በአካባቢያችን ይኖራል በሚል የሰጉ 100 የዩጋንዳ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን አምባሳደር መለሰ አለም ተናገሩ!

የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ ዓለም በዛሬው እለት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ዋና ዋና የውጭ ዲፕሎማሲ ተግባራት ላይ መግለጫና ማብራሪያ ሰጥዋል። በመግለጫው የሰላም ዲፕሎማሲ ከኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ጋር በማስተሳሰር እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ረገድ ከሳዑዲ ዜጎችን የማምጣት ተግባር ከተጀመረ ድፍን አንድ አመት የሆነው ሲሆን በዚህ አንድ አመት ውስጥ 125ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገርቤት መመለስ መቻሉ አምባሳደር መለሰ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ የምጽአት ቀን በአካባቢያችን ይኖራል በሚል የሰጉ ከሴራሬ እና ኩሚ ከሚባሉ ቦታዎች ወደ 100 የሚጠጉ ዜጎች በድንበር በኩል ወደ ኢትዪጵያ የገቡ መሆኑን ለማወቅ መቻሉን አንስተዋል። እነዚሁ ምፅዓት የሰጉ የኡጋንዳ ዜጎች በኛንጋቶም መስፈራቸውን ተናግረዋል።

ከምስራቃዊ ዩጋንዳ ተነስተው በድንበር በኩል ሰላም እና መረጋጋት ለማግኘት ኢትዮጵያ መጥተዋል ዝርዝር ጉዳይ በቀጣይ ይገልፃል ሲሉ ቃል አቀባይ አክለዋል።በተጨማሪም ወደ እስያ ሀገራት የሚደረግ ህገወጥ ጉዞ በተለይ ደግሞ መዳረሻቸውን ማይንማር/በርማ እና ላኦስ ያደርጉ ሲሆን እነዚህንም ዜጎች ወደ ሀገር ለመመለስ እየተሰራ ስለመሆኑ ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል።

@Leyu_News
@Leyu_News
270 views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 10:12:33
በሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተኮሱት በተባለ ጥይት ሦስት ሰዎች መገደላቸውንና ስድስቱ መቁሰላቸውን ሰምቻለሁ ሲል አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

ሰዎቹ የተገደሉት፣ ሰኞ'ለት የአይሻ ወረዳ ነዋሪዎች መከላከያ ሠራዊት በሱማሌ ክልልና አፋር ክልል የድንበር ውዝግብ የአፋር ክልል ልዩ ኃይልን ያደግፋል በማለት ተቃውሟቸውን ለማሰማት አደባባይ በወጡበት ወቅት እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከመድረሳቸው በፊት፣ ተቃዋሚዎች የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ሐዲድ መስመርን ዘግተው እንደነበርና መስመሩን ለማስከፈት በተፈጠረ ውዝግብ ሰዎቹ እንደተገደሉ ምንጮች ነግረውኛል ሲል ዜና ምንጩ አትቷል።

በሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተኮሱት በተባለ ጥይት ሦስት ሰዎች መገደላቸውንና ስድስቱ መቁሰላቸውን ሰምቻለሁ ሲል አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

ሰዎቹ የተገደሉት፣ ሰኞ'ለት የአይሻ ወረዳ ነዋሪዎች መከላከያ ሠራዊት በሱማሌ ክልልና አፋር ክልል የድንበር ውዝግብ የአፋር ክልል ልዩ ኃይልን ያደግፋል በማለት ተቃውሟቸውን ለማሰማት አደባባይ በወጡበት ወቅት እንደኾነ ዘገባው ጠቅሷል። የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከመድረሳቸው በፊት፣ ተቃዋሚዎች የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ሐዲድ መስመርን ዘግተው እንደነበርና መስመሩን ለማስከፈት በተፈጠረ ውዝግብ ሰዎቹ እንደተገደሉ ምንጮች ነግረውኛል ሲል ዜና ምንጩ አትቷል።

@Leyu_News
@Leyu_News
565 views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 10:10:10
ፖፕ ፍራንሲስ ሆስፒታል ገቡ!

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በመተንፈሻ አካላት የጤና ችግር ምክንያት ሆስፒታል ገቡ።ፖፕ ፍራንሲስ ከመተንፈሻ አካላት ህመም ጋር በተያያዘ ለጥቂት ቀናት ሮም በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ሊቆዩ እንደሚችሉም ቫቲካን አስታውቋል።

የ86 ዓመቱ አባ ፍራንሲስ በቅርብ ቀናት ውስጥ የመተንፈስ ችግር እንደገጠማቸው ነገር ግን በኮቪድ-19 አልተያዙም ሲል መግለጫው አክሏል።“ለተወሰኑ ቀናት ተገቢ የሆስፒታል ህክምና ያስፈልጋቸዋልም” ብሏል የቫቲካን መግለጫ።“ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በደረሷቸው በርካታ መልዕክቶች ልባቸው የተነካ ሲሆን እየተደረገላቸው ላለው ጸሎትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል” ሲልም አክሏል።

የአባ ፍራንሲስ ጥበቃን ጨምሮ የቅርብ ሰራተኞቻቸው በጌሚሊ ሆስፒታል እንደሚቆዩም ለጉዳዩ ቅርበት ያለው ግለሰብ ለቢቢሲ ተናግሯል።ለአባ ፍራንሲስ ይህ ወቅት በዓመቱ ውስጥ በሥራ የሚጨናነቁበት ጊዜም ነው።

የካቶሊክ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዐቢይ ጾምን እየጾሙ ሲሆን በመጨረሻው ሳምንትም የህማማት፣ ስቅለትና ፋሲካ በዓላትን ያከብራሉ።ለእነዚህም ክብረ በዓላት አባ ፍራንሲስ እየተዘጋጁ እንደሆነ ተነግሯል።በዚህ ሳምንት እሑድ የሆሳዕና በዓል የሚከበር ሲሆን ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የህማማት ሳምንት እንዲሁም የትንሳዔ በዓል ይከበራል።

[BBC]

@Leyu_News
@Leyu_News
486 views07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ