2023-03-28 12:36:37
አቶ ክርስቲያን ታደለ "ስልጣን በመልቀቅ የመፍትሄው አካል አይሆኑም ወይ? ብለው ለጠየቁት ጥያቄ ጠ/ሚንስተሩ የሰጡት ምላሽ?
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሰጡት ምላሽ፦
"ስልጣን ብትለቅ የተባለው በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው ፤ ግን ጥሩ የሚሆነው ስልጣን ብንለቅ ነበረ ምክንያቱም መንግስት ማለት አስፈፃሚ ብቻ ማለት አይደለም። ህግ አውጪ መንግስት ነው፣ ህግ ተርጓሚ መንግስት ነው ፣ አስፈፃሚ መንግስት ነው እኛ እዚህ ያለን ሰዎች የመንግስት ባለስልጣኖች ነን።
ይልቁኑንም የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ደግሞ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው የአንድ ሚኒስትር አለቃ ናቸው እና በጋራ ብንለቅ ቢሆን ምክንያቱም እርሶም እንደሚገነዘቡት የሁሉ ችግር ምንጭ እና ባለቤት እኔ ብቻ ልሆን አልችልም። ኃላፊነት ከወሰድንም በጋራ ቢሆን ጥሩ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
ነገር ግን ይሄን ጥያቄ እሳቸው ቢያነሱትም እሳቸው ላይም ይነሳ ነበር በውጭ ያሉ እንደሳቸው ፓርላማ አሸንፈው መግባት ያልቻሉ ሰዎች ለምንድነው እኚህ ሰውዬ የቋሚ ኮሚቴ ኃላፊነት ላይ የተቀመጡት አይለቁም እንዴ ? እያሉ ከዚህ ቀደም በሚዲያ እንደምትሰሙት ብዙ ይተቻሉ፤ እርሶ ምርጫ አሸንፈው ነው የገቡት እዚህ ተቀምጠው የህዝቡን ጥያቄ ማንሳትዎ ተገቢ ነው ብዬ ማስበው መቆጣጠሩም የሚያደርጉት ጥረትም።
ግን ከስልጣን ጋር ተያይዞ ያለውን ጉዳይ በአንድ ቀላል ምላሴ ለማስረዳት በደቡብ ህንድ ጦጣን የማጥመድ ቴክኒክ አለ ጦጣን እንደምታውቁት ቁንጥንጥ ናት፣ ቅብዝብዝ ናት ለአደን አትመችም እና በደቡብ ህንድ ያሉ አዳኞች ጦጣን ለማጥመድ የኮኮናት ፍሬ በጦጣ እጅ ልክ በቀጭኑ ይቀዱና ከውሥጥ ሩዝ ያስቀምጣሉ ሲቀዱት የጦጣ እጅ ቀጭን ስለሆነ በዚያ ልክ ይቀዱትና ውስጥ ግን ሰፋ አድርገው ሩዝ ያስቀምጣሉ፤ሊይዟት ስለማይችሉ ጦጣ ሩዝ አየሁ ብላ እጇን ሰዳ ካፈሰች በኃላ ልውጣ ስትል የተሰራው ለቀጭኑ ስለሆነ ከጨበጠች በኃላ አይለቃትም።
ይቺ ጦጣ የሰው ሩዝ ነው የያዝኩት የማይገባኝን ሩዝ ነው የያዝኩት ይዤው ከቆየሁ ልያዝ እችላለሁ በትኜው ልሂድ አትልም እንደጨበጠች ትታገላለች በዚህ ጊዜ ያን የኮከናት ፍሬ መውሰድ ስለማትችል አዳኙ መጥቶ ይይዛታል። ጦጣዋን ያደናት የያዛት ምንድነው ያላችሁ እንደሆነ ሃሳቧ ነው እንጂ ወጥመዱ አይደለም፤ እዛው በትና በትለቅ ትወጣለች በሀሳብ ግን ሩዝ አፍሼ ካልወጣሁ ስላለች ሀሳቧ አጥምዶ ያስቀራታል እዛው።
ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እንደሚባለው ቁጭ ብለው የሚያልሙ ሰዎች አሉ ሁል ጊዜ በዚያ መንገድ ጥሩ አይሆንም።
ሁለተኛ ቢጨበጥ ጥሩ የሚሆነው ስልጣንን በሚመለከት በእኔ እና በተከበሩ አቶ ብናልፍ መካከል የሚደረግ ድርድር የለም። የስልጣን ባለቤት ህዝብ ነው፤ስልጣን ሰጪም ነፋጊም ህዝብ ነው፤እኔ ና አቶ ብናልፍ ማድረግ ያለብን የተሻለ ሃሳብ ይዘን ህዝባችን ጋር መቅረብ እና የኔን ሃሳብ ምረጥልኝ ብለን በሰጪው ነው የምንመረጠው እንጂ በምክር ቤት ውስጥ ስጠኝ ልቀቅልኝ በሚል አይሆንም።
ሰጪው ጋር ሃሳብ የተሻለ ይዞ መቅረብ ታስፈልጋል፤ ስለዚህ ስልጣን በኮሮጆ እንጂ በመናጀ አይያዝም እና ሶስት ዓመት ይቅራል ለምርጫ በውጭም አሉ ይሄ የኦሮሞ መንግሥት ይሄ የኦሮሞ መንግስት እያሉ የሚዘፍኑ ዘፋኞች አሉ እነሱን ጨምሮ ሰብሰብ ብሎ ሃሳብ አጠናክሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ነው እኛ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደተባለድ የተገባውን ቃል ካልመለስን የኢትዮጵያ ህዝብ በእኛ አስተዳደር ካልረካ በምርጫ ከጣለን በተደጋጋሚ እንዳልነው በደስታ እናስረክባለን። ፓርቲዎች መዘጋጀት ያለባቸው ሃሳብ ይዘው መምጣት ነው፤ አሁን ሃሳብ የለም፤ ሰብሰብ ብሎ ሃሳብ ይዞ ያን ወደ ህዝብ አቅርቦ ለመመረጥ እና ለማሸነፍ የሚደረግ ጥረት ለሁላችን የሚጠቅመን ይሆናል" ብለዋል።
@Leyu_News
@Leyu_News
1.9K views09:36