Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2023-03-30 07:31:37
የአውሮፓ ሕብረት 60 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን በአዲስ አበባ የሕብረቱ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ሕብረቱ በአጠቃላይ የ331 ሚሊየን ዩሮ ሰብዓዊ ድጋፍ ለአፍሪካ ቀንድ እንደሚሰጥ ይፋ ያደረገ ሲሆን÷ ይህም በዋናነት ለምግብ ዋስትና፣ ለተፈናቀሉ/ስደተኞች፣ ለአደጋ ዝግጁነት እንዲሁም ለትምህርት እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡

በመሆኑም ሕብረቱ ከዚህ ውስጥ በ2023 በግጭት እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ለሚደረጉ ሰብዓዊ ተግባራት ድጋፍ የሚውል ከ60 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ በላይ ገንዘብ በኢትዮጵያ ለሚያከናውነው የሰብዓዊ ረድኤት ስራ መመደቡ ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ875 ሺህ በላይ ስደተኞች እንዳሉ ይታመናል፡፡በተለይም ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ሱዳን የመጡ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች መሆኗም ነው ተጠቆመው፡፡ ሕብረቱ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እየሠራ መሆኑንም ገልጿል።

 @Leyu_News
@Leyu_News
778 views04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 20:44:48
"ሕክምና መከልከል ከመግደል እኩል ነው!

#አቶ_ክርስቲያን_ታደለ (የህ/ተ/ም/ቤት አባል)

*
በሕመም ላይ የሚገኙትን ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ በቤታቸው ተገኝተን ጠይቀናቸዋል። ስለጤናቸው እና የሕክምና ፍላጎታቸውም ማብራሪያ ሰጥተውናል።

ጄኔራል መኮንኑ ሕክምና የጠየቃቸው የእግር ሕመም ለአገራቸውና ለሕዝባች ሲሉ ሲታገሉ በጥይት በመመታታቸው ነው። ለአገር እና ሕዝብ የተዋጉት ጄኔራል ደማቸውን ያፈሰሱት ለግል ፍላጎታቸው ሲባዝኑ አልነበረም። እንደወጉ ቢሆን የአገር መከላከያ ሰራዊት የእኒህን ጄኔራል መኮንን የሕክምና ወጪ በመሸፈን ደረጃውን የጠበቀ ሕክምና እንዲያገኙ ማስቻልን ጨምሮ አስፈላጊ ነገሮችን ሁሉ መፈፀም ነበረበት። «ጽድቁ ቀርቶ በቅጡም በኮነነኝ» እንዲሉ በደጋጎች ቸር አድራጎት ታግዘው ሕክምና ለማድረግ ወደ እስራኤል ለመብረር ቢወጥኑም የኤርፖርት የፀጥታ ኃላፊዎች «የበላይ አካል ትእዛዝ» ነው በሚል ፓስፖርታቸውን ቀምተው «ቀርቷል» የሚል ቃል በእስክርቢቶ ጽፈውበት ጉዞ ከልክለዋቸዋል።

አፈናው ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ አትገባም ከሚል ለሕክምና ከኢትዮጵያ አትወጣም ወደሚል ተዛምቷል። አትወጣም ማለት አትታከምም ማለት ነው። አትታከምም ማለት ደግሞ እንድትሞት እንፈልጋለን ማለት ነው። አፈናው ከዚህ ደርሷል።

መላው ኢትዮጵያውያን መንግስት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ሕክምና በመከልከል በሕይወታቸው ላይ አደጋ እንዲወድቅ የሚያደርገውን አፈና እንዲያወግዙ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ለጄኔራል መኮንኑም ፈጣሪ ምሕረትን እንዲያመጣላቸው በጎውን ሁሉ እንመኛለን።"


#አቶ_ክርስቲያን_ታደለ (የህ/ተ/ም/ቤት አባል)

@Leyu_News
@Leyu_News
1.4K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 19:40:43 የመከላከያ ሰራዊት፤ ለሁለት ዓመት ገደማ በታጣቂዎች ስር የቆየውን የአበርገሌ ወረዳ ዋና ከተማ ዳግም ተቆጣጠረ!!

ላለፉት 21 ወራት በህወሓት እና በአገው ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ ታጣቂዎች ይዞታ ስር የቆየችውን የአበርገሌ ወረዳ ዋና ከተማን፤ የመከላከያ ሰራዊት መልሶ ተቆጣጠረ። የመከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስር ወደምትገኘው “ንየር አቑ” ከተማ የገባው፤ ታጣቂዎቹ አካባቢውን በትላንትናው ዕለት ለቅቀው ከወጡ በኋላ እንደሆነ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል አጎራባች የሆነው የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ አበርገሌ እና ጻግብጂ የተባሉት ወረዳዎቹ ከቁጥጥሩ ውጭ ሆነው ቆይተዋል። ጦርነቱ በተጀመረ “በአጭር ጊዜ” ውስጥ በህወሓት ታጣቂዎች እጅ ገብተው የነበሩት ሁለቱ ወረዳዎች፤  ለመጀመሪያ ጊዜ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የገቡት የፌደራል ጦር የትግራይ ክልልን ሲቆጣጠር ነበር። 

ይሁንና የፌደራሉ መንግስት በሰኔ 2013 ዓ.ም ከትግራይ ክልል ሲወጣ፤ ሁለቱ ወረዳዎች ዳግም በህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ለመውደቅ ተገድደዋል። ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር በአማራ ክልል እና አፋር ክልሎች ሲዋጋ የቆየው የመከላከያ ሰራዊት በአማጽያኑ እጅ የነበሩ በርካታ ቦታዎችን ቢያስለቅቅም፤ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ስር ያሉት ሁለት ወረዳዎች ግን በታጣቂዎች ተይዘው ቆይተዋል።

የአማራ ክልል መንግስት በጻግብጂ እና አበርገሌ ወረዳዎች ያለውን ችግር ለመፍታት፤ በአካባቢው ከሚንቀሳቀሱት ታጣቂዎች ጋር የሰላም ንግግር ማካሄድ መጀመሩን ባለፈው የካቲት ወር መጨረሻ ገልጾ ነበር። “ከአገው ሸንጎ” ታጣቂዎች ጋር ተጀምሮ የነበረው የሰላም ንግግር “አለመሳካቱን” ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የገለጹት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ስቡህ ገበያው፤ ሆኖም በመከላከያ ሰራዊት እና የህወሓት ጀነራሎች መካከል የተደረገ ውይይት ውጤት ማምጣቱን አስረድተዋል።

በሁለቱ አካላት መካከል በትላትናው ዕለት የተካሄደው ውይይት ትኩረት ያደረገው “በሰላም ጉዳይ” እና “ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ ስለሚቻልባቸው” መንገዶች እንደነበር የአበርገሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አለሙ ክፍሌ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ይህንን ውይይት ተከትሎም፤ ራሱን “የአገው ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ” በማለት የሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባላት የዚያኑ ዕለት ንየር አቑ ከተማን ለቅቀው መውጣታቸውን አክለዋል። 

“የወረዳው ዋና ከተማ ሙሉ ለሙሉ ነጻ ሆኗል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ትላንት ገብቶ አድሯል። እኛ ዛሬ እዚያው ነው ያለነው። ያለ ምንም ተኩስ፤ የመከላከያ ሰራዊት በሰላም ከተማውን ተቆጣጥሮታል” ሲሉ አቶ አለሙ በዛሬው ዕለት በአካባቢው ያለውን ሁኔታ አስረድተዋል። የመከላከያ ሰራዊት ንየር አቑ ከተማ መግባቱን ተከትሎ፤ “የተወሰኑ” የታጣቂ ቡድኑ አባላት “ተሳስተን ነበር” በማለት እጃቸውን መስጠታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

(ምንጭ፣ Ethiopia Insider)

@Leyu_News
@Leyu_News
1.5K views16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 19:39:02 ራቾ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ራቾ በሚባል አካባቢ የሸኔ ታጣቂዎች በንጹሃን ላይ ከቅዳሜ መጋቢት 16 ጀምሮ ጥቃት በማድረስ ላይ መሆናቸውን ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በጥቃቱ በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል ያሉት ምንጮች፣ ከ100 በላይ ሰዎች መታገታቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
የራቾ አካባቢ በውስጡ አራት ቀበሌዎችን የያዘ ነው ያሉት ምንጮች በሀርቡ ድሬ፣ ሀሙማ ገንዶና ባቡ ድሬ ቀበሌዎች ላይ ጥቃቱ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ ይሁንና ታጣቂዎቹ ከቀበሌው ነዋሪዎች መከላከል ይገጥመናል ብሎ በማሰብ በሆሮ ግንደ በርበሬ ቀበሌ ላይ ጥቃት አለማድረሳቸው ተሰምቷል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
1.3K views16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 12:29:03 በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ምርጫ እንዲካሄድ የክልሉ ፓርቲዎች ጠየቁ

ረቡዕ መጋቢት 20 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ባልተደረገባቸው ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ምርጫ እንዲደረግ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ጥያቄያቸውን ለቦርዱ ያቀረቡት፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በኩል ሲሆን፣ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ምርጫ እንዲደረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ተብቧል፡፡

አዲስ ማለዳ የጋራ ምክር ቤቱ ለቦርዱ ያቀረበውን የጥያቄ ደብዳቤ የተመለከተች ሲሆን፣ በድብዳቤው ላይ እንደተገለጸው በጸጥታ ችግር ያልተካሄደውን ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩን የጋራ ምክር ቤቱ መጋቢት 14/2015 ባካሄደው ስብሰባ መገምገሙ ተጠቁሟል፡፡ በተካሄደው ስብሰባ ገዥውን ፓርቲ ብልጽግናን ጨምሮ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ እንዲካሄድ የተስማሙ ሲሆን፣ በዚሁ መሰረት ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች ቦርዱ ምርጫ እንዳካሂድ ጠይቀዋል፡፡

ምርጫውን ለማካሄድ ፖርቲዎቹ ከዚህ ከኹለት ዓመት በፊት ያቀረቧቸው እጩዎች የሚቀይሩበት አዲል እንዲመቻች፣ ከዚህ በፊት ታግዶ የነበረው የጉምዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያ ንቅናቄ(ጉህዴን) እጪ እንዳቀርብ ቦርዱ እንዲፈቅድ ምክር ቤቱ ጠይቋል፡፡

በክልሉ የሚካሄደው ምርጫ በፓርቲዎች መካከል ጠንካራና ፍትሐዊ ፉክክር እንዲኖር፣ የምርጫ ቅስቀሳ በጀት ለኹሉም ፓርቲዎች እዲመደብም ተጠይቋል፡፡ እንዲሁም በክልሉ በክረም ወቅት ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ስለሚኖር፣ ምርጫው ከግንቦት 30/2015 ወዲህ እንዲያደረግ ቦርዱ ጥያቄ ቀርቦታል፡፡

በ2013 የታተሙ ምርጫ ነክ ሰነዶች በሙሉ እንዲወገዱና የመራጮች ምዝገባ እንደ አዲስ እንዲካሄድ ምክር ቤቱ ጠይቋል፡፡ ቦርዱ የጋራ ምክር ቤቱ አባል ፓርቲዎች የተስማሙበትን ሁኔታ መሰረት በማድረግ፣ ምርጫ የሚያካሂድበትን እቅድ አውጥቶ እንዳሳውቅ ተጠይቋል፡፡

በክልሉ ካሉት ሦስት ዞኖች በኹለቱ ዞኖች ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ያልተካሄደ ሲሆን፣ በክልሉ የተከሰተው የጸጥታ ችግር ለተከታታይ ሦስትና አራት ዓመታት ምርጫ እንዳይካሄድ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል፡፡ አሁን ላይ በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ አንጻራዊ መረጋጋት አሳይቶ ከቤት ንረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ አካባቢያቸው የተመለሱበት ሁኔታ መፈጠሩን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
711 views09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 12:28:45
660 views09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 11:45:51
የመንጃ ፍቃድ ለማውጣት 960 ጊዜ የፅሁፍ ፈተና ከወደቀች በኃላ በ69ኝ ዓመቷ ያለፈችው ሴት የህይወት ታሪክ መነጋገሪያ ሆኗል

በደቡብ ኮርያ ሲንቾን መንደር ሳ-ሶን የተባለች ግለሰብ የመንጃ ፍቃድ ለማውጣት 960 ጊዜ የፅሁፍ ፈተና የወደቀች ሲሆን በመጨረሻም 961ኛ ሙከራ ፈተናውን በ61 ዓመቷ አልፋለች። አስደናቂው የስኬት ታሪኳ ላይ ለመድረስ ለ30 ዓመታት ፈተናውን መውሰዷ ተነግሯል።

ዛሬ ላይ ግለሰቧ 81ኛ ዓመቷ ላይ የምትገኝ ስትሆን ታሪኳ እንደገና ቀርቦ በመላው አለም ያሉ ሰዎችን እያበረታታ ይገኛል። ፈተናውን በ69 አመቷ ስታልፍ የእቅፍ አበባ ስጦታ እንደተበረከተላት ተናግራለች።

@Leyu_News
@Leyu_News
728 views08:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 11:07:13 በትግራይ ክልል የቀድሞው ጊዜያዊ አስተዳደር 17 ሺሕ ሠራተኞች ታስረዋል ተባለ

በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ የተመሰረተው የተጋሩ ኢትዮጵያዊያን ፎረም ለዘላቂ ሠላም፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ በቀድሞው የትግራይ አስተዳደር ሥር ሲያገለግሉ የነበሩ 17 ሺሕ ሰዎች በእስር ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡

በትግራይ ክልል በእስር ላይ ይገኛሉ የተባሉት ዜጎች፣ የፌደራል መንግሥት ሰኔ 21/2013 ከትግራይ ክልል ከወጣ በኋላ ሕወሓት ከጠላት ጋር ተባብራችኋል በሚል ያሰራቸው መሆናቸውን ፎረሙ አስታውሷል፡፡

በክልሉ የሚገኙ እስረኞች የቀድሞው ጊዜያዊ አስተዳደር ሠራተኞች በአስቸኳይ ተፈተው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ የጠየቀው ፎረሙ፣ ከክልሉ ውጪ በተለያዩ አካባቢዎች የታሰሩ የትግራይ ተወላጆች በእስር ላይ የሚቆዩበት የሕግም ይሁን የፖለቲካ ሁኔታ ስለሌለ ለተሟላ የሰላም ትግረበራ ሲባል እንዲፈቱ ተጠይቋል፡፡

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ወደ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ እየተላከ ቢሆንም፣ ሕዝቡ በአግባቡ እርዳታ እያገኘ አለመሆኑን ፎረሙ አረጋገጫለሁ ብሏል። የቀረበውን እርዳታ በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ የፌደራል መንግሥቱ ጣልቃ እንዲገባም ተጠይቋል፡፡

በኢትዮጵያ ሰላምና ዴሞክራሲ ለማስፈን የተሟላ የሕዝብ ተሳትፎ አስፈላጊ በመሆኑ፣ አዲስ በተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ፍትሕና ተጠያቂነትን መሰረት ያደረገ አቃፊና አሳታፊ እንዲሆን ፎረሙ ጠይቋል፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ በክልሉ የአንድ ወገን የበላይነት የተንጸባረቀበት እና አሳታፊ ያልሆነ አስተዳደር ከሆነ ያልተገባ አለመግባባት ሊፈጠር እንደሚችል ፎርሙ ስጋቱን ገለጿል፡፡

በሌላ በኩል የትግራይ ሕዝብ “ከጦርነት በፊት የተበደራችሁትን ገንዘብ ክፈሉ” የሚል ከፍተኛ ጫና እየደረሰበት ነው ተብሏል፡፡ ሕዝቡ ችግር ውስጥ በሚገኝበት ሁኔታ ተጨማሪ ጫና የሚፈጥር የሚፈጥር አካሄድ በአስቸኳይ እንዲቆም ተጠይቋል፡፡ 

@Leyu_News
@Leyu_News
819 views08:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 07:45:01
በሻሸመኔ ለደረሰው ከፍተኛ ጉዳት ድጋፍ ለማሰባሰብ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሄደ

በዉይይቱ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ እና ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ እና ምዕራብ አርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ በመሩት ውይይት በርካታ የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች ተገኝተዋል።

ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በሚገኘው በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ካህናትና ምዕመናን ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ በመሆኑ ለችግረኞች ድጋፍ ለማሰባሰብ ያለመ እንደሆነ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የደረሰውን ጉዳት በፖሮጀክተር እና በምስል የታገዘ የደረሰውን ዘግናኝ ግፍ አብራርተዋል።

ተጎጂዎቹ እስካሁን በሆስፒታል ሆነው ህክምና የሚፈልጉ እና አንዳንዶችም ለቋሚ የአካል ጉዳት የተዳረጉ እና ቤተሰቦቻቸው የተገደሉባቸውና ለከፍተኛ ለችግር የተጋለጡ ስለሆነ ይህን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ገንዘብ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል ሲል የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል ።

በተጨማሪም በቦረና በደረሰው ድርቅ ዜጎች እና እንስሳት በውሃ ጥም ንቃቃት ሲያልቁ ቤተክርስቲያን ግድ ይላታል ያሉት ብፁዕ አቡነ ሄኖክ እንድረስላቸው ሲሉም አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ውድመት ደርሶበት የነበረውን የሰሜን ወሎ እና የዋግኽም አህጉረ ስብከት እና አብያተ ክርስቲያንን ለማቋቋም የሚያስችል ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚያስችል የተቋቋመው ኮሚቴ በአጭር ሪፖርቱ 16 ሚሊዮን ለማሰባሰብ አቅዶ እስካሁን ድረስ 4 ሚሊዮን ብር እንዳሰባሰበ ተገልጿል ሲል የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ዋቢ አድርጎ ተሚማ ዘግቧል።

Via:- ዳጉ ጆርናል

@Leyu_News
@Leyu_News
1.1K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 21:06:15
ድምጻዊያኑን ያስለቀሰው የህጻናት ዝማሬ

ድምጻዊ አቡሽ ዘለቀ እና ድምጻዊ ዳኘው ዋለ በዛሬው ዕለት በደብረ ብርሐን የሚገኙ ተፈናቃዮችን ጎብኝተዋል። ከሕዝብ የተሰበሰበ ልገሳ ከማሰራጨት ባሻገር በ2 የተፈናቃዮች ጣቢያ ተገኝተው ጉብኝት ያድረጉት ድምጻዊያን በህጻናት በተደረገላቸው አቀባበል ልባቸው መነካቱን ገልጸዋል።

ሕጻናቱ በተለይም "
"እናት አባት ቢሞት በአገር ይለቀሳ
አገር የሞተ እንደሁ ወዴት ይደረሳል"
የሚል ስንኝ ያለውን ውብ አገሬ የተሰኘ ዝማሬ ሲያሰሙ ሁለቱም ድምጻዊያን እንባቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ተስተውለዋል።

እነዚህ ህጻናት በማያውቁት ምክንያት ተፈናቅለው በደብረ ብርሐን መጠለያ ጣቢያ ገብተው ስማቸው ተፈናቃይ ሕጻናት ከተባሉ ውለው አድረዋል።

መረጃው የያሬድ ሹመቴ ነው!

@Leyu_News
@Leyu_News
1.6K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ