Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2023-04-02 14:08:56
1.4K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 14:06:33
አትሌት አበጀ አያና የፓሪስ ማራቶንን አሸነፈ

ኢትዮጵያዊው አትሌት አበጀ አያና በዛሬው ዕለት የተካሄደውን የፓሪስ ማራቶን አሸንፏል፡፡አትሌት አበጀ ውድድሩን ያሸነፈው 2 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ14 ሴከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ነው ድል ያደረገው።

ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጉዬ አዶላ 2 ሰዓት 7 ደቂቃ ከ35 ሴከንድ በሆነ ጊዜ ሁለተኛ በመሆን ውድድሩን መጨረሱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እንዲሁም ኬንያዊው አትሌት ጆስፋት ቦይት ሦስተኛ ሆኖ ውድድሩን አጠናቋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
1.4K viewsedited  11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 10:54:27 ሩሲያ የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንትነትን ተረከበች

በሩሲያ ፕሬዝዳንትነት የተበሳጨችው ዩክሬን “ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በጥፊ እንደመምታት ነው” ብላለች ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ከጀመረች ወዲህ የፀጥታው ም/ቤት ፕሬዝዳንት ስትሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ነው

ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የሚያዝያ ወር ፕሬዳንት ስፍራን ተረክባለች።

ዩክሬን ለሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት የወሩ ፐሬዝዳንትነት ስፍራ እንዳይሰጣት ለማድረግ በርካታ ጥረቶችን ብታደርግም ሳይሳካ ቀርቷል ነው የተባለው።

ሩሲያ ኃላፊነቱን መረከቧን ተከትሎ በተመድ የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊይ ናቤንዚያ፤ ሞስኮ በፕሬዝዳንትነት ጊዜወ የጦር መሳሪያ ቁጥጥርን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ክርክሮችን እደምታካሂድ አስታውቀዋል። በተጨማሪም የአንድ ሀገር የበላይነትን ስለሚያስቀረው አዲሱ የዓለም ስርዓት ላይ ውይይቶች እንደሚካሄዱም ገልጸዋል።

የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንትንት በሩሲያ መያዝ ያስደገጣት ዩክሬን በበኩሏ፤ “የወሩ ምርጥ ቀልድ ነው” በማለት አጣጥላለች።

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሜትሪ ኩሌባ፤ “ሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንት መሆን በዓለም የደህንነት ስርዓት ውስጥ የዓለም የፀጥታ እና የደህንነት ስርዓት ውስጥ የሆነ ችግር ያሳያል” ብለዋል።

“ሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዘዳንት መሆን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በጥፊ እንደመምታት ነው” ሲሉም ሁኔታውን ገልጸውታል።

የተባሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት አምስት ቋሚ እና 10 ተለዋዋጭ በድምሩ 15 አባላት ያሉት ሲሆን፤ ሁሉም አባላት የምክር ቤቱን የፕሬዝዳንትነት ስፍራ በየወሩ እየተቀባበሉ ይመራሉ።

ሩሲያ ለመጨረሻ ጊዜ የፀጥታው ምክር ቤት የሆነችው በፈረንጆቹ የካትቲ ወር 2022 ላይ ነበር።
@Leyu_News
@Leyu_News
1.6K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 10:09:11
በአማራ ክልል መራዊና ቋሪት ከተሞች የልዩ ሀይሉን ትጥቅ መፍታት በመቃዎምና ዘመነ ካሴን ፍቱልን በሚል ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.5K views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 09:22:21
ህወሓት ግንባር የቆዩ ታጣቂዎቹን ፖሊስ እንዲሆኑ እያደረገ ነው ተባለ

አርብ መጋቢት 22 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ህወሓት በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በግንባር ሲዋጉ የቆዩ ታጣቂዎችን የፖሊስ መታወቂያ በመስጠት በየከተሞች እየመደበ ነው ተባለ፡፡

ህወሓት በሰላም ስምምነቱ መሰረት ትጥቅ መፍታት ስላለበት ታጣቂዎቹ ትጥቅ እንዳይፈቱ ለማድረግ  በፖሊስነት እየመደባቸው መሆኑን አዲስ ማለዳ ከምንጮች ሰምታለች፡፡

ህወሓት ታጣቂዎቹን በጊዜያዊ መንግሥት መዋቅሩ ውስጥ አስገብቶ ደሞዝ እንዲከፈላቸው ለማድረግ እየሰራ ነው የተባለ ሲሆን፣ ግንባር ላይ ሲዋጉ ከነበሩ ታጣቂዎች መካከል "በፖሊስነት ኮረም ተመድበናል በቅርቡ እንመጣለን" ያሉ መኖራቸውን አዲስ ማለዳ ከአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጣለች፡፡

በሌላ በኩል ሰሞኑን ከአበርገሌ በገዛ ፈቃዳቸው የወጡ የህወሓት ታጣቂዎች ከጻግብጂ ግን ሊወጡ እንዳልቻሉ ተመላክቷል፡፡

በዋግኽምራ ዞን የምትገኘዋ የጻግብጂ ወረዳ ኮረምና አላማጣን ለመቆጣጠር ስትራቴጂክ መሆኗን ተከትሎ ህወሓት ሊወጣ አልቻለም የሚል አስተያየታቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

ህወሓት ከጻግብጂ በተጨማሪ ኮረም ውስጥ ስድስት የገጠር ቀበሌዎችን እያስተዳደረ እንደሚገኝም ተነግሯል፡፡

በእነዚህ ቀበሌዎችም የመሬት ግብር የሚሰበስብ ሲሆን፣ ለህዝብ ከሚመጣው እርዳታ ላይም ቀንሶ የሚወስድ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ 15 ኪሎ ግራም እህል ከሚያገኙ ግለሰቦች 5 ኪሎ ግራም የሚሆነውን እንደሚወስድ ተነግሯል፡፡

ህወሓት የሰላም ስምምነቱን የሚያከበር ከሆነ ህወሓት ከጻግብጂ ወረዳ እንዲሁም ከስድስቱ ቀበሌዎች መውጣት እንደነበረበት ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
1.6K views06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 22:44:36 ልዩ ሀይል…

የሌሎች ክልሎች ልዩ ኃይሎች ትጥቅ ይፈታሉ፤ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ግን ሁኔታዎች ስለማይፈቅዱ ትጥቅ አይፈታም ተብሏል።

ትናንት በተደረገው ስብሰባ የተሃድሶ ኮምሽኑ ኃላፊ ተሾመ ቶጋ በሰጠው መግለጫ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ትጥቅ እንደማይፈታ ገልፆአል። በዋነኛነት ትኩረት የተደረገው ሌሎቹ ላይ ሲሆን የኦሮሚያ "ሁኔታዎች ሲመቻቹ" ነው ተብሏል። "ሁኔታዎች አልተመቻቹም" ብለዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
865 views19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:41:26
የኬንያ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የመግደል ሙከራ እንደተደረገባቸዉ ተናገሩ

የኬንያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ባለፈው ሐሙስ በፀረ-መንግስት ተቃውሞ ወቅት መኪናቸው በሰባት ጥይት መመታቱን በመናገር ክስተቱ በቀጥታ የመግደል ሙከራ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ለመገናኛ ብዙሃን ኦዲንጋ በሰጡት መግለጫ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ኢስትላንድስ ክፍል በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ፖሊስ በመኪናቸው እና በሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ላይ ኢላማ ያደረገ ጥቃት መሰንዘሩን ተናግረዋል፡፡

በፀረ-መንግስት ተቃውሞ ወቅት ፖሊስ ጋዜጠኞችን ኢላማ ማድረጉንም አንስተዋል፡፡ በተጨማሪም በናይሮቢ ከተማ በሚገኘው ሮያል ሚዲያ አገልግሎት ቢሮ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የኬንያ ፖሊስ እቅድ እንዳለዉ በመግለጫዉ ተጠቅሷል፡፡ ኦዲንጋ በተቃውሞው ወቅት በባለሥልጣናት የሚደርሰዉን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ችላ ማለቱን ተችተዋል።

መንግስት የኑሮ ውድነቱን እንዲቀንስ እና የምርጫ ማሻሻያ እንዲያደርግ ጫና ለማሳደር ተቃዋሚዎች በሚያዚያ 3 ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያካሂዱ አስታዉቀዋል፡፡በትላንትናዉ እለት በተካሄደዉ ተቃውሞ ስድስት ጋዜጠኞች የጉዳት ሰለባ ሆነዋል፡፡ ይህም ባለፈው ሳምንት የተቃውሞ ሰልፉ ከተጀመረ ወዲህ የቆሰሉት የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ቁጥር ወደ 22 ከፍ አድርጎታል፡፡

"ዩናይትድ ስቴትስ በጋዜጠኞች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት እንዳሳሰባት እንዲሁም የፕሬስ ነፃነትን እና ደህንነትን መጠበቅ የዲሞክራሲ መሰረት ነው" ሲሉ አምባሳደር ሜግ ዊትማን በዛሬዉ እለት በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.4K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 19:38:58
#LUXURY_BRAND_PERFUMES

CREED AVENTUS

BEST MEN'S PERFUME

ENLIGHTED LUXURY

AMAZING FRAGRANCE

100ML

IMPORTED FROM EUROPE

FREE  DELIVERY

PRICE :- 8300ETB


#LIVING_A_LUXURIOUS_LIFE_IS_A_CHOICE
-------------------------------
     PHONE        +251964593642
                                    +251906495051
                                    +251907495051

TELEGRAM     @AM_CS
                                   @AM_CS1
                                   @AM_CS2
-------------------------------

ተጨማሪ ብራንድ የሆኑ የወንድ እና የሴት ሽቶዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+-XYkLOolhDVkNTc8
https://t.me/+-XYkLOolhDVkNTc8
1.1K views16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 18:25:10 ትራምፕ የፊታችን ማክሰኞ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ በካቴና አይታሰሩም - ጠበቃቸው

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሰኞ በግል አውሮፕላናቸው ወደ ኒውዮርክ በማቅናት እጃቸውን ይሰጣሉ ተብሏል።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.2K views15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-01 16:22:04 በጋሞ ዞን 279 ሺሕ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስልጋቸው ተነገረ

ላለፉት አራት ዓመታት በቂ የሆነ ዝናብ ባላገኙ የጋሞ ዞን አካባቢዎች የሚኖሩ 279 ሺሕ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚስልጋቸው የዞኑ ግብርና ጽ/ቤት ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ፡፡

በዞኑ ካሉ 20 የአስተዳደር መዋቅሮች መካከል በአስሩ ላይ ድርቅ ማጋጠሙን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ቲኮ ትላንታ ለአዲስ ማለዳ ተናግዋል፡፡

በድርቁ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ምግብ ፍለጋ ወደ ሌሎች የዞኑ አካባቢዎች መንቀሳቀሳቸውን የገለጹት ምክትል አስተዳዳሪው፣ በቂ የሆነ ድጋፍ ባለማግኘታቸው ምክንያት ለልመና የተዳረጉ እንዳሉም ተናግረዋል፡፡

የዞኑ ነዋሪዎችም በድርቅ ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ የተሰማ ሲሆን፣ በአርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የአዲስ ማለዳ ምንጮችም ከዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች እንደመጡ የሚናገሩ ሰዎች ለዕለት ጉርስ በመለመን ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

ነዋሪዎች በቂ የምግብ ድጋፍ እንዲያገኙ ዞኑ ለደቡብ ክልል አስተዳደር ማሳወቁን የተናገሩት ቲኮ፣ እስካሁን የተደረጉ ድጋፎች በቂ አለመሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በአራት ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ ነዋሪዎች ከፌደራል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የገንዘብ ድጋፍ መገኘቱ የተነገረ ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የተገኘ ምንም አይነት ድጋፍ አለመኖሩ ተሰምቷል፡፡

በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች በተያዘው መጋቢት ወር ውስጥ ዝናብ መጣል መጀመሩን ምክትል አስተዳዳሪው የተናገሩ ሲሆን፣ በፍጥነት ለምግብነት መድረስ የሚችሉ ሰብሎችን ለማምረት ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል። በዚህም ቦሎቄ እንዲመረት የዘር አቅርቦት በጽ/ቤታቸው በኩል መመቻቸቱን የገለጹት ቲኮ፣ ከሦስት ወራ በኋላ አርሶ አደሩ ምርት ያደርሳል ተብሎ እንሚጠበቅ ተናረዋል፡፡

በድርቅ የተጎዱ ሰዎች ከጉዳቱ እስኪያገግሙ ድረስም በርብርብ ድጋፍ እንዲረግላቸው ተጠይቋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
316 views13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ