Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 37

2023-03-25 19:55:32
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ተቋማዊ እና ህጋዊ ሂደቶችን የጣሱ ናቸዉ - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)  ከተማ እና መሠረተ ልማት ትይዩ ሚኒስቴር  ከተማዊ ፕሮጀክቶች ሲቃኙ በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ሙያዊ ትንተና በዛሬዉ እለት ማካሄዱን አስታውቋል።

በመርሃ ግብሩ መንግሥት እያከናወናቸው ያሉ ፕሮጀክቶች ዋና ዋና ባህሪያት ፣ ፕሮጀክቱን በመፈጸም ሂደት እና ውጤታቸው ላይ የተስተዋሉ ችግሮች በሰፊው መዳሰሳቸዉም ተገልጿል።በዚህም ፕሮጀክቶቹ ከሕጋዊ የግዢ መመሪያ ውጪ በልዩ ትኩረት በተለይ በጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ የሚሠሩ ናቸው ብሏል፡፡

በተጨማሪም የቅደም ተከተል መርህን ያላገናዘቡ ፣ ሀገራዊ ምርትን የማያበረታቱ ሳይሆኑ በከፍተኛ ውጪ የውጭ ምንዛሪ የሚጠቀሙ እንዲሁም ግንባታቸዉ እየተከናወነ ያሉት በውጭ ድርጅቶች በመሆኑ የዕውቀትም ሆነ የቴክኖሎጂ ሽግግር ጥቅም የማያስገኙ መሆናቸው በዉይይቱ መድረኩ መነሳቱን ብስራት ራዲዮ ከፓርቲዉ ካገኘዉ መረጃ ተመልክቷል፡፡

ፕሮጀክቱን በመፈጸም በኩልም የሂደት ግልጽነት መጓደል ፣ የአሳታፊነት ማነስ እና ተቋማዊ እና ህጋዊ ሂደቶችን መጣስ (Undermining institutions and legal frameworks) ተስተውለዋል ብሏል ፓርቲዉ፡፡

ውጤታቸውም ላይ ቢሆን አካባቢያዊ ፣ማህበረሰባዊ እና ኢኮኖሚዉ ላይ ያሳደሩት አሉታዊ ተጽእኖዎቸን በተመለከተ ሰፊ ውይይት ተደርጓል። በመጨረሻም ፓርቲዉ በፕሮጀክቶቹ ላይ ምን ሊሆን ይገባል ተብሎ ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ የመፍትሔ ሐሣቦችን በመውሰድ እና ተጨማሪ ውይይቶች እንደሚቀጥሉ ገልጿል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
1.4K views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 14:27:31
ትራምፕ እኔ ከታሰርኩ ከፍተኛ 'ሞት እና ውድመት' ይከሰታል ሲሉ አስጠነቀቁ

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እ.ኤ.አ. በ2016 የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ የመጨረሻ ደረጃ ላይ ለወሲብ ፊልም ኮከብ ስቶርሚ ዳኒልስ የጸጥታ ገንዘብ እንዲከፍሉ ጠበቃቸውን በማዘዛቸው መከሰሳቸውን ተከትሎ እኔ ከታሰርኩ “ሞት እና ውድመት” ሊኖሩ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

በቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት “ምንም ወንጀል እንዳልተፈፀመ እየታወቀ ምን ዓይነት ሰው እኔን ሊከስ ይችላል ሲሉ ትራምፕ አርብ ዕለት በ Truth Social ልጥፍ ላይ ጽፈዋል።

ምንም እንኳን እርሱን በስም ባይጠቅስም ትራምፕ እኚህ ሰው “አሜሪካን በእውነት የሚጠላ የስነ ልቦና ውድቀት” ብለው የሚጠሩት ሰው “በእንደዚህ ዓይነት የውሸት ክስ ሞት እና ውድመት በአገራችን ላይ ከባድ አደጋ ሊሆን እንደሚችል ያውቃል” ብለዋል ።

@Leyu_News
@Leyu_News
794 views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 13:37:02
ወልቂጤ ዝም ጭር ብላለች።

@Leyu_News
@Leyu_News
941 views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 11:33:03 በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ!

በሀገራችን የሃይማኖት አባቶችን ይቅርና ታላቅን አለማክበር የሚያሳፍር ምናልባትም ከባሕላዊ እሴትነቱ ባለፈ ሃይማኖታዊ ይዘቱ የሚጎላ እሴታችን የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲሀ ግን የሃይማኖት አባቶችን ማዋረድ፣ ድብደባ መፈጸም አልፎም አስነዋሪ በሆነ ኹኔታ ወግሮና በአሰቃቂ ኹኔታ መግደል እየተለመደ መጥቷል። እንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች በጸጥታ አካላት ጭምር ሲፈጸሙ የሚታዩ ሲሆን ድርጊቱ ትናንት በሃይማኖት ተቋማት ላይ የተፈጸመው መንግሥታዊ ጣልቃ ገብነት ብሎም ሃይማኖት ተኮር ጥቃት ከፍ ወዳለ ምዕራፍ መሸጋገሩን የሚያሳይ እና እውቅና ተሰጥቶት ወደለየለት ጭፍጨፋ አደገ ወይ? የሚያስብል ግፍ ሆኖ አግኝተነዋል።

መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ፉሪ አካባቢ ቀሲስ ዓባይ መለሰ የተባሉ ካህን ቅዳሴ ጨርሰው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ እያሉ በድንጋይ ተወግረው ተገድለዋል። ይህንን አስነዋሪ ድርጊት ለማጋለጥ በሰዓቱ የነበረውን ኹኔታ በምስልና ቪዲዮ ለማስረጃ ለመያዝ የሞከሩ ሰዎች ቢኖሩም በአካባቢው የፀጥታ ኃይሎች ሞባይል በመሰብሰብ የቀረጹትን ምስልና የቪዲዮ ማስረጃ እንዳጠፉባቸው ታማኝ ምንጮች ዘግበውታል። ጉዳዩ ቀደም ብሎ ከፍ ባለ ዛቻና ማስፈራሪያ የታጀበ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን በዚህ ኹኔታ ግን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ያደርጉታል የሚል እምነት እንዳልነበራቸው ተናግረዋል፡፡

ፓርቲያችን ድርጊቱን የፈጸሙት አካላት ብቻ ሳይሆን ለሕዝብ መረጃ እንዳይደርስ ያደረጉ አካላት እኩል የድርጊቱ አባሪና ተባባሪ በመሆናቸው ይዘገይ እንደሆነ እንጂ ከሕግ ተጠያቂነት አያመልጡም፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ሥርዓት መር የሆነውና ሃይማኖትን ማዕከል ያደረገው ጥቃትና ጭፍጨፋ በአስቸኳይ እንዲቆም ያገባኛል የሚል አካል ኹሉ እንዲረባረብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በመጨረሻም ፓርቲያችን ድርጊቱን በጽኑ እያወገዘ በአሰቃቂ ኹኔታ ለተገደሉት አባት እርፍተ ነፍስን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ደግሞ መጽናናትን ይመኛል።ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ

እናት ፓርቲ
መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

@Leyu_News
@Leyu_News
1.1K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 10:48:07 አብን የአሜሪካ መንግሥት በሰሜኑ ጦርነት ተሳታፊዎች ላይ ያሳለፈው የወንጀል ፍረጃ  ሕወሃት "ወልቃይትን መልሶ በኃይል እንዲቆጣጠር ዓላማ ያለው ነው" ሲል ትናንት ባወጣው መግለጫ ተቃውሟል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያወጣው ፍረጃ፣ "መሠረተ ቢስ፣ ሃላፊነት የጎደለው እና አድሏዊ" መሆኑን የጠቀሰው አብን፣ የአማራ ክልል ኃይሎች "በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን" አልፈጸሙም በማለት አስተባብሏል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በአማራ ክልል ኃይሎች ላይ ያሳለፈውን ፍረጃ እንደገና እንድትፈትሽና እንዲያስተካክልም አብን ጠይቋል። የአሜሪካ መንግሥት የወልቃይት አማራዎች በሕወሃት አስተዳደር ስር ለዓመታት ለደረሰባቸው በደልና ለማንነት ጥያቄያቸው እውቅና እንዲሰጥም አብን ጨምሮ ጠይቋል።

(Wazema)

@Leyu_News
@Leyu_News
1.1K views07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 10:46:44
የዩክሬን ፖሊስ አንድ ቄስ በአገልግሎት ላይ እያሉ ማሰሩ ክፉኛ አስተቸው

የ65 ዓመቱ ቄስ የአምልኮ ልብሳቸውን ለብሰው የቁርባን ስርዓት በመስፈጸም ላይ ሳሉ በፖሊስ ተጎትተዋል።

በቡኮቪና፣ ቼርኒቭትሲ መንደር የጌታ ዕርገት ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ኢቫን ፕሮትሲዩክ ከሶስት ቀን በፊት ቁርባን ሲያስፈጽሙ ነበር በፖሊሶች የተወሰዱት ።

ቄሱ በፖሊሶች ከመጎተትቸው በፊት ቁርባኑን ለመጨረስ እንዲፈቀድላቸው ለግማሽ ሰዓት ያህል ከፖሊሶቹን ሲለምኑ ነበር።

Via:- RT

@Leyu_News
@Leyu_News
1.0K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 10:45:19
የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ክቡር አክከሬን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በቤተሰቦቻቸው እና በምእመናን ታጅቦ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በክብር ገብቷል።

ከመርሐ ግብሩ እንደተጠቀሰው ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ሥርዓተ ጸሎቱ እየተከናወነ ያድራል ከዚያ ከቅዳሴ በኋላ ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በማቅናት ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈጸም ይሆናል።

Via ኢኦቴቪ

@Leyu_News
@Leyu_News
971 viewsedited  07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 08:21:36
#SPORT : ኢትዮጵያ በጊኒ ተሸነፈች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድናችን
#የአፍሪካ_ዋንጫ ማጣርያ የምድብ ሶስተኛ ጨዋታውን ከጊኒ አቻው ጋር አድርጓል።

ጨዋታውን ያደረገው በሞሮኮ " ሞሀመድ አምስተኛ " ስታዲየም ነው።

በዚህም ጨዋታ ብሔራዊ ቡድናችን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

ውጤቱን ተከትሎ አሁን ያለው የምድቡ ደረጃ ፦

1ኛ. ጊኒ 6 ነጥብ
2ኛ. ግብፅ 6 ነጥብ
3ኛ. ኢትዮጵያ 3 ነጥብ
4ኛ. ማላዊ 3 ነጥብ

ብሔራዊ ቡድናችን ከቀናት በኋላ የምድብ አራተኛ ጨዋታቸውን
#ከጊኒ ጋር ያደርጋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
1.2K viewsedited  05:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 20:43:34 “ወደድንም ጠላንም ጎረቤት ሆነን ነው የምንቀጥለው”:- ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ ዛሬ በሰጡት ወቅታዊ ማብራሪያ ላይ፣ ስለ አማራ እና ትግራይ ክልል ግንኙነት በሰጡት አስተያየት “ወደድንም ጠላንም ጎረቤት ሆነን ነው የምንቀጥለው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ጌታቸው ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን በስጡት ማብራሪያ፣ በኹለቱ ክልሎች መካከል የሚስተዋሉ ችግሮች ከስሜት በጸዳ ሁኔታ በሰላማዊና በሕገ መንግሥታዊ መንገድ መፍታት የሚያዋጣ ነው ብለዋል፡፡

አሁንም የሚታዩት ችግሮች የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል አደብዝዞ ወደ ለየለት “ቁርቁስ” የሚያስገቡ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ ሰላሙን ለማስቀጠል፣ በተለይ “ወንድም በሆነው የአማራ ሕዝብ ዘንድ ይሄ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት አልባት ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ ነው” ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

“ግጭት ያቆምነው ተመልሰውን ወደ ግጭት ለመግባት አይደለም” ያሉት ጌታቸው፣ ያልተቋጩ ነገሮች በቀጣይ ግንኙነት የሚታዩ ስለመሆናቸው ጠቁመዋል፡፡

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ፣ አወዛጋቢ ሆኖ የቀጠለው ከትግራይ ክልል ይወጣሉ የተባሉ ኃይሎች አለመውጣታቸው መሆኑ በተለይም በሕወሓት በኩል በተደገጋሚ ይሰማል፡፡ ጌታቸው በማብራሪያቸው፣ የኤርትራ ሰራዊት አሁንም በትግራይ ክልል ስለመኖሩና ጥቃት እንደሚፈጽም ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ “የአማራ ታጣቂዎች የኛ ነው ብለው በጉልበት በያዟቸው አካባቢዎችላይ ችግር እየፈጠሩ ነው፡፡”  ሲሉ ከሰዋል፡፡

የፌደራል መንግሥት ይሄን የማስቆም ግዴታ አለበት ብለው እንደሚያምኑ የጠቆሙት ጌታቸው፣ የሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል፣ ሕዝቡን ወደ ቦታው መመለስና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ማስጀመር ነው ብለዋል፡፡

“በአማራ በኩል ያሉ ታጣቂዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሰላሙን ወደ ኋላ እንዳይመልሰው ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባ ነው” ሲሉ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በሆኑ ማግስት ዛሬ በሰጡት ማብራያ ጠቁመዋል፡፡

ለችግሩ መነሻ የሆኑ ጉዳዮች ፖለቲካዊ ጉዳዮችን እየፈቱ ከመሄድ አንጻር አሁንም ከፍተቶች መኖራችን ጠቁመዋል፡፡ የጊዜያዊ መንግሥቱ ምስረታ ችግሮችን በሂደት ለመፍታት እድል የሚሰጥ ቢሆንም፣ በሕገ መንግሥቱ መሰረት የኤርትራ ሰራዊትና “የጎረቤት ታጣቂ” ያሏቸውን አካላት የማስወጣት ቀጣይ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

በፕሪቶሪያው የሕወሓትና የፌደራል መንግሥት የሰላም ስምምነት መሰረት፣ በፖለቲካዊ ውይይት ይፈታሉ ተብለው ከታሰቡ ጉዳዮች አንጻር አበረታች ሥራ መሰራቱን ጌታቸው በማብራሪያቸው ላይ ጠቁመዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
471 views17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-24 20:33:19
ጀነራል ተፈራ ማሞ ህክምና እንዲያገኙ ጥሪ ቀረበ!

ወደ ሀገረ እስራኤል ሄደው እንዳይታከሙ የተከለከሉት የብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ የጤንነት ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ። የሀገር ባለ ውለታ የሆኑት ብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ያጋጠማቸው ህመም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰባቸው መምጣቱን ተከትሎ በሀኪሞች ውሳኔ መሰረት በአስቸኳይ ህክምና ያገኙ ዘንድ ሁሉም በከልካዩ ላይ ጫና እንዲያሳድር ጥሪ ቀርቧል።

@Leyu_News
@Leyu_News
534 views17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ