Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 36

2023-03-27 07:49:58 በአዲስ አበባ አሮጌ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በአዲስ ተተክተው ባለመጠናቀቃቸው የኤሌክትሪክ መቆራረጡ ቀጣይነት ሊኖረዉ እንደሚችል ተነገረ

በአዲስ አበባ ከሰሞኑ የአየር ሁኔታ ጋር በተገናኘ በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እየተቋረጠ  ይገኛል፡፡የአገልግሎት መቆራረጡን ተከትሎ ነዋሪዎች ከፍተኛ ጫና በስራ እና በእለት ተእለት ህይወታቸው ላይ እየደረሰ እንደሚገኝ ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡

የሀይል መቆራረጥ ችግር መኖሩን ተገንዝበነዋል የሚሉት የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ሲሆኑ ችግሩ የሚይጋጥመው በሰሞንኛ የአየር ንብረት ሳቢያ የሚፈጠር ነው ሲሉ ገልፀዋል።ለስራ እና ለጥገና አገልግሎት ሳቢያ  ለጥንቃቄ ሲባል ሆን ተብሎ እንደሚጠፋም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ብልሽት ሲያጋጥም ደንበኞች ፈጥነው ሊያስመዘግቡ ይገባል ያሉ ሲሆን ካልተመዘገብ ግን ተቋሙ መረጃ ላይደርሰው ስለሚችል ለበርካታ ቀናት አገልግሎት ሊቋረጥ ስለሚችል ፈጥነው ሊያስመዘግቡ ይገባል ብለዋል።

አሮጌ መስመሮቹን በአዲስ የመተካት ስራ እስኪጠናቀቅ ድረስ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል በመገንዘብ ህብረተሰቡ በትግስት ሊጠብቀን ይገባል ሲሉ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
@Leyu_News
@Leyu_News
1.7K views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 18:32:03
በጫሞ ሐይቅ 8 ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ሰጠመች!

ከአማሮ ልዩ ወረዳ አልፉጮ አቡሎ ወደ አርባምጭ ከተማ ስምንት ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን የደቡብ ክልል ፖሊስ አስታወቀ።የክልሉ ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ፥ ጀልባዋ ስምንት ሰዎች አሳፍራ ትጓዝ እንደነበር አረጋግጠዋል።

የአደጋው መንስኤ ከመጠን በላይ መጫን እና ባልተለመደ ሁኔታ የተከሰተ ማዕበል መሆኑ ተገልጿል።ጀልባዋ ከሥምንቱ ሰዎች በተጨማሪ ሙዝ እና ዕቃ መጫኗን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ደግፌ ደበላ ገልፀዋል።

የሕይወት አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው ለዚህም የተለያዩ ጀልባዎችና ዋናተኞች ፍለጋ ላይ መሆናቸውን ገልጸው በተከናወነው የፍለጋ ሥራ ከጫማዎች እና የተለያዩ አልባሳት ባለፈ የተገኘ ነገር የለም ብለዋል።

የአማሮ ልዩ ወረዳ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ኃላፊ ብሩክ አየለ እንዳሉት የመስጠም አደጋው ትናንት ከሰዓት ነው ያጋጠመው።የሥራ ኃላፊዎቹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ እስካሁን በሕይወት የተገኘ አለመኖሩን ጠቁመው፥ ተሳፋሪዎችን ከዚህ በኋላ በሕይወት የማግኘት ተስፋው መሟጠጡን ተናግረዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.1K views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 17:11:14 ደራ

በኦሮሚያ ክልል ታጣቂዎች ሸዋ ደራ ጉንደ መስቀል ጥቃት መፈጸማቸው ተነገረ!!!


ዛሬ ለሊት ደራ  ራቾ ከፍተኛ ቁጥር  ያላቸው ታጣቂዎች የአማራዎችን ቤት እየመረጡ ሲያቃጥሉ አድረዋል።
እነዚህ ሀይሎች ቤቶችን ሲያቃጥሉ አድረው  አሁን ላይ ወደ ሮብ ገበያ መግባታቸው ታውቋል።
ታጣቂዎቹ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎችን አግተው  መውሰዳቸውን ገልፀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ አሁን በመንግሥት በኩል የተደረገ መከላከል እንደሌለ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
በመሆኑም በአካባቢው ያለው ህዝብ ከደረሰው ጥፋት የባሰ ነገር እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፣መንግስት ተገቢውን ትኩረት መስጠት አለበት ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።(አዩ)

@Leyu_News
@Leyu_News
2.0K views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 16:40:00
#ሰበር_ዜና

ይቅርታ ጠየቁ !!

የቀድሞው  ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለሃይማኖት ወልዱ በትላንትናው ዕለት ቤተክርስቲያን ያደረገችውን ጥሪ በመቀበል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የተደረሰውን ስምምነት በመቀበል በዛሬው ዕለት ወደ እናት ቤተክርስቲያናቸው መመለሳቸውን የሚገልዕ ደብዳቤ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በማቅረብ በይፋ ተመልሰዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማዕከል

@Leyu_News
@Leyu_News
1.9K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 16:37:15
1.7K views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 15:25:04
የተረሳ 150 ሺሕ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ!

በድሬዳዋ ከተማ ከሚያሽከረከረው ባጃጅ ላይ የተረሳ 150 ሺሕ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።

መኮንን ግርማ ኑሮን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ ባጃጅ ላይ ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ሲሆን መጋቢት 15 ቀን 2015 ዓ.ም እንደተለመደው ለስራ በድሬዳዋ ጎዳና ላይ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ ባጃጁን እያሽከረከረ ሳለ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆኑት መሀመድ ዑስማን ከሳቢያን ወደ ኦርቢት ለመሄድ በሱ ባጃጅ ተሳፍረው ወደተባለው ቦታ ማድረሱን ተናግሯል።

ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እና እንድመለከት ተነገረኝ የሚለው ወጣቱ ከተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሬ ስመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ በርካታ ብር ተቀምጦ ማግኘቱን እና ወዲያው ገንዘቡን ይዞ ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳሬክቶሬት በመምጣት 150 ሺሕ ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል።

ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን የድሬዳዋ ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።

ገንዘባቸው የተመለሰላቸው መሐመድ ዑስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የምሽት ባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልፀው ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.3K views12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 13:13:44
የብፁፅ አባቶች ስርአተ ቀብር ተፈፀመ!!

የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ሣልሳይ እና የብፁዕ ዶ/ር አቡነ አረጋዊ ሥርዓተ ቀብር ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከፍተኛ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፣ የሌሎች እምነት ተቋማት መሪዎች፣ ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ተፈፅሟል።

@Leyu_News
@Leyu_News
274 viewsedited  10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 08:48:43 ሰሜን ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈናቀሉ ከ4 ሺሕ 400 በላይ ተፈናቃዮችን ምን እንደማደርጋቸው ግራ ገብቶኛል አለ
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ቤታቸው ፈርሶ ተፈናቅለው ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ የገቡ ከ4 ሺሕ 400 በላይ ተፈናቃዮችን ምን እንደማደርጋቸው ግራ ገብቶኛል አለ።

‹‹ተፈናቃዮቹ ዘመድ ላይ ተጠግተው ለቀናት ቢቆዩም አሁን ግን መኖር ከብዶናል ብለው ወደ እኛ እየመጡ ነው። እኛ ጋር ምግብም ሆነ ሌላ የምንሰጣቸው ነገር የለንም። እናም ምን እንደምናደርጋቸው ግራ ገብቶናል።›› ሲሉ የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አበባው መሰለ ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል።

‹‹ቢፈናቀሉ እንኳን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው ጊዜያዊ መጠለያ ሰጥቶ ሊያግዛቸው የሚገባ። ሕገወጥ ሥራ ካለም በሕግ ተጠያቂ ማድረግ ያለበት እዚያው ነው። ቢያንስ ሴቶችና ህጻናትን ግን ከተማ አስተዳደሩ በሰብዓዊነት ሊያግዝ ይገባ ነበር።›› ሲሉም ተደምጠዋል።

ተፈናቃዮች ወደነበሩበት ሊመለሱ የሚችሉበት መንገድ አለ ወይ? ተብለው የተጠየቁት ኃላፊው ‹‹ማን ያነጋግረናል? የከተማ አስተዳደሩ አቅደው ነው እየሠሩ ያሉት፣ በዚህ ሰዓት ይህን ያህል ሕዝብ ሜዳ ላይ መበተን ትክክል አይደለም›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

‹‹ለኹሉም ጊዜ አለው።›› ያሉት ኃላፊው፣ በዞኑ ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ 77 ሺሕ ገደማ ሕዝብ ባለበት፤ አሁን ደግሞ ከ4 ሺሕ በላይ ከአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈናቀሉ ዜጎች እንደተጨመሩ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ተጨማሪ ጫና ማምጣት ዓላማው ሌላ ነው፣ ሁኔታው ሁሉ የማያምር እየሆነ ነው ብለዋል ኃላፊው።
በዚያ ላይ ተፈናቃዮች ቤታቸው በማንነታቸው ተመርጦ እንደፈረሰ እንደነገሯቸው ጠቅሰው፣ ድርጊቱ አግባብ አይደለም ሲሉ ኮንነዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ከኦሮሚያ ክልል እና ከአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈናቀሉ በድምሩ ከ82 ሺሕ በላይ ዜጎች መኖራቸውን ያስረዱት አበባው፤ ‹‹እየለመንን ነው እየመገብናቸው ያለው፣ ምግብ እንኳን ከፌዴራል መንግሥት አይላክም። ለዓመት ሦስት ጊዜ ያውም ለአንድ ሰው 15 ኪሎ ግራም ስንዴ ብቻ ነው የተላከው።›› ሲሉ ተናግረዋል።

በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል የኦነግ ሸኔ ኃይል እስካልጸዳ ድረስ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደማይቻሉ አበባው ገልጸዋል። ከዚህ በፊት የተወሰኑ ሰዎችን ከክልሉ ጋር በመነጋገር ልከው የነበረ ቢሆንም፣ የተገደሉና ከባድ ሁኔታ ያጋጠማቸው እንደነበሩም አስታውሰዋል።

አክለውም፣ ችግር ውስጥ እያስገባን ያለውም፤ የምንስማማባቸው ጉዳዮች እና እየተፈጸመ ያለው ሐቅ የተለያየ እየሆነ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ከኦሮሚያ ክልል የወለጋ ዞኖች እና ከምዕራብ ሸዋ ዞን ማንነትን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶች ምክንያት በየቀኑ በመቶዎች የሚቀጡሩ ሰዎች ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ እንደሚገቡ ተፈናቃዮች ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ለአብነትም ቻይና ካምፕ በሚባለው መጠለያ ጣቢያ በየቀኑ ያለማቋረጥ ከ150 ሰዎች በላይ ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው እንደሚመጡ ገልጸዋል።

በሳሙኤል ታዴ
@Leyu_News
@Leyu_News
854 views05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 20:37:49 አቶ ስብሐት ነጋ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ መሰረት ነው ለህክምና ከኢትዮጲያ የወጡት።

አቶ ስብሐት ነጋ ወደ ውጭ ሀገር ሄጄ ለመታከም ተከልክያለው ሲሉ  ያቀረቡት ክስ ተከትሎ መከልከላቸው ተገቢ አደለም በማለት ፍርድ ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ነው  ለህክምና ከኢትዮጲያ የወጡት።

አቶ ስብሐት ነጋ በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው ህክምና አድርገው ለመመለስ ወደውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ  ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ገልጸው  ለፍርድ ቤት ክስ መስርተው እንደነበር ይታወሳል።

በህዳር 23 ቀን 2015 ዓ/ም በነበረ ቀጠሮ  ጉዳያቸውን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ የፍታብሔር  ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት   አቶ ስብሐት ወደ ውጪ እንዳይወጡ መከልከሉ ተገቢ አደለም የሚል ውሳኔ ሰጥቶ ነበር

ይህን ውሳኔ  ከሰጠ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ አለመፈጸሙን ተከትሎ አቶ ስብሐት በጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን አማካኝነት ውሳኔው እንዳልተፈፀመላቸው ገለጸው በድጋሚ አቤቱታ አቅርበዋል።

በዚህ አቤቱታ መነሻ ለምን የፍርድ ቤቱ ውሳኔ እንዳልተፈጸመ ከፌደራል ፖሊስ እና ከኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳዮች የሚመለከታቸው ኃላፊዎች  ቀርበው  እንዲያብራሩ ከተደረገ በኋላ የፍርድ ቤቱ ውሳኔው እንዲፈጸም በድጋሚ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

አቶ ስብሐት በዚህ መልኩ ፍርድ ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መነሻ  ከብዙ መጉላላት በኋላ ነው ለህክምና ከኢትዮጲያ ወደ ውጭ የወጡት።

ይሁንና በልዩ ሁኔታ በመንግስት ተመቻችቶላቸው እንዲወጡ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ግን ከዕውነት የራቀ ነው።

ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@Leyu_News
@Leyu_News
1.6K views17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 20:17:30 "የሕገ ወጥ ቡድኑን  የሹመት ይጽደቅልን" ጥያቄን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መቼውንም የማትቀበለው  ጥያቄ ነው" - የመንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

በዛሬ ዕለት የተካሔደውን  በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በሕገ ወጥ መንገድ በተሾሙ  የቀድሞ አባቶች  መካከል የነበረውን ውይይት አስመልክተው መግለጫው የሰጡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  መንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር ገብረ ክርስቶስ  ሲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ከመጋቢት ፮/፳፻፲፭ ዓ/ም ጀምሮ በሕገ ወጥ የተሾሙ ግለሰቦችን አስመልክቶ  በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ለመቀበል   ያከናወነውን  ተግባራት አብራርተዋል።

በዚህም ቅዱስ ሲኖደስ  በቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ከሕገ ወጥ የተሾሙ ግለሰቦች በአምስት  የሥራ ቀናት  ውስጥ ለመንበረ ፓትርያርክ  ጠ/ጽ/ቤት የይቅርታ መመልከቻ እንዲያስገቡ ቅዱስ ሲኖዶስ  ጥሪ ያስተላላፈ ቢሆንም በይቅርታ ደብዳቤ አስገብተው ከተመለሱት ከአንዱ " አባ "   ኃይለ ኢየሱስ ከተባሉት ውጭ ሌሎች ግን   በይቅርታ  ከመመለሰ ይልቅ ለውይይትና  ሕገ ወጥ ድርጊቱም እንዲጸድቅላቸው መጠየቃቸውን  ተገልጿል።

የመምሪያው ኃላፊ ሊቀ ሥዩማን እስክንድር  ገብረ ክርስቶስ ቀጥለው ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ቤት የሰላም ዓደባባይ የንስሓ  ሰገነት በመሆኗ ለፍቅር ረጅም ርቀት በመጓዝ  ግለሰቦቹ  ጋር በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ እንዲሁም በሌሎች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት   አማካኝነት  መወያያቷን  አስታውሰዋል። ከዚህም አልፎ ቤተ ክርስቲያን የሀገር ሰላም የኢትዮጵያውያን የደኅንነት ኑሮ በእጅጉ ስለሚያሳስባት  በብዙ ርቀት ለይቅርታ በሯን ከፍታ ስትጠባበቅ እንደነበረችም አክለው ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመጡት  ሁሉንም እንወክላለን  ያሉት  6  ግለሰቦች  ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ከብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ጋር የተወያዩ ሲሆን በውይይቱ ግን  የተዘረጋው የቤተ ክርስቲያን  የፍቅርና ይቅርታ እጅ በግለሰቦቹ ግን እንደመልካም አልታየም። ከዚህ ይልቅ  ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ከተደረሱ 10 የስምምነት ነጥቦች  መካከል በተራ ቁጥር 6 የሚገኘው ውሳኔ  "በሕገ ወጥ መንገድ  የተሾሙት  "አባቶች"   ወደ ቀደመ አገልግሎታቸው  ይመለሳሉ" የሚል  ቢሆንም ግለሰቦቹ ግን በመርሕ ደረጃ ስምምነቱን እንቀበለዋለን  በአፈጻጸም ደረጃ ግን   ቅዱስ ሲኖዶስ  ሹመታችንን ያጽድቅልን" የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን  የመምሪያው የሓላፊ  ገልጸዋል።

ስለሆነም ይላሉ የመምሪያው ሓላፊ ቤተ ክርስቲያን እስካሁን የሄደችበት የይቅርታ መንገድ  እጅግ የሚያስመሰግን ሲሆን ከዚህ በኋላ  ሕገ ወጦቹን  በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን የሚከተለውን ውሳኔ መወሰኗን አስታውቀዋል።
፩.በየትኛውም መንገድ  የጋራ ውይይት አይኖርም
፪.ለይቅርታ የሚመጡ ከሆነ  በቡድን  ተሰባስቦ  ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ እንዲሆን
፫.የይቅርታ ማመልከቻውን እያንዳንዳቸው  ለመንበረ  ፓትርያርክ ጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ማስገባት  ይኖርባቸዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዚህና በሌሎች መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ  መጋቢት  ፳፩ ቀን  ፳፻፲፭ ዓ/ም  (21/07/2015 )  ምልዓተ ጉባኤ መጠራቱ የሚታወስ ነው።

Via ኢኦቴቪ

@Leyu_News
@Leyu_News
1.5K views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ