Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ አሮጌ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በአዲስ ተተክተው ባለመጠናቀቃቸው የኤሌክትሪክ መቆራረጡ | LEYU NEWS

በአዲስ አበባ አሮጌ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በአዲስ ተተክተው ባለመጠናቀቃቸው የኤሌክትሪክ መቆራረጡ ቀጣይነት ሊኖረዉ እንደሚችል ተነገረ

በአዲስ አበባ ከሰሞኑ የአየር ሁኔታ ጋር በተገናኘ በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እየተቋረጠ  ይገኛል፡፡የአገልግሎት መቆራረጡን ተከትሎ ነዋሪዎች ከፍተኛ ጫና በስራ እና በእለት ተእለት ህይወታቸው ላይ እየደረሰ እንደሚገኝ ለጣቢያችን ገልፀዋል፡፡

የሀይል መቆራረጥ ችግር መኖሩን ተገንዝበነዋል የሚሉት የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ በቀለ ክፍሌ ሲሆኑ ችግሩ የሚይጋጥመው በሰሞንኛ የአየር ንብረት ሳቢያ የሚፈጠር ነው ሲሉ ገልፀዋል።ለስራ እና ለጥገና አገልግሎት ሳቢያ  ለጥንቃቄ ሲባል ሆን ተብሎ እንደሚጠፋም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ብልሽት ሲያጋጥም ደንበኞች ፈጥነው ሊያስመዘግቡ ይገባል ያሉ ሲሆን ካልተመዘገብ ግን ተቋሙ መረጃ ላይደርሰው ስለሚችል ለበርካታ ቀናት አገልግሎት ሊቋረጥ ስለሚችል ፈጥነው ሊያስመዘግቡ ይገባል ብለዋል።

አሮጌ መስመሮቹን በአዲስ የመተካት ስራ እስኪጠናቀቅ ድረስ ችግሩ ሊቀጥል እንደሚችል በመገንዘብ ህብረተሰቡ በትግስት ሊጠብቀን ይገባል ሲሉ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
@Leyu_News
@Leyu_News