Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-21 17:02:17 የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ይቅርታ ጠየቀ!

-መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል

የዒድ ሰላት ለመስገድ ከቤታችሁ ወጥታችሁ ላመለጣችሁ የከተማችንና አካባቢው ሙስሊሞች በሙሉ!!

ዛሬ በነበረው የኢድ ሰላት ፕሮግራም ላይ ለመታደም ጥሪያችንን አክብራችሁ በአንድነት  አምራችሁና ደምቃችሁ ግዙፉ የከተማችን ውበት ሆናችሁ በመዋላችሁ የተሰማንን ታላቅ ደስታ እንገልፃለን።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በድጋሚ እንኳን ለ1444 ዓ.ሂ  የኢድ አልፊጥር በዓል  በሰላም አደረሳችሁ እያልን በዛሬው እለት የተሰገደው የኢድ ሰላት በሰላም፣በደስታ መጠናቀቁ ቢያስደስትም የዒድ ሰላት ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት ከነበረው ሰአት ቀድሞ በመሰገዱ የዒድ ሰላት ላመለጣችሁ የከተማችን ሙስሊሞች ይቅርታ እንጠይቃለን።

በትናንትናው እለት ከፌደራል መጅሊስ ጋር በጋራ በሰጠነው መግለጫ ሸሪአውን በጠበቀ መልኩ በእለቱ ንግግሮች እንደማይኖሩና በማለዳ ሰግደን እንደምንበተን ለህዝባችን ገልፀን ቢሆንም በእለቱ የተገኙት ሚድያዎች በአብዛኛው በሚባል መልኩ ትኩረት ሰጥተው ባለማስተላለፈቸው እና ከሚዲያዎቹ በተጨማሪ ሌሎች አማራጮችን በሰፊው  ባለመጠቀማችን ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት እንደነበሩ ተረድተናል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ሲሰገድበት የነበረውን ሂደትን ለማሻሻል በሚል መልካም እሳቤ በተፈጠረ ክፍተት ሰላት ላመለጣችሁ ሁሉ ታላቅ ይቅርታ እየጠየቅን በቀጣይ የሚስተካከል መሆኑን ህዝባችን እንዲገነዘብ እያልን፣
በበጎና ገንቢ በሆነ መልኩ አስተያየታችሁን ለለገሳችሁን የከተማችን ነዋሪዎች ምስጋና እያቀረብን በዓሉ የሰላም

የደስታ፣የመተዛዘን፣የመረዳዳት እንዲሆን መልካም ምኞታችንን ለመግለፅ እንወዳለን።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.6K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 16:03:35
ዩክሬን በመጨረሻ ኔቶን እንደምትቀላቀል የኔቶ ዋና ጸኃፊ አረጋገጡ!!

ሁሉም የኔቶ አጋሮች ዩክሬን የህብረቱ አባል እንድትሆን ተስማምተዋል፤ አሁን ግን ዋናው ትኩረት ሀገሪቱ በሩሲያ ላይ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው ሲሉ የኔቶ ዋና ፀሃፊ ጄንስ ስቶልተንበርግ ተናግረዋል።

በጀርመን ራምስቴይን የአየር ኃይል ጣቢያ ከሚካሄደው የዩክሬን መከላከያ ቡድን ስብሰባ በፊት ሲናገሩ፣ በዩክሬን ያለው ጦርነት አንዴ ካበቃ ኪየቭ “አዳዲስ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችል መከላከያ” ሊኖራት ይገባል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ዩክሬን የምዕራባውያን ወታደራዊ ጥምረት የሆነውን ኔቶ ለመቀላቀል በተደጋጋሚ ጥያቄ ብታቀርብም፣ ህብረቱ አስቸኳይ መፍትሄ አልሰጣትም።ከሩሲያ ጋር ጦርነት የገጠመችው ዩክሬን ኔቶን ለመቀላቀል ጥረቷን ቀጥላለች። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ያወጀችው ኔቶ ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋቱን እና ይህም ለደህንነቷ እንደሚያሰጋት ከገለጸች በኋላ ነበር።

ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ከጦር መሳሪያ ጀምሮ በርካታ ድጋፍ እያደረጉ ያሉት አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት በዩክሬን ኔቶን መቀላቀል ላይ ቁርጥ ያለ ውሳኔ አላሳለፉም።በዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ስጋት የገባቸው ስዊድን እና ፊንላንድ ኔቶን ለመቀላቀል ጥያቄ አቅርበው፣ ፊንላንድ ወታደራዊ ጥምረቱን ተቀላቅላለች።

ሁለቱ ሀገራት ጥያቄ ያቀረቡት ቀደም ብለው የነበረ ቢሆንም በቱርክ ተቃውሞ ጥያቄያቸው ተጓትቶ ነበር። የቱርክ ፖርላማ መፍቀዱን ተከትሎ ፊንላድ አባል ሆናለች። ነገርግን ቱርክ በስዊድን አሉ ከምትላቸው የኩርድ አማጺያን ጋር በተያያዘ ያቀረበችው ጥያቄ ስላልተመለሰ የስዊድንን የአባልነት ጥያቄ አላጸደቀችውም።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.7K views13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 12:24:24 የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የ72 ሰዓት ተኩስ አቁም አወጁ!

የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከዛሬ ጀምሮ ለ72 ሰዓታት የሚተገበር የተኩስ አቁም ስምምነት አውጀዋል።የተኩስ አቁም ስምምነቱ  የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ቤተሰቦች እንዲገናኙ፣ የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ እና ንፁሀን ዜጎች ከጦርነት ቀጠናው ለቀው እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑ ተጠቅሷል።  

የተዋጊ ኃይሎቹ መሪዎች ለ72 ሰዓት የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረጋቸው ቢገለፅም፣ በተለያዩ ቀጠናዎች በሚገኙ የውጊያ አካባቢዎች የከባድ መሳሪያዎች ድምፅ እየተሰማ ስለመሆኑ ተጠቅሷል።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.8K views09:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 10:42:26
በብፁዓን አባቶች የሚመራ የሰላም ልኡክ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ መቐለ እንደሚጓዝ ተነገረ

በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሥር በትግራይ በሚገኙ አኅጉረ ስብከት መካከል የነበረው ግንኙነት መቋረጡ የሚታወስ ሲሆን በትግራይ ክልል የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል በትግራይ ከልል ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች የግንኙነት ማስቀጠያ ደብዳቤዎች ሲጻፉ መቆየታቸውን ይታወቃል።

በዛሬው እለትም ለ ኢኦተቤ ቲቪ መግለጫ የሰጠው ልኡኩ የደብዳቤው ግንኙነት እንደታሰበው የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ምክንያት ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከብፁዓን አባቶች፣ ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከምዕመናን የተወጣጣ ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አስታውቋል::

የኮሚቴው ዓላማ የሰላም መድረክ ማመቻቸት ፣ የሚያቀራርብ አንድ የሚኾንበትን መንገድ በጋራ ማፈላለግ እንደሆነም በመግለጫው ተገልጿል።

ልኡኩ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ክልል ትግራይ በመጓዝ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓም በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል።

Via ኢኦተቤ ቴቪ / ተሚማ

@Leyu_News
@Leyu_News
4.0K views07:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 08:44:05
የዒድ አልፈጥር በዓል እየተከበረ ነው

የ2015 ዓ.ም የዒድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው።

የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የመተዛዘን እና የመረዳዳት እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል።

በታላቁ የረመዷን ወር መጨረሻ የሚከበረውን የዒድ አልፈጥር በዓልን በሰላምና በመተሳሰብ እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ማሳለፍ እንደሚገባም ጥሪ አቅርቧል።
@Leyu_News
@Leyu_News
4.0K views05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:44:19 #AddisAbaba

ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።

1444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የኢድ ሶላት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ይፋ አድርጓል።

አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መንገዶች የሚዘጉ መሆኑን በማወቅ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ ብሏል።

የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤

- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ፤

- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤

- ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤

- ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

- ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤

- ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀኛ፤

- ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤

- ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት ፤

- ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ፤

- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ  ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ ፤

- ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ እንዲሁም ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ አካባቢ #ይለፍ_ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.4K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:42:59
በስርቆት የተነሳ በምስራቅ ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ኃይል ተቋረጠ!

ከአዋሽ ወደ ድሬዳዋ በተዘረጋው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ ሁርሶ አካባቢ በተፈፀመ ስርቆት የምስራቅ ኢትዮጵያ ትልልቅ ከተሞችና አካባቢያቸው ሙሉ በሙሉ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

በተፈፀመው ስርቆት በድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ጅግጅጋና ሌሎች የምስራቅ ኢትዮጵያ ከተሞችን ጨምሮ ወደ ጅቡቲ ኤክስፖርት የሚደረግበት መስመር ኃይል ተቋርጧል።

የተቋረጠውን መስመር ለመጠገን የቴክኒክ ባለሙያዎች ቡድን ከቆቃ በሌላ አማራጭ ኃይል ለመስጠት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመላክተዋል::የኃይል መቋረጡ የረመዳን ፆም ፍቺ ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር በምስራቅና በማዕከላዊ ሪጅን የጥገና ባለሙያዎች በቆቃና በሁርሶ አካባቢ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል።

[Walta]

@Leyu_News
@Leyu_News
2.3K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:41:54 መፍትሔ ስራይ ወዓይነ ጥላ(የባህል ህክምና)

የምንሰራው ጥበብ
============

1.ለሀብት

2.ለገበያ ብዙ ደንበኛ እንዲኖረን

3.ለመስተፋቅር

4.ለማንኛውም በሽታ

5.ለዐይነ ጥላ ማክሸፍያ

6. ለሰላቢ በሌላ አማርኛ ነገሮችን ለመሰወር

7.ለግርማ ሞገስ

8.ለትምህርት ዘኢያገድፍ

9.ለዐቃቤ ርዕስ ለመከላከያ

10.ሰው እንዲወደን ማድረግያ

11.ብልት ማሳደጊያ ዕፀ አብይ

12.ለስንፈተ ወሲብ

13.ለዐደበተ ርቱዕ ጥሩ ተናጋሪ እንድንሆን

14.ለቁመት መጨመርያ ዕፀ (ኤግኤል)

15.በግለ ወሲብ ለምትሰቃዩ ወይም በሴጋ

16.ለመልክ ውበት እንዲኖረን ማድረጊያ

17. ስራ እንድንቀጠር ማድረግያ

18.ፈተና አሪፍ ውጤት እንድናመጣ ማድረግያ

19.ለሴቶች ትልቅ ዳሌ እንዲኖረን ማድረግያ በዕፀዋት ብቻ

20.ፀጉር እንዲረዝም ማድረጊያ

21.ለውፍረት

22.ለቅጥነት

23.ለስልጣን መጨመርያ

24.ለጥላ ወጊ

25.ለህዝብ ፍቅር

26.ብር እንዳይባክን ማድረግያ

27.የሴት ድንግልና መመለሻ

28.ለቁማር (ለዕድል)

29.ደፋር ለመሆን

30. ህልም እንፈታለን

31. ትዳር ላይ ማትስማሙ እድትስማሙ ሚያደርግ

32.ለመካን

33.ዝናብ ለማዝነብ

34.ቅጠልን ወደ ብር ለመቀየር

35.መንፈሶችን ለማዘዝ

36.የሰዎችን መረጃ መሰብሰቢያ አስማት የግል ጉዳያቸው ጭምር

37. ማንኛውም የፍርድ ቤትም ሆነ የትኛውንም ክርክር ለማሸነፍ

38.ሳይወዱ በግድ በማንኛውም ነገር እንዲስማሙ ማድረግያ

39.የምትወልዱትን ልጅ ለመወሰን ወንድ ከፈለጋችሁ ወንድ ሴት ከፈለጋችሁ ሴት

40.የሞተ ዘመዳችሁን ጠርቶ ለማግኘት በረቀቀ መንፈሳዊ አሰራር

41.ማንኛውም መተት የተደረጉበት አጋንንት ለያዘው መፍትሄ አለን

42.ስለ ወደ ፊት እጣ ፋንታ ማወቅ ለምትፈልጉ

43.ለማንኛውም ቋንቋ ለማወቅ

44.እቁብ ዲደርሰን ማድረጊያ

45.ከሀብታሙ ወደ ድሀው የሀብት ዝውውር ማድረግ

46.ትዳሩ ለፈረሰ ወደ ቀድሞ ትዳሩ መመለሻ

እያንዳዱ ችግር እኛጋ መፍትሄ አለ


0918487073 ወይም 0920253444  ይደውሉልን
https://t.me/+k6toMAyjGuwwYWE0
https://t.me/+k6toMAyjGuwwYWE0

(ከየትኛውም እምነት በማይጋጭ መልኩ ነው
---------------------------------------
ምንሰራው በሰለሞን ጥበብ ብቻ )
---------------------------------------
2.0K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:41:52
1.7K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 19:26:31
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ደጋሎ ከአገሪቱ ጦር ሠራዊት ዋና አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን ጋር ለድርድር አልቀመጥም ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

ግጭቱን የጀመሩት ጀኔራል ቡርሃን ናቸው ያሉት ጀኔራል ደጋሎ፣ ወደፊትም ከባላንጣቸው ጋር ድርድር እንደማይኖር መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የሱዳን ጦር ሠራዊትም፣ ከፈጥኖ ደራሽ ሠራዊቱ ጋር የሚደረግን ድርድር ውድቅ አድርጓል። ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ጥሪ ብናደርግም የጦር ሠራዊቱ አዛዦች ግን ተኩስ አቁም አይፈልጉም ያሉት ጀኔራል ደጋሎ፣ ነገ ለሚከበረው ኢድ አልፈጥር በዓል ተኩስ አቁም ቢደረግ ተቃውሞ የለንም ማለታቸው ተገልጧል። ጀኔራል ደጋሎ ሠራዊታቸው ከሩሲያው የግል ወታደራዊ ኩባንያ "ዋግነር" ድጋፍ ያገኛል መባሉን አስተባብለዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.0K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ