Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 14

2023-04-18 19:41:53
ለቅርጫ ከታረደ በሬ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ተገኘ!

በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በምትባል ቀበሌ በጋራ ሆነው ለበዓል የቅርጫ በሬ ያረዱት ሰዎች ከበሬው ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ አግኝተዋል።በሬውን በ40 ሺሕ ብር የገዙት ተቃራጮቹ ከበሬው ሆድ ውስጥ ያገኙትን ወርቅ በ53 ሺሕ ብር በመሸጥ የበሬውን ሥጋ በነፃ በልተው 13 ሺሕ ብር ማትረፍ መቻላቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ከበሬው ሆድ ውስጥ እንዴት ወርቅ ተገኘ? ሳይንሱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሰጡት በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የአሰላ የእንስሳት ጤና ማዕከል የላቦራቶሪ ባለሙያ ዶ/ር አብዲሳ ለማ በበረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ጥቃቅን ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች እየተመገቡ በጊዜ ሂደት ማዕድናቱ በሐሞት ውስጥ እየተጣሩ ወደ ወርቅነት (በተለምዶ ‘የሐሞት ወርቅ’ ወደሚባለው) እንደሚቀየሩ ተናግረዋል፡፡ንጥረ ነገሩ በከብቶቹ ሆድ ውስጥ እየቆየ ሲሄድ የሐሞት ፍሳሽን ስለሚመጥጥ ከብቶቹ እንዳይደልቡ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.6K views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 16:05:31
የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጡ ሰብአዊ መብት የሚጥስ ነው ሲል አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በተመረጡ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የጣለዉን ማዕቀብ እንዲያነሳም ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠይቋል።አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት እገዳዉን ከጣለ 3ኛ ወሩን ይዟል።እገዳዉ ሰዎች መረጃ እንዳያገኙ መገደብን ጨምሮ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀምና ያለመጠቀም የሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነዉ ብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዉሞን በሰላማዊ ሰልፍ የመግለፅ መብትን እንዲያከብርና የታሰሩ የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን እንዲፈታ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ትናንት ማምሻ ባወጣዉ መገለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ባለፈዉ ሳምንት አማራ ክልል በተፈጠረዉ ሁከት ምክንያት ያሰሯቸዉን 7 የመገናኛ ዘዴ ባልደረቦች ባስቸኳይ እንዲፈቱ፣ ከእስረኞቹ ባንዷ ላይ ተፈፀመ የተባለዉን አካላዊ ጥቃት እንዲያጣሩ ጠይቋል።

መግለጫዉ እንዳለዉ ባለስልጣናቱ «ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትንና ሁሉም ወገን በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብቱን ማስከበር አለባቸዉ።»ባለፈዉ ሳምንት በአማራ ክልል የመብት ጥሰትና ሁከት መቀስቀሱ እንዳሳሰበዉ የመብት ተሟጋቹ ድርጅት አስታዉቋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጥ መደረጉ፣ የሰብአዊ ርዳታ አቀባይ ድርጅት ሰራተኞችን ጨምሮ ሰዎች መገደላቸዉ፣ አዲስ አበባ ዉስጥ ሰዎች በጅምላ መታሰራቸዉንም ድርጅቱ «አሳሳቢ» ብሎታል።የመንግስት ኃይላትም ሆኑ ሌሎች ታጣቂዎች «የሰብአዊ ርዳታ ሰራተኞችን ያለማጥቃት ኃላፊነት አለባቸዉ።» ይላል መግለጫዉ።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.3K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 15:26:19 በሱዳን ኦምዱርማን ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ

በጦርነቱ በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መድረሱ ተገልጿል

ከተቀሰቀሰ አራተኛ ቀኑን በያዘዉ የሱዳን የከተማ ዉስጥ ጦርነት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና የአገሪቱ ጦር ዉግያ ዉስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ በርካታ ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ በሆነችዉ ሱዳን ኢትዮጵያዊንም ህይወታቸዉ እንዳለፈ ተሰምቷል።

በሱዳን 12 ዓመታትን የቆየዉና አስተያየቱን ለብስራት ራዲዮ የሰጠው የጤና ባለሙያ ወንድወሰን ጌትነት፤ ከትናንት በስቲያ 11 ሰዓት ከ30 አካባቢ ኦምዱርማን በተሰኘዉ አካባቢ በጦርነቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን በጦር ጄት ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን ተናግሯል። እስካሁን ከ10 በላይ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ ሞተዋል ያለም ሲሆን፤ በትናትናዉ ዕለት በካርቱም ( ጅሬፍ ) በደረሰ ሌላ ጥቃት፤ ባለትዳሮች ሕይወታቸውን ሲያጡ የሦሥት ዓመት ሕጻን ልጃቸዉ ከጥቃቱ መትረፉን ገልጿል።

በተጨማሪም በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይም ጥቃት መድረሱን የገለጸው ወንድወሰን፤ የትኞቹ ታጣቂዎች እንደፈጸሙት ባያረጋግጥም የኤምባሲዉን ቅጥር ግቢ ጥሰዉ በመግባት በግቢዉ በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ባለቤት በሆነበት የመጠለያ ማዕከል ዉስጥ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ አጸያፊ ተግባራት ጭምር መፈጸማቸዉን ተናግሯል።

የኤምባሲዉ ጥበቃዎች በጦርነቱ ወቅት ከግዳጅ ቦታቸዉ በመነሳታቸዉ የተባለዉ ጥቃት መድረሱንና፤ ታጣቂዎቹ ገንዘብን ጨምሮ የተለያዩ ዘረፋዎችን መፈጸማቸዉንም ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሱዳን ልዩ ተወካይ ባወጣው መረጃ፤ በሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት እስከ አሁን በትንሹ 200 ሰዎች መሞታቸው የገለጸ ሲሆን፤ 1 ሺሕ 8 መቶ ያህል ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸዉን አስታውቋል፡፡

አዲስ ማለዳ

@Leyu_News
@Leyu_News
3.2K views12:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 15:25:50
2.8K views12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 12:20:45 የፌዴራል ፖሊስ ልብስ በመልበስ ንብረት የዘረፉ ተከሳሾች በጽኑ እስራት ተቀጡ

ተከሳሾቹ÷ 1ኛ አሸብር ተስፋዬ፣ 2ኛ  አብዲ ሰይድ (ኢ/ር) እና 3ኛ ሰለሞን አየለ መሆናቸው የፍትሕ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ተከሳሾቹ ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ሰለፊያ መስጂድ አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ልብስ በመልበስና የጦር መሳሪያ በመያዝ የግል ተበዳይ ሳሊሞ ጀማል ረዳን ግቢ የውጭ በር በማንኳኳት እና ሕጋዊ ሰዎች ነን፣ ሕጋዊ ወረቀት ይዘናል፣ ለፍተሻ ነው የመጣነው በማለት ወረቀቱን ያሳያሉ፡፡

የግል ተበዳይም ይህንኑ አምነው በሩን ሲከፍቱ ተከታትለው በመግባትና በሽጉጥ በማስፈራራት÷ 300 ሺህ 590 ብር፣ ግምቱ 80 ሺህ ብር የሆነ አንድ ሩሲያ ሰራሽ ማካሮቭ ሽጉጥ ከ8 ጥይቶች ጋር እንዲሁም 15 ሺህ ብር የሚያወጣ አንድ ሳምሰንግ ጋላክሲ ሞባይል ይዘው መሰወራቸውን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

በአጠቃላይ 395 ሺህ 590 ብር ዋጋ ያለው ንብረት ዘርፈው በመሰወር በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈጸሙት ከባድ የውንብድና ወንጀል በዐቃቤ ሕግ ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ 1ኛ ሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ሚያዝያ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ባስቻለው ችሎት በ3ቱም ተከሳሾች ላይ በደረጃ 8 እርከን 34 ስር መነሻ ቅጣት ተይዞ÷ በ1ኛ እና በ2ኛ ተከሳሽ ላይ 1 የቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው እርከን 33 ስር በማሳረፍ እያንዳንዳቸው በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡

በ3ኛ ተከሳሽ ላይ ደግሞ 2 የቅጣት ማቅለያ ተይዞለት እርከን 32 ስር በማሳረፍ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
3.3K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 10:29:40
በሱዳን የአሜሪካ ኤምባሲ ተሽከርካሪ በጥይት ተደበደበ።

በሱዳን ፣ ካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ብረት ለበስ ተሽከርካሪው " ሆን ተብሎ " በጥይት መደብደቡን አስታወቀ።

ድርጊቱን የፈፀመው ሄሜቲ የሚመሩት RSF ቡድን መሆኑን ኤምባሲው ለአል አረቢያ ገልጿል።

ኤምባሲው ተሽከርካሪው በ100 ጥይት መደብደቡን ገልጾ ድብደባው ያደረሰው ምንም ጉዳት የለም ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ የአሜሪካ መንግሥት ጦርነት ውስጥ ካለችው ሱዳን ዜጎቹን የማስወጣት እቅድ እንደሌለው ዋይትሃውስ አሳውቋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.4K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 08:29:51 "ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም" በሚል ምክንያት ያኮረፈዉ ወጣት እራሱን አጠፋ

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ደቡብ አሪ ወረዳ ለበዓል ልብስ አልተገዛልኝም በሚል ከቤተሰቦቹ ተጨቃጭቆ መግባባት ያልቻለዉ ወጣት በገመድ እራሱን ሰቅሎ ሕይወቱን ማጥፋቱ የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ።

በደቡብ አሪ ወረዳ ባላመር ቀበሌ ነዋሪ የሆነዉ ወጣቱ ለ2015 የትንሳኤ በዓል ልብስ እንዲገዛለት ለወላጆቹ ጥያቄ ማቅረቡ ተከትሎ፤ ወላጆቹ ቀደም ሲል የሚለብሳቸዉን ልቦሶች አጽድቶ በመልበስ የዘንድሮዉን በዓል አክብሮ እንዲዉልና በሱ ጥያቂነት ሳይሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ቤተሰብ አልባሳት ይገዛልሀል የሚል ተስፋ አስቆራጭ ምላሽ ይሰጠዋል።

ወጣቱ በወላጆቹ እምቢታ ተናዶ እራሱን እንደሚያጠፋ ዝቶ ከቤተሰቦቹ ጋር ከስምምነት ሳይደርስ መለያየቱን ከፖሊስ በደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

ወጣቱ እራሱን ለማጥፋት ቢዝትም ቤተሰብ እንዲህ አይነቱ እኩይ ተግባር ሊፈፅም ይችላል የሚል ጥርጣሬ እንዳልነበረው ተገልጿል። ነገር ግን ሚያዝያ 08 ቀን 2015 ከቀኑ 12:00 ሰዓት ላይ ወጣቱ እራሱን በገመድ ሰቅሎ በድን ገላዉ ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ እንደተገኘና የወጣቱ አድራጎት ቤተሰቡን በእጅጉ ያስደነገጠና ያሳዘነ ሆኖ ማለፉን ነዉ ፖሊስ ያስታወቀዉ።

ኹለት ወራትን በፆም በፀሎት የከረሙት የሟች ቤተሰቦች የፋሲካን በዓል ለማክበር ያልታደሉ ሆነዉ ድንኳን ቀስተዉ የልጃቸዉ ሀዘን ለመቀመጥ ተገደዋል።

ወላጆች ልጆቻቸዉ ለሚያቀርቡላቸዉ ጥያቄዎች በተግባር ምላሽ መስጠት የማይችሉ ከሆነ እንዲህ አይነቱ ዉጤት በማያስከትል መልኩ በበጀት እጥረት ምክንያት የአቅም ዉስንነት ይሁን ሌሎችንም ምክንያቶች በመጥቀስ በፍቅር ልጆችን የማሳመን ሥራ መስራት እንጂ፤ ከልጆች ጋር እልህ ተጋብቶ እነሱን በኃይል በመጫን አይደረግልህም የሚል አቋም መያዝ ስህተት መሆኑ ማመን እንደሚያስፈልግም የደቡብ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል።

@Leyu_News
@Leyu_News
463 views05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 08:29:14
469 views05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 07:50:37
በሱዳን…!

"…በሱዳን የፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ወዳጅ እንደሆኑ የሚነገርላቸው የሱዳን ልዩ ኃይል ፈጥኖ ደራሽ ጦር መሪ የጄነራል ሄሜንቲ የሚመራው ቡድን ዋነኛውን የሱዳን ፕሮፓጋንዳ ማሽን የሆነውንና በእምዱሩማን የሚገኘውን የሱዳን ብሮድካድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሬዲዮና ቴሌቪዥን ማሰራጫው ሕንፃ በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ተሰምቷል።

በተያያዘ ዜና ሄማቲ “ማርከን የለቀቅናቸው የግብፅ አየር ሀይሎች አሁን እየደበደቡን ነው። 31 ጊዜም አየሮቹ የተነሱት ከግብፅ ነው። ሂሳብ እናወራርዳለን። ረመዳን ነው እያሉ እያለቀሱ ስንቸገር ነበር የለቀቅናቸው። ነገ ግን ብንማርካቸው አንለቃቸውም። አሁን እየተደራጀን ነው። እየተከላከልን እንጅ የምንጠራበትን የጃንጃዊ ጥቃታችንን አልጀመርንም። ቡረሀን ደውሎ ውጊያ እናቁምና አብይ አህመድና መሀመድ ቢን ዛይድ ያደራድሩን ብሎ ለፀሀፊየ ነግሯታል። እጅህ ላይ የፍትህ ገመድ ሳላጠልቅ አልደራደርም ብየዋለሁ። ግብፅ ግን እድሉን ተጠቅማ የሱዳንን ተቋሞች  በአየር ጥቃት እያወደመች ነው።” ሲል ተናግረዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
822 views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 22:36:38 #Update

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገባችሁና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት የተሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ ተማሪዎች በተከታዩ ሊንክ አማካይነት የማመልከቻ ፎርሙን መሙላት ትችላላችሁ፦

http://survey.ethernet.edu.et/index.php/518562?lang=en

የማመልከቻ ፎርሙን መሙላት የሚቻለው ከዛሬ ሚያዝያ 09 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

በማመልከቻ ፎርሙ ልትሞሏቸው የሚገቡ፦

➧ የ12ኛ ክፍል ውጤት ኮፒ፣
➧ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኮፒ፣
➧ ግለ ታሪክ (CV) ኮፒ፣
➧ የልደት የምስክር ወረቀት ኮፒ እና
➧ ሌሎች በፎርሙ የተጠቀሱ መረጃዎች።

መረጃዎቹ ተጣርተው ለፈተና የሚቀረቡ ተማሪዎችን ዝርዝር በቀጣይ እንደሚያሳውቅ የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

@Leyu_News
@Leyu_News
2.3K views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ