Get Mystery Box with random crypto!

LEYU NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS L
የቴሌግራም ቻናል አርማ leyu_news — LEYU NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @leyu_news
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 527
የሰርጥ መግለጫ

#ልዩ_መረጃ  |  #ቀዳሚ_ምርጫዎ
➠ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ
➠ወቅታዊ መረጃዎች
➠ልዩ ልዩ ዘገባዎች
➠ የስፓርት እና መዝናኛ ዜናዎች
➠ጠቃሚ ጥቆማዎች ይደርሶታል።
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።
         PROMOTION
➥   
🎬  "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
News & Media Channel®

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-04-19 16:14:46
በጥንታዊው የሶደሬ ፈለገ ሰላም መድኃኔዓለም ገዳም ላይ የታጠቁ ኃይሎች የቦንብ ጥቃት እና እገታ ፈፀሙ

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ከአዳማ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘውና በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፖትርያሪክ የተመሠረተው የሶደሬ ፈለገ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ትናንት ከምሽቱ 3:30- 4:00 ሰዓት ከ50 በላይ የሚሆኑ የታጠቁ ኃይሎች ቤተክርስቲያኑን ሰብረው በመግባት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፡፡

የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የደረሰውን ጉዳት ለማጣራት ልዑካንን የላከ ሲሆን የደረሰው ጉዳት ተመልክተዋል ከልብ ማዘናቸውን በመግለጽ የአካባቢውን ምዕመናን በቃሉ አጽናንተው ተመልሰዋል፡፡

በሩ ጠንካራ በመሆኑ የታጠቁ ኃይሎች ቦንብ በማፈንዳት ሰብረው ለመግባት የቻሉ ሲሆን በቤተክርስቲያኑ ንዋየ ቅድሳት ላይ ከፍተኛ የቃጠሎ ጉዳት ደርሷል ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የቤተክርስቲያኑን አስተዳዳሪ ቤት ሰብሮ በመግባት በወቅቱ አስተዳዳሪው ባይኖሩም በቤት እቃዎች ላይ ጉዳት አድርሰዋል ፡፡ በካህናት ላይ ከፍተኛ ማዋከብ የተፈጸመ ሲሆን ይኸው የታጠቀ ኃይል የደብሩን ገንዘብ ያዥ የሆኑትን አቶ ተስፋዬን አፍነው መውሰዳቸውንና እስካሁን ሰዓትም የታገተው አቶ ተስፋ እንዳልተለቀቁ ተገልጿል ፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
3.4K views13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 16:14:20
3.0K views13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 12:12:39 መረጃ..!

ወልድያ ከተማ የኢንተርኔት አገልግሎት ከተቋረጠ 2ኛ ቀኑን ይዟል። በተመሳሳ ጎንደር ከተማ የሞባይል ኢንተርኔት ከተቋረጠ 15 ቀን አልፎታል።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.5K views09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:26:17 አንዱዓለም አራጌ እና ኢዜማ ተለያዩ

ለ ኢዜማ የአዲስ አበባ ምርጫ ክልል 12/13 ሊቀመንበር
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- ከአባልነት መልቀቅን ስለማሳወቅ፦

ክቡርነትዎ እንደሚገነዘቡት፣ በኢትዮጵያ ረጅም የህላዊ ዘመን ውስጥ በፓለቲካ ሰማያችን ላይ የደቀደቀውን የሚዳሰስ
የአገዛዝ ጨለማ ለመግፈፍ የማያልቁ የሚመስሉ ረጃጅም የመከራ ሌሊቶችን ብናሳልፍም፣ ይልቁንም ጨለማው በርትቶ
የነፃነት ጀምበርም ከአድማሳችን እጅግ ርቃ በጭቆና ጥቀርሻ መቀበሯ ጥልቅ ህመም ቢፈጥርብን፤ ለሀገራችን የንጋት ኮኮብ ሆኖ፣ ሕዝባችንንም ከአገዛዝ ቀምበር አላቆ በፍቅር፤ በፍትህና በወንድማማችነት ኮረብታዎች ላይ ግዘፍ ነስታ የምትቆም፣ ያለፉትንም የሃሩር ዘመናት የምታስረሳ ኢትዮጵያ እንድትጠባ ከልብ በመሻት ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)ን መመስረታችን ይታወቃል።

እኔም ኢዜማን ከመጠንሰስ እስከ መመሥረት፣ ከምሥረታ በኋላም
ወረዳችንን በአባልነት ፓርቲያችንን በአመራርነት እስከማገልገል የዘለቀ አቅም የፈቀደውን እንቅስቃሴ ማድረጌም ይታወሳል።
የቆዩ ስህተቶችን በፓርቲያችን ውስጥ ላለመድገሞ እንዲሁም የህልሞቻችን ሁሉ በኩር የሆነውን ሰብዓዊ ልእልና የነገሠባት
ኢትዮጵያን በእርግጠኝነት እውን ለማድረግ በሰከነና በተጠና መንገድ ለመራመድ ከፍ ያለ ጥረት ስናደርግ መቆየታችን
ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በአጋዛዝ ውስጥ ተወልዶ በአገዛዝ መዳፍ ውስጥ እንደ ሸበተ ትውልድ እፍኛችንን የሞላው ጉም ነው
ወይንስ የሚጨበጥ ተስፋ የሚለውን ጉዳይ ለመገምገም ፈፅሞ በዚያ መጠን መቸገር ሳይገባን አላስፈላጊ የህልም ሩጫ
የሚመሰሉ የሃሳብ ልፊያዎችን ለማድረግ ተገደን ቆይተናል፡፡
ሁኔታዎችን በውይይትና በሀሳብ ፍጭት ለመፍታት መሥራቱ የሚከበርና እንደ ፖለቲካ ባህልም ልናዳብረው የሚገባ መሆኑ
እሙን ነው፡፡ይሁን እንጂ ምንም እንኳን በጭንቅም ቢሆን ዛሬ ላይ ቆመን በምልሰት የክርክሮቻችን መቋጫና ውጤቱም ምን
እንደሆነ እያየን ቢሆንም፣ በወቅቱ አንኳር በሚሰኙ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በድምፅ ለመሸናናፍ ያደርግናቸው እልህ አስጨራሽ
ፍልሚያዎች የፓርቲው አዎንታዊ መገለጫዎች ናቸው ብዬ እወስዳለሁ፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሁሉ መድህን
ለመሆን ከሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በተገኙ አባላት የተመሰረተ ፓርቲ ኢትዮጵያ በየትኛውም የታሪክ ድርሳን ላይ
ከሰፈረው መከራዋ ሁሉ የከፋውን በምታስተናግድበት በዚህ ዘመን፣ የክብር ፈርጦቿ ሲረግፉና ፀንታ የቆመችባቸው አምዶች
በአገዛዝ መዶሻ ሲፈረካከሱ፤ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን ተግባራዊ በማድረግ፤ ታግሎ ሕዝቡን በማታገል ከደመና
በላይ አንገታቸውንና ልባቸውን አደንድነው፣ በፈርዖን ሰረገላ ላይ ተዘልለው ፣ ሕዝቡን ወደ ቀይ ባህር ዳርቻ በማሳደድ
ሀቅላቸውን የሳቱ ገዢዎች ወደ ቀልባቸው እንዲመለሱ እና ለሁላችንም ድህነት ይሆን ዘንድ መሥራት ቢጠበቅበትም ፍየል
ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ ሆኖ የተሳከረ ሚና በመጫወት እየተንጎላጀ ይገኛል ።
እኛም እንዳቀድነው፣ ሕዝባችንም አብዝቶ እንደተመኘው፣ አገዛዝንና ከእርሱም የሚታጨደውን ሰቆቃ በማምከን በሀገራችን
ሰማይ ሥር እውነተኛ ፍትሕ እና ዴሞክራሲ ይሰፍን ዘንድ አመርቂ የሚባል አስተዋፅኦ ለማድረግ አለመቻሉ እንዳለ ሆኖ፣
እንደ “የበዐል ነቢያት” አገዛዝን ከቦ እያሸበሽበ፣ የአገዛዝ ጡጫ እንዲፈረጥም ማድረጉ ለብዙዎች ፍች ያልተገኘለት ቅዠት
ሆኖአል። ከዚህ ሁሉ የሚከፋው ደግሞ ከስሁት መንገዱ ለመመለስ በማይችልበት መዳፍ ውስጥ መጨመቁ ነው።
ያነሳኋቸውንና ነገሬን ላለማርዘም እንዲሁም ከተገቢነት አንፃር መዝኘ የተውኳቸውን ሀሳቦች ግንዛቤ ወስጥ በመክተት
ደጋግሜ የሁኔታ ትንታኔ ብሰራም የኢዜማ ስብራት ሲጠገን ለማየት አልቻልኩም። ለመላምታዊ ጥያቄዎቼም አዎንታዊ ምላሽ
ማግኘት ባለመቻሌም አዝናለሁ፡፡
ክቡርነተዎ እንደሚያውቁት፣ የፖለቲካው አውሎ ነፋስ ገና ከሩቅ ግሳንግሱን እየጠራረገ ሲመዘገዘግ፣ የለም የፓርቲያችንን
ቁመናና አሰላለፍ ከወዲሁ እናስተካክል የሚል ተማጽኖ ከማቅረብም ባለፈ በአባላት ፊት ቀርቤ ብሞግትም የሚገባውን ድጋፍ
ባለማግኘቴ ውሳኔያቸውን በጸጋ ተቀብዬ በአባልነት መቀጠሌ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከፍ ብዬ ካወሳኋቸው ምክንያቶችበተጨማሪ በእለት ከእለት ውሎዬ የማገኛቸው ዜጎች ሁሉ አሁንም የፓርቲው አመራር አባል እንደሆንኩ እንደሚቆጥሩ
ለመገንዘብ ችዬአለሁ፡፡ በመሆኑም በሌለሁበት እርምጃ የውግዘትም ሆነ የውዳሴው ተቋዳሽ ለመሆን አልሻም። ስለሆነም
ከዚህ በላይ ሳልዘገይ ነገሮች እንደየዘርፋቸው ማሰቀመጥ ተገቢ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። በሌላ በኩል እንደጠቀስኩት ኢዜማን
አይነ -ግቡና ዘመን ተሻጋሪ ለማድረግ የሰነቅነው ህልም እውን ይሆናል ወይ? በሚለው ጉዳይ ላይ ደጋግሜ የሠራሁት የሁኔታ
ትንታኔ አዎንታዊ ምላሽ ሊያስገኝልኝ ባልቻለበት ሁኔታ ኢዜማ ውስጥ መቀጠሉ ትርጉም የሚሰጥ ሆኖ አላገኘሁትም፡፡
በመሆኑም ይህን በመሰለ ሁኔታ ተጨማሪ ቀናትን በኢዜማ ጣራ ሥር መቀጠል የሚያስችለኝ አንዳች አይነት ምክንያት
አልቀረኝም።
ክቡርነተዎ ፈቃድዎ ቢሆን ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ በተለያዬ ደረጃ ለሚገኙ የኢዜማ ቤተሰቦች መልእክት ለማስተላለፍ
እወዳለሁ ፤ለተወደዳችሁ የኢዜማ አባላት፤ አብረን የተለምነው መንገድ የነጠረ የሚባል አይነት ቢሆንም ፤ ከስልት አንፃር
የተከተልነው መሰመር እሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ እንዳደረገን በቀና ልቦና በሕዝባችን ዘንድ ያለንን ሥፍራ መረዳት ብቻ ብዙ
ይናገራል፤ ሕዝብ ምን ፍሬ አለው ካላልን በስተቀር። በመሆኑም ብዙ ድንቅ የሚባሉ ጊዜዎችን አብረን ብናሳልፍም ከፍ ብዬ
በገለፅኳቸው ምክንያቶች አብሬያችሁ ልጓዝ ባለመቻሌ በጣም አዝናለሁ! እዚህ ውሳኔ ላይ መድረስ ፈጽሞ ቀላል
እንዳልነበረም ልገልፅላችሁ እወዳለሁ፡፡ ከእናንተ ጋር ያሳለፍኳቸው ውስን የትግል አመታት በሕይወቴ ትልቅ ቦታ
የምሰጣቸውና ሁልጌዜም አክብሮቴን የምቸራቸው እንደሆኑ እገልፅ ዘንድ ይገባኛል፡፡ እንዲሁም በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ
ሆኜም ቢሆን ፣ ከልብ ባዘንኩባቸው ጊዜያትም እንኳን ሳይቀር ለእናንተ ያለኝ ፍቅር አለመቀየሩን ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡
ፓርቲውን በሃላፊነት እንዳገለግል ለሰጣችሁኝ እድል፣ ላሳያችሁኝ ፍቅርና በጎነት ሁሉ ከልብ አመሠግናለሁ፡፡ አብረን
ባሳለፍናቸው አመታት ቅር ያሰኘኋችሁ ወንድሞችና እህቶች ካላችሁ በዚህ አጋጣሚ ከልቤ ዝቅ ብዬ ይቅርታ ልጠይቃችሁ
እወዳለሁ፡፡ የእኔ የሁኔታ ትንታኔ ስህተት ሆኖ ያቀዳችሁት ሁሉ ተሳክቶ ኢዜማም የእውነት ዘመን ተሻጋሪ፤ አይነ- ግቡና
ለኢትዮጵያ ሕዝብም መድህን እንዲሆን የምታደርጉት ጥረት እንዲሳካ ከልብ እመኛለሁ፡፡
በዚህ አጋጣሚ በተለያየ መንገድ፣በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ ኢዜማን ስትደግፉ አብሬያችሁ ለመሥራት እድሉ ለገጠመኝ
ለማከብራችሁና ለምወዳችሁ ወገኖቼ ሁሉ ከብዙዎቻችሁ ጋር ለመሥራት መቻሌን ከፈጣሪ እንደተቸረኝ ትልቅ ጸጋ
እቆጥረዋለሁ፡፡ ምናልባትም ከእኔ ከዚህ በላይ ጠብቃችሁ የጎደለ ነገር ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡
በምርጫ ወረዳ 12/13 እንዲሁም በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሳይገባኝ ለለገሳችሁኝ ከፍ ያለ
አክብሮትና ፍቅር ከልብ እያመሰገንኩ ፍቅርና አክበሮቴ እጥፍ ተባዝቶ ይድረሳችሁ! በተፈጠረው ሁኔታ ስለሚያድርባችሁ
ቅሬታ ሁሉ ይቅርታ እየጠየቅኩ አስፈላጊ ሆኖ ቢገኝ ለተሠሩ ግድፈቶች ሁሉ ሃላፊነት ለመዉሰድ
ዝግጁ መሆኔን ለመግለፅ እወዳለሁ፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
3.6K views08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:25:48
2.9K views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:22:44
የሱዳን ተፋላሚዎች ለ24 ሰአት እንዲቆይ የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጣሰ!

የሱዳን ተኩስ አቁም ተግባራዊ ሊሆን ትንሽ ሲቀረው የተፈጠረው ተኩስ እንዲጣስ አድርጎታል።ተኩስ አቁሙ የተደረሰው አሜሪካ ሰብአዊ ቀውስ እንዳይፈጠር በማል በሱዳን ተፋላሚ ወገኞች ላይ ጫና ማሳደሯን ተከትሎ ነበር።

ስምምነት ከተደረሰ ከደቂቃዎች በኋላ በካርቱም ዋና ከተማ የአረብ የቴሌቭዥን የዜና ማሰራጫዎች በቀጥታ ስርጭት ሲዘግቡ ከባድ ፍንዳታ ከጀርባ ይሰማ ነበር ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

የጦር አውሮፕላኖች ከካርቱም በላይ ሰማይ ላይ እያገሱ እንደነበር እና በምስራቅ ወደ ከተማዋ ከፍተኛ የጦር ሰራዊት መግባቱን እማኞች ገልጸዋል።

[Alain]

@Leyu_News
@Leyu_News
3.0K views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 10:53:09 ከጅቡቲ በዱቤ በሚሸመተዉ ነዳጅ ፤ ከ 3 ቢሊዮን ብር በላይ የተጭበረበረ እና ያልተከፈለ ገንዘብ አለ ተባለ

የነዳጅ ግብይት ሪፎርሙ ትኩረት ሰጥቶ እየተተገበረ ካለባቸዉ መስኮች ዉስጥ አንዱ የዱቤ ነዳጅ ግብይት እንዲቋረጥ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል። በግብይቱ ፤ ማደያዎች 10 በመቶዉን ብቻ በጥሬ ገንዘብ ከፍለዉ ቀሪ ክፍያዉን በግዜ ልዩነት ዉስጥ እንዲከፍሉ ይደረግ ነበረ።

በዚህ አንድ አመት ገደማ ባስቆጠረዉ አሰራር ብቻ ታድያ ከ 3 ቢሊዮን ብር በላይ የተጭበረበረ እና ያልተከፈለ ገንዘብ መኖሩን በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት አቶ አህመድ ቱሳ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።አማካሪዉ ነበረ ባሉት የተዝረከረከ አሰራር ከፍተኛ ኪሳራዎች ማጋጠማቸዉን ገልጸዋል።

አንዳንዶቹም በፍ/ቤት የተያዙ ጉዳዮች እንዳሉም አቶ አህመድ ያነሱ ሲሆን ከመጋቢት ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንዲቋረጥ በተደረገዉ በዚህ አሰራር ታድያ ከ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ መኖሩን አስረድተዋል። አሰራሩ የእጅ በእጅ ክፍያን ተግባራዊ ካደረገ በኋላ ትልቅ ስኬት የተገኘበት መሆኑን አቶ አህመድ ጨምረዉ  ተናግረዋል፡፡

@Leyu_News
@Leyu_News
3.0K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 09:04:36
የግብፅ ወታደሮች በሱዳን የተገኙት ለወታደራዊ ስልጠና ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ተናገሩ

በሱዳን የግብፅ ወታደሮች በፈጥሮ ደራሽ ኃይሉ ተይዘዋል


የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አንዳንድ የግብፅ ወታደሮች በጎረቤት ሀገር ሱዳን መኖራቸውን የገለፁ ሲሆን የግብፅ ወታደሮች ግን በቀጠለው ጦርነት ውስጥ እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል። በሱዳን ጦር ሠራዊቱ እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (አርኤስኤፍ) ወታደራዊ ቡድን መካከል በተፈጠረው ግጭት ወደ የትኛውም ወገን የማይሰለፉ ናቸው፤ በወታደራዊ ስልጠና ላይ እንደነበሩ ተናግረዋል ።

አርኤስኤፍ ቅዳሜ እለት በሰሜን ሱዳን በሚገኘው ሜሮዌ ወታደራዊ አየር ሰፈር የግብፅ ወታደሮች የሚያሳይ ቪዲዮ በትዊተር ገፁ ላይ ማጋራቱ ይታወሳል። አል ሲሲ "በሱዳን የሚገኙ የግብፅ ወታደሮችን በፍጥነት ወደ ሀገር ውስጥ እንደምናመጣቸው ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን የገለፁት  ከመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር ባደረጉት ውይይት መሆኑን በከፊል በግል ባለሀብት በሚተዳደረው ኤክስትራ ኒውስ ቲቪ ላይ የተላለፈው መረጃ ያሳያል። ግብፅ በሱዳን "የውስጥ ጉዳይ" ውስጥ ጣልቃ እንደማትገባ ገልፀው ነገር ግን "ተኩስ እንዲያቆሙ ለማበረታታት" በቡድኖች መካከል ያለውን የሽምግልና ሚና መጫወት እንደምትችል ተናግረዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News
3.8K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 08:10:44 ከ14ሺህ በላይ የጦር መሳሪያ ጥይት እና ቦምብ ጭኖ ለማምለጥ የሞከረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ቱሉ ወረዳ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን በተሸከርካሪ ጭኖ ሲጎዝ የነበረ አሽከርካሪ በጸጥታ አካላት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን የቱሉ ወረዳ ፖሊስ  ጽ/ቤት ረዳት ኢንስፔክተር ተስፋዬ አብዲሳ  በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የሰሌዳው ቁጥር ኮድ 3 11188 ኢቲ በሆነ ባለ ሁለት ጋቢና ፒክአፕ ተሽከርካሪ ውስጥ  አስራ አራት ሺኂህ ሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ የጦር መሳሪያ፣ ሶስት ክላሽ እና ሁለት ኤፍ 1 የተባለ ቦምብ ተገኝቷል። የጦር መሳሪያው ከሶማሌ ክልል ቦዴ ከተማ  ወደ ጭሮ ከተማ ሲጓጓዝ አርበረከቴ ኬላ ላይ አልፈተሽም በማለት ከጸጥታ አካላት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉ ተነግሯል፡፡

አሽከርካሪው አልፈተሽም በማለት ለማምለጥ የሞከረ እና  የተኩስ ልውውጥ ከጸጥታ አካላት ጋር የተደረገ ሲሆን  የመኪና ጎማው በጥይት ተመቶ በቁጥጠር ስር ሊውል የቻለ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም አሽከርካሪው ላይ  ምርመራው እየተጣራ መሆኑንም ረዳት ኢንስፔክተር ተስፋዬ አብዲሳ አሳውቀዋል
@Leyu_News
@Leyu_News
4.1K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 21:19:08 ለአራተኛ ቀን የቀጠለው የሱዳን ውጊያ

የተኩስ አቁም እንዲካሄድ ከሚደረገው ግፊት በተቃራኒ በሁለቱ ተቀናቃኝ ሃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ ለአራተኛ ቀን ቀጥሎ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም አሁንም የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ነው።

በካርቱም የፍትህና ዲሞክራሲ ተሟጋቿ ሃላኣ አልቃሪብ አሁንም እሷ ባለችበት አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ እንደሚሰማ ለቢቢሲ ተናግራለች።

“ወዴትም መሄድ አይቻልም ምክንያቱም መውጣት ከፍተኛ አደጋ አለው። ደህንነቱ የተጠበቀ ምንም መንገድ ” የለም ያለችው ሃላኣ በካርቱም ያለው ሁኔታ “እጅግ አሳሳቢ” እየሆነ እንደመጣ ተናግራለች።

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም የሚገኘውን የወታደራዊ ዋና መስሪያ ቤት ለመቆጣጠር በሱዳን ጦርና በፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ አሁንም ድረስ እየተካሄደ ነው።

በጠቅላይ ማዘዢያው አከባቢ ከፍተኛ የቦምብ ድብደባና የከባድ መሳሪያ ደምጾች እንደሚሰማ አል አረቢያ ቲቪ ዘግቧል።

በካርቱም አየርማረፊያና በሌሎችም ቦታዎች ውጊያዎች እንዳሉ ሪፖርቶች እያመላከቱ ነው።

ሁለቱም ተቀናቃኞች የጦሩን ዋና ማዘዣና አየር ማረፊያውን ተቆጣጥረናል ይላሉ።

አራተኛ ቀኑን የያዘውን እና ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች የተገደሉበትን ውጊያ እንዲቆም በርካታ ዓለም አቀፍ ጥሪዎች እየቀረቡ ነው።
የመንግስታቱ ድርጅት ልዩ መልዕክተኛና የሱዳን ተቀናቃኝ መሪዎች ግንኙነት
በተያያዘ የመንግስታቱ ድርጅት የሱዳን መልዕክተኛ ከሁለቱ ተቀናቃኝ ቡድን መሪዎች ጋር በየቀኑ እንደሚገናኙ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

የተመድ ልዩ መልዕክተኛው ቮልከር ፔርተስ የሱዳንን ስልጣን ለመቆጣጠር ከሚዋጉት ሁለቱ ጄነራሎች ጋር በየዕለቱ መረጃ እንደሚለዋወጡ ነው የተናገሩት።

ልዩ መልእክተኛው መሪዎቹ ከተመድ ጋር ግንኙነት ቢኖራቸውም እርስ በእርሳቸው እንዳልተነጋገሩም አክለዋል።

ቮልከር ፔርተስ ጨምረው ሲቨል ሰዎች ከአደጋ እንዲድኑ ውጊያው ለሰብአዊነት እንዲገታና በተጨማሪም የተሟላ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚያደርጉትን ውትወታ እንደሚቀጥሉም አመላክተዋል።

ተደረሰ የተባለው የተኩስ አቁም ባለፈው ዕሁድና ሰኞ ሙሉ በሙሉ ተተግብሮ አልታየም።

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከንም የሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ሃይል አዛዦችን ማነጋገራቸውን እና ደም አፋሳሹን ውጊያ እንዲያቆሙ መጠየቃቸው ተዘግቧል።

የሱዳን ዶክተሮች የሟቾች ቁጥር ወደ 200 መጠጋቱን የገለጹ ሲሆን ትክክለኛው የሞት ቁጥር ከዚህም ሊልቅ እንደሚችል ተገምቷል።

    ቢቢሲ አማርኛ

@Leyu_News
@Leyu_News
1.8K views18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ