Get Mystery Box with random crypto!

የግብፅ ወታደሮች በሱዳን የተገኙት ለወታደራዊ ስልጠና ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ተናገሩ | LEYU NEWS

የግብፅ ወታደሮች በሱዳን የተገኙት ለወታደራዊ ስልጠና ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ተናገሩ

በሱዳን የግብፅ ወታደሮች በፈጥሮ ደራሽ ኃይሉ ተይዘዋል


የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ አንዳንድ የግብፅ ወታደሮች በጎረቤት ሀገር ሱዳን መኖራቸውን የገለፁ ሲሆን የግብፅ ወታደሮች ግን በቀጠለው ጦርነት ውስጥ እንደማይሳተፉ አረጋግጠዋል። በሱዳን ጦር ሠራዊቱ እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (አርኤስኤፍ) ወታደራዊ ቡድን መካከል በተፈጠረው ግጭት ወደ የትኛውም ወገን የማይሰለፉ ናቸው፤ በወታደራዊ ስልጠና ላይ እንደነበሩ ተናግረዋል ።

አርኤስኤፍ ቅዳሜ እለት በሰሜን ሱዳን በሚገኘው ሜሮዌ ወታደራዊ አየር ሰፈር የግብፅ ወታደሮች የሚያሳይ ቪዲዮ በትዊተር ገፁ ላይ ማጋራቱ ይታወሳል። አል ሲሲ "በሱዳን የሚገኙ የግብፅ ወታደሮችን በፍጥነት ወደ ሀገር ውስጥ እንደምናመጣቸው ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን የገለፁት  ከመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር ባደረጉት ውይይት መሆኑን በከፊል በግል ባለሀብት በሚተዳደረው ኤክስትራ ኒውስ ቲቪ ላይ የተላለፈው መረጃ ያሳያል። ግብፅ በሱዳን "የውስጥ ጉዳይ" ውስጥ ጣልቃ እንደማትገባ ገልፀው ነገር ግን "ተኩስ እንዲያቆሙ ለማበረታታት" በቡድኖች መካከል ያለውን የሽምግልና ሚና መጫወት እንደምትችል ተናግረዋል።

@Leyu_News
@Leyu_News