Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.07K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2023-09-20 07:01:02 "ከሰደበኝ የነገረኝ"
~
ከነብያችን ﷺ ክብር ላይ መከላከል ግዴታችን ነው። በባለጌዎች ስራ መቆጣትም ተገቢ ነው። ግን እንዴት ነው የነዚህን ባለጌዎች ስራ ኮፒ ፔስት አድርጎ ማሰራጨት ከሳቸው ክብር መከላከል የሚሆነው? እንዴትስ አስችሏችሁ ነው የነሱን ፀያፍ ንግግር ባደባባይ ደግማችሁ የምትለጥፉት? ወላሂ ከልጁ ብልግና በላይ እንዲህ አይነቱ አካሄድ የበለጠ ያሸማቅቃል። እስኪ አስቡት አንድ ባ ለጌ እጅግ ነውረኛ በሆኑ ቃላት እናታችሁን ቢሳደብና ከዚያ አንዱ ወንድማችሁ ተነስቶ ከእናታችሁ እከላከላለሁ በሚል ስሌት ያንን ፀያፍ ስድብ በያቅጣጫው እያስተጋባ ላ'ገር ቢያዳርሰው ያስደስታችኋል? "ማሻአላህ እናታችንን የሚወድ ጀግና ነው" ብላችሁ ነው የምታሞካሹት? ወይስ በሞኝነቱ ነው የምትሳቀቁት? ከተሳዳቢው ብል ግና በላይኮ የሚያበግነው የዚህኛው ሞኝነት ነው። "ከሰደበኝ የነገረኝ" ሲባል ሰምታችሁ አታውቁም?
ብቻ እንዲህ አይደለም ከኢስላም መከላከል። እንዲህ አይደለም ነብዩን ﷺ መውደድ። ዐረቦች እንዲህ አይነት ውል የሳተ ጥረት ሲያዩ የሚሉት ድንቅ ብሂል አለ። "ሰዕድ ሆይ! ግመል እንዲህ አይደለም የሚነዳው" የሚል።
ነገሩ እንዲህ ነው። ማሊክ ብኑ መና የተሰኘ ይሄ ነው የሚባል ቦታ የሌለው ሰው ነበር። ሌላ ባይችል ግመል መጠበቅ ግን ይችላል። ጥሩ እረኛ ነው። ግመል ጥበቃ ክህሎት የሚፈልግ ሙያ ነው። አንድ አውቃለሁ ባይ ወንድም አለው። ሰዕድ የሚባል። ማሊክ አገባና የደስታውን ጊዜ በቤቱ ሊያሳልፍ ፈልጎ በግመል ጥበቃው ላይ እንዲተካው ወንድሙን ከጠየቀ በኋላ እንዴት አድርጎ መያዝ እንዳለበት ሊነግረው ቢል "ደግሞ ግመል ጥበቃ ሙያ ሆኖ ነወይ?" በሚል ሊሰማው አልፈቀደም። የሆነ ሰዓት ማሊክ ቢወጣ አቶ ሰዕድ ሆየ ዝንጥ ብሎ ለብሶ ወጥቶ ኖኖ ግመሎቹን ባግባቡ ወደ ውሃ ማውረድ አቅቶት፣ በያቅጣጫው ተበታትነውበት ከግራ ቀኝ ሲዋትት ያየዋል። በዚህን ጊዜ ነበር ማሊክ ይህንን ዘመን ተሻጋሪ ስንኝ በወንድሙ ላይ የጣለው።
أوْرَدَهَا سَعْدٌ وسَعْدٌ مُشْتَمِلْ ... مَاهكَذَا يا سعدُ تُورَدُ الإبل
ስለዚህ እንደ ሰዕድ አንሁን። ይሄ የሰሞኑ ዋልጌ የመጀመሪያ ባለጌ አይደለም። የመጨረሻም አይሆንምና ከስህተታችን ትምህርት እንውሰድ። መሰል ጥፋት ሲገጥመን ምን እናድርግ?
1ኛ፦ የባለጌዎችን ነውረኛ ተግባር ባደባባይ መለጠፍ፣ ደግሞ ማስተጋባት፣ አካውንታቸውን/ ገፃቸውን ማያያዝ እጅግ ሰቅጣጭ የሆነ ከአጥፊዎቹ የከፋ ድንቁ ርና ነውና ከዚህ እንቆጠብ።
2ኛ፦ ጠላት ኢስላምን ወይም ነብያችንን ﷺ የሚያንቋሽሽ ፊልም ሲለቅ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰራጭ የሚያደርጉት ሙስሊሞች ናቸው። ይሄ በጣም የሚያም እውነት ነው። "ብታዩትኮ በጣም ነው የሚዘገንነው"፣ "ኧረ የሚወራ አይደለም"፣ ወዘተ እየተባባሉ እየገቡ ያዩታል። እይታው በጨመረ ቁጥር ስርጭቱ፣ ተደራሽነቱ በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል። በእንዲህ አይነት ሞኝነት ሲበግኑ ያገራችን ሰዎች የሚሉት ነገር አለ። "የራሴን ሞኝ ግደልልኝ፣ የሰውን ሞኝ አኑርልኝ።" ወዳጅ የሚበግንባችሁ አትሁኑ።
መሰል ጥፋት ሲገጥመን ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ፣ ኮፒ ፔስት እያደረግን ስድቡን ሳናስተጋባ፣ "ትርጉሙ ምንድነው" እያልን ሞኞች እንዲተረጉሙት ሳናስታውስ፣ "እንትን ተጠቅማችሁ ተርጉሙት" እያልን መንገድ ሳናሳይ፣ የአጥፊዎቹን አካውንት ሳናስተዋውቅ ሃይማኖታችንን ወይም ነብያችንን ﷺ የተሳደበ አንድ ባለጌ ሰው እንዳለ በተመጠነ መልኩ እየጠቀስን መናገር በቂ ነው። ያለበለዚያ አጥፊው ከሚችለው መጠን በላይ ጥፋቱን እናሰራጨዋለን። ሰላም።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
14.3K viewsedited  04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-19 19:45:07
እህታችንን እንርዳት። ከባድ የሆነ ካንሰር አይነት ታማለች።

የባንክ አካውንት
1000558459682
ዘይነባ የሱፍ ሀሰን
ንግድ ባንክ
ሼር አድርጉ ነይቱ ባረከላሁ ፊኩም።
20.1K viewsedited  16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-17 23:16:16
አዋጅ ለሙስሊሞች!
~
ንቁ! በጊዜ የጀመረ ጅብ የት ሊያሳድረኝ ነው የሚሉት ብሂል አለ። በዚህ ከባድ ጊዜ ሙስሊሙ ላይ የጥላቻ ቅስቀሳ የሚያደርግ አካል ሁሉ በእጁ ቢሆን ምን እንደሚያደርግህ አስብ። የእምነት ተቋሞቻቸውን የመሳሪያ ማከማቻ ያደረጉት እነሱ ሆነው ሳለ ምስኪኑን ሙስሊም ህብረተሰብ እየከሰሱ ነው። የክሱ አላማ በቀጣይ ሙስሊሙ የጥቃት ኢላማ እንዲደረግ መቀስቀስ ነው።
ሙስሊሙ ወገኔ ሆይ! የተዘጋጀልህን እያየህ።

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
17.2K views20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-17 13:30:02 ደርስ
~
* መንሃጁ ሳሊኪን
* ክፍል:-

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
12.6K viewsedited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-17 06:39:28 ያንተ ዘር ከማንም በላይ አይደለም
~
ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا فضلَ لعربيٍّ على عجميٍّ، ولا لعجميٍّ على عربيٍّ، ولا لأبيضَ على أسودَ، ولا لأسودَ على أبيضَ -: إلّا بالتَّقوى، النّاسُ من آدمُ، وآدمُ من ترابٍ
"ዐረብ ለሆነ ሰው ዐረብ ባልሆነው ላይ ብልጫ የለውም። ዐረብ ያልሆነውም በዐረቡ ላይ እንዲሁ (ብልጫ) የለውም። ለነጩም በጥቁሩ ላይ የለውም። ለጥቁሩም በነጩ ላይ የለውም። አላህን በመፍራት ቢሆን እንጂ። ሰዎች ሁሉ ከኣደም ናቸው። ኣደም ደግሞ ከአፈር ነው።" [አሶሒሑል ሙስነድ፣ ሙቅቢል፡ 1523]

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል
Https://t.me/IbnuMunewor
16.3K viewsedited  03:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-16 19:33:47 ሑዘይፋ መስጂድ የሚሰጠው ሳምንታዊው የእሁድ ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ።
14.5K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-15 08:13:14
አመድ በዱቄት ይስቃል
~
እምነታቸው እንዳለ በተረት፣ በአስቂኝ ኹራፋት እና አጉል እምነት የተሞላ እንደሆነ አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው። "ፃድቅስ አየሁ ተክለ ሃይማኖት፣ ባንድ እግሩ ቆሞ ሰባት ዓመት" እያሉ እየቀደሱ፣ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ 9 አመት ዓባይ ባሕር ውስጥ በራሳቸው ተዘቅዝቀው በመቆም ለኢትዮጵያ ጸለዩ ብለው መፅሐፈ ገድል የፃፉ፣ ግራኝ የወረወራቸው፣ ግራኝ ፈረሱን ያሰረባቸው እያሉ ግዙፍ ቋጥኞችን የሚያሳዩ፣ ቡና መጠጣት፣ ተምር የእስላም ነው እያሉ አሳፋሪ ትንታኔ የሚሰጡ፣ ማርያም የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን መቀመጫ ለጎመችለት ብለው መፅሐፍ የፃፉ፣ ማህበራዊ ሚዲያውን በመሪ ጌታዎች የመተት ማስታወቂያ ያጥለቀለቁ ... እነዚህ ናቸውኮ ኢስላምን በአጉል እምነት ሊከሱ የሚነሱት? ልካቸውንማ ሊያውቁ ይገባል። ቆማ'ጣን ቆ'ማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል።
ደግሞኮ ይሄ በተረትና መሰረት የለሽ ኮተቶች ማመን 'ሳይንስ' አምላኪ የሆኑት ሳይቀሩ የሚታወቁበት ነው። ያያያዝኳቸው ፅሁፎች የብሪታኒዋ ንግስት የሞተች ጊዜ የወጡ የታዋቂዎቹ CNN, The New York Times እና Daily Mail ዘገባዎች ናቸው። ለንግስቲቱ የመንግስተ ሰማያት በር ተከፈተ፣ ለሷ ሃዘን ቀስተ ደመና በሰማይ ታየ እያሉ ነው የዘገቡት።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
12.7K views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-14 21:08:36 በተለይ ለኦሮሞ እና ለአማራ ሙስሊሞች
~
ወንድሞችና እህቶች! እባካችሁ አላህን ፍሩ! ብዙዎቻችሁ ፖለቲከኛ አፋችሁን ከፍታችሁ እየተከተላችሁ እጅግ ፀያፍ የሆነ ዘረኝነት ውስጥ ወድቃችኋል። ፖለቲካ ውስጥ ከመስመጣችሁ የተነሳ የሙስሊም ደም ከምንም የማትቆጥሩበት ደረጃ ላይ ደርሳችኋል። ፖለቲካ በወለደው ጥላቻ የተነሳ ከሃገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ ብዙ ሙስሊም እየተጎዳ ነው።
ዱዓቶች አላህን ፍሩ ይህንን ጉዳይ ችላ አትበሉ። የኦሮሞ ሙስሊም የአማራ ወገኑ ህይወት የማያስጨንቀው፣ የአማራ ሙስሊም የኦሮሞ ወንድሙ ህይወት ደንታ የማይሰጠው ደረጃ የደረስነው ለኢስላም የሰጠነው ቦታ ከዘር የረከሰ በመሆኑ የተነሳ ነው።
የመጅሊስ ሰዎች አላህን ፍሩ። የብዙዎችን ህይወት እየቀጠፈ ባለው በዚህ ጥንብ ዘረኝነት ላይ ባግባቡ ስሩ። የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ማለት መዘዙ ለሁሉም ከባድ ነው። ኢስላማዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የፖለቲከኞችን ይሁንታ አትጠብቁ። ኦሮሚያ ውስጥ ሙስሊሞች ሲጨፈ ^ ጨፉ ከማንም ቀድሞ ሊጮህላቸው የሚገባው ኦሮሞው ሙስሊም ነው መሆን ያለበት። አማራ ክልል ላይ ሙስሊሞች ሲጨፈ ^ ጨፉ አማራው ሙስሊም ነው ከማንም ቀድሞ ሊጮህላቸው የሚገባው። እኛ ለእኛ ካልተቆረቆርን የሙስሊም ወገናችን ህመም ካላመመን ማን ይቆርቆርልን? ደግሞም እንወቅ! በምናጋግለው ፈተና ውስጥ እስካለን ድረስ እጃችን ቀጥታ ባይገባበት እንኳ በሚጠፋው ነፍስ ሁሉ ከአላህ ዘንድ ተጠያቂዎች ነው የምንሆነው። አላህን እንፍራ! አላህን እንፍራ! በዚህ የዘረኝነት በሽታ ከማንም በላይ እየተጎዳን ያለነው እኛው ነን።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
13.4K viewsedited  18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-14 09:03:52
ከሃይማኖተኛ እስከ ፖለቲከኛ፣ ከአክቲቪስት እስከ አርቲስት በስልጤ ህዝብ ላይ ተነስተዋል። ደግሞ "በ 21ኛው ክ/ዘመን በድግምት ያምናሉ" ይላሉንዴ? ጥንቆላን በ 21ኛው ክ/ዘመን እያራመዱ እንደሆነ አባቶቻቸው እየመሰከሩ አይደለም ወይ?
ለማንኛውም የስልጤ ህዝብ ሆይ! በነዚህ አካላት በተደጋጋሚ እየተነደፍክ እንደሆነ ልብ በል። ከሰሞንኛ ግርግር ባለፈ ድምፅህን አጥፍተህ ዘመን ተሻጋሪ የሆነ መሬት የረገጠ ስራ ላይ አበክረህ ስራ።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
14.1K views06:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-14 07:03:39 ዳንስና ጭፈራውን - ነብዩን ﷺ ማወደስ ብሎ ይጠራዋል።
ከዚያ "አትጨፍር" ስትለው - "ነብዩን ማወደስ አይቻልም ወይ?" ይላል።
ማን አታወድስ አለህ? ጭፈራ ዒባዳ አይደለም ነው የተባልከው።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
13.0K views04:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ