Get Mystery Box with random crypto!

ጥያቄ፡- “የረመዳንን ቀዷእ ቀናት ሳያወጣ በፊት የሸዋልን ስድስት መፆም ይቻላልን?” መልስ፡- “በ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ጥያቄ፡- “የረመዳንን ቀዷእ ቀናት ሳያወጣ በፊት የሸዋልን ስድስት መፆም ይቻላልን?”
መልስ፡- “በረመዳን ያፈጠረባቸውን (ያልፆመባቸውን) ቀናት ቀዷእ ካወጣ በኋላ ከዚያም ስድስቱን ከፆመ ይሄ መልካም ነው። ይህንንም ያንንም ማድረግ የማይችል ከሆነ ግን ነብዩ ﷺ “ረመዳንን ፆሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለ ልክ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው” ያሏትን ስድስቷን (አስቀድሞ) ሊፆም ይችላል። ለምን ይህን አልን? ምክንያቱም የቀዷው ጊዜ ከስድስቷ ፆም በተለየ (ወቅቱ) ሰፊ ስለሆነ ነው። (ስድስቷ ግን) ከሸዋል ውጭ ጊዜ የላትም። የቀዷእ ወቅት ግን ከዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንደመጣው እንዲህ ብላለች፡ ‘በሸዕባን (ወር) እንጂ ቀዷየን አላወጣም ነበር።’ ምክንያቱም በአላህ መልእክተኛ ﷺ ጉዳይ ትጠመድ ስለነበር ነው።” https://www.muqbel.net/fatwa.php?fatwa_id=2278#:~:text=%D9%86%D8%B5%20%D8%A7%D9%84%D8%A5%D8%AC%D8%A7%D8%A8%D8%A9%3A,%D9%83%D9%84%D9%87%20%22%20%D8%8C%20%D9%84%D9%85%D8%A7%D8%B0%D8%A7%20%D9%82%D9%84%D9%86%D8%A7%20%D9%87%D8%B0%D8%A7%20%D8%9F
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 25/ 2014)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor