Get Mystery Box with random crypto!

የሸዋል ስድስት ቀናትን ፆም የሚመለከቱ ነጥቦች ~ 1. ከሸዋል ስድስት ቀናትን መፆም ፋይዳው ምንድ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሸዋል ስድስት ቀናትን ፆም የሚመለከቱ ነጥቦች
~
1. ከሸዋል ስድስት ቀናትን መፆም ፋይዳው ምንድነው?
መልስ፦ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كَانَ كَصِيَامِ الدَّهْرِ
“ረመዷንን ፁሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለው አመት እንደመፆም ነው።” [ሙስሊም፡ 1164]
ስለዚህ ስድስት ቀናትን በሸዋል ወር ውስጥ መፆም አጅሩ ከረመዷን ወር ፆም ጋር የሚቆራኝ ነው ማለት ነው።

2. ከሸዋል ስድስት ቀናትን መፆም የሚጠቁመው ሐዲሥ ሰነዱ አስተማማኝ ነውን?
መልስ፦ ሐዲሡ ሚዛን በሚደፋ አቋም ለማስረጃነት በቂ ነው። ዝርዝር የፈለገ ይህንን ሊንክ ተከትሎ ይመልከት፦ https://tinyurl.com/mucfx3ny

3. ከሸዋል ውጭ ባሉ ወራት ውስጥ ስድስት ቀናት ቢፆም የሸዋልን ፆም ይተካልን?
መልስ፦ ማስረጃ የመጣው ሸዋልን በተመለከተ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ለማለት የሚያስችል መረጃ የለም።

4. አከታትሎ ነው ወይስ አፈራርቆ ነው የሚፆሙት?
መልስ፦ በሸዋል ወር ውስጥ እስከሆነ ድረስ አከታትሎም ይሁን አፈራርቆ፣ ቀጥታ ከዒድ በኋላም ይሁን አዘግይቶ በፈለገው መልኩ መፆም ይችላል።

5. ፆሙን ከሸዋል አንድ መጀመር ይቻላል?
መልስ፦ ሸዋል አንድ ዒድ ነው። በዒድ ቀን መፆም ደግሞ አይፈቀድም።

6. ቀዷእ ያለበት ሰው ሸዋልን መፆም ይችላል?
መልስ፦ ከፊል ዓሊሞች አይቻልም ይላሉ። የአብዛኞቹ ዓሊሞች አቋም ግን ይቻላል የሚል ነው። ጠንካራውም አቋም ይሄ ነው። ይህንን ከሚጠቁሙ መረጃዎች ውስጥ፦

[ማስረጃ አንድ]፦

እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብላለች፦
كانَ يَكونُ عَلَيَّ الصَّوْمُ مِن رَمَضَانَ ، فَما أسْتَطِيعُ أنْ أقْضِيَ إلَّا في شَعْبَانَ
ከረመዷን (ያልፆምኩት) ፆም ይኖርብኝ ነበር። በሸዕባን እንጂ ቀዷኡን ማውጣት አልችልም ነበር።” [ቡኻሪ፡ 1149] [ሙስሊም፡ 1849]
ልብ በሉ! ሸዕባን በኢስላማዊው አቆጣጠር ከረመዷን በፊት ያለው ወር ነው። የረመዷንን ቀዷእ ሳታወጣ ቀጣዩ ረመዷን ሲቃረብ ነበር የምትፆመው። በዚህ መሃል ላይ ትልልቅ አጅር ያላቸው የዐረፋ ፆም፣ የዐሹራእ ፆም፣... አሉ። ዓኢሻ ይህን ሁሉ አትፆምም ነበር፣ ከአመት እስካመት ሱና ፆም አትፆምም ነበር ብሎ ማሰብ ይከብዳል።
“አይ ለሳቸው ስትል ነበርኮ የረመዷንን ቀዷእ የምታዘገየው” ከተባለ “አዎ። ነብያችን ﷺ ሸዕባንን አብዛኛውን ይፆሙት ስለነበር ሸዕባን ላይ ቀዷእ ለማውጣት ሰፊ ጊዜ ይኖራታል። ግና እሳቸውኮ
* ዐረፋና ዐሹራእ ይፆሙ ነበር።
* በሌሎችም ወራት “አያፈጥሩም እስከምንል ድረስ ይፆሙ ነበር” ብላለች ዓኢሻ። [ቡኻሪ፡ 1969]
* ከየወሩ ሶስት ቀን ይፆሙ ነበር። [አቡ ዳውድ፡ 507]
* በየ ሳምንቱም ሰኞና ሐሙስም ይፆሙ ነበር። [ቲርሚዚይ፡ 745]
* በተጨማሪም “ከረመዷን ቀጥሎ በላጩ ፆም የሙሐረም ወር ፆም ነው”ብለዋል። [1163]
* በየወሩ “አያመል ቢድ” ማለትም 13ኛ፣ 14ኛ እና 15ኛ ቀናትን መፆምንም አዘዋል። [ነሳኢ፡ 7/222] [ቲርሚዚይ፡ 761]
ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋር የረመዷንን ቀዷእ እስከ ሸዕባን ድረስ የምታዘገይበት አንዱ ምክንያት ቀጣይ ረመዷን እስካልገባ ድረስ ማዘግየት ስለሚቻል ነው። እንጂ በዚህ ሁሉ መሃልም መፆም ትችል ነበር።

[ማስረጃ ሁለት]፦

የረመዷንን ቀዷእ ወሩ እንዳለቀ ወዲያውኑ አከታትሎ መፆም ግዴታ አይደለም። ይሄ የብዙሃን ዑለማእ አቋም ነው። ቀጣይ ረመዷን እስካልገባ ድረስ ማዘግየት ይቻላል። ወዲያውና አከታትሎ መፈፀም ግዴታ ካልሆነ ደግሞ መሃል ግዴታ ያልሆኑ ፆሞችን መፈፀም የተከለከለ አይሆንም። ይህ እንግዲህ ቀዷእ ላለበት ሰው በላጩ አፈፃፀም ቀድሞ ቀዷኡን መፆም፣ ከዚያም የሸዋልን ስድስት ማስከተል ከመሆኑ ጋር ነው።
ነገር ግን በወር አበባ ወይም በሌላ ምክንያት በርከት ያለ ቀዷእ ያለ ከሆነ ሸዋልን ለመፆም በቂ ጊዜ ላይኖር ይችላል። ወይም የፆሙ ጊዜ በመደራረቡ ሊከብድ ይችላል። በዚህና መሰል ሁኔታ ላይ ላለ አካል ሸዋልን የመፆም አጅር እንዳያልፈው ቢያስቀድምና ቀዷኡን አረፍ ብሎ ቆይቶ ቢፆም የሚከለክለው ግልፅ ማስረጃ የለም።

ብዥታዎች፦
-
የግዴታ ፆምን ቀዷእ ሳይፆሙ ሱና ፆም መፆም አይቻልም የሚሉ ዓሊሞች እንዳሉ ገልጫለሁ። ከሚጠቅሷቸው ማስረጃዎች ውስጥ፦

[አንዱ]

መግቢያዬ ላይ የጠቀስኩትን “ረመዷንን ፁሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለው አመት እንደመፆም ነው” የሚለውን ሐዲሥ ነው። ማስረጃ የሚያደርጉበት አግባብ የተጠቀሰው አጅር ሙሉ ረመዷንን ፁሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለን ነው የሚል ነው።
ይሄ ግን አብዛኛው ሙስሊም ረመዷንን ሙሉውን ስለሚፆም በዚህ መልኩ ተገለፀ እንጂ በተጨባጭ ሸሪዐዊ ምክንያት ሙሉውን ያልፆመ ሰው ከተጠቀሰው አጅር ውጭ ይሆናል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ያክል ነብያችን ﷺ “ረመዷንን አምኖና አጅሩን አስቦ የፆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል” ብለዋል። ይህ ማለት ግን በወር አበባ ምክንያት ሙሉውን ያልፆመች ሴት ይህንን አጅር አታገኝም ማለት አይደለም።

[ሁለተኛ] ማስረጃ የሚያደርጉት ተከታዩን ሐዲሥ ነው፦
من أدركَ رمضانَ وعليهِ من رمضانَ شيءٌ لم يقضهِ، لم يتقبَّل منهُ ومن صامَ تطوُّعًا وعليهِ من رمضانَ شيءٌ لم يقضهِ، فإنَّهُ لا يتقبَّلُ منهُ حتَّى يصومَهُ
“በሱ ላይ ቀዷእ ያላወጣው የረመዷን ፆም እያለበት ረመዷን የደረሰበት ሰው አላህ አይቀበለውም። በሱ ላይ ቀዷእ ያላወጣው የረመዷን ፆም እያለበት ግዴታ ያልሆነ ፆም የፆመ ሰው ቀዷኡን እስከሚፆም ድረስ ተቀባይነት አይቀበለውም።” [ሙስነድ አሕመድ፡ 8606]

መልስ፦ ዶዒፍ ነው። [አልዒለል፣ ኢብኑ አቢ ሓቲም፡ 768]

[ሶስተኛ] የሚጠቀሰው እንዲህ የሚል ነው፦
አንድ ሰው፡ “የረመዷን ቀዷእ አለብኝ። ከመሆኑም ጋር አስሩን ትርፍ ፆም ልፆም ፈልጌ ነበር” ሲል አቡ ሁረይራህ ረዲየላሁ ዐንሁ፡ “አይሆንም። ይልቁንም በአላህ ሐቅ ጀምር፣ እሱን ቀዷእ አውጣ። ከዚያ በኋላ የፈለግከውን ትርፍ ፆም ፁም” አሉ። [ሙሶነፍ ዐብዲረዛቅ፡ 7715]

መልስ፦ ግንዛቤው ላይ የተለያዩ ሃሳቦች ከመሰንዘራቸው ጋር ቀጥታውን ስንወስድ ከዓኢሻ ሐዲሥ ጋር የሚቃረን ነው። የዓኢሻ ሐዲሥ ደግሞ የነብዩ ﷺ ኢቅራር (ማፅደቅ) ያለበት ስለሆነ ቅድሚያ ይሰጠዋል።

[ማጠቃለያ]:-

ስለዚህ የረመዳን ፆም ቀዷ ያለበት ሰው
① ለቀዷው ሰፊ ጊዜ ስላለና
② የሸዋል ጊዜ አጭር ስለሆነ ሸዋልን አስቀድሞ መፆም ይችላል።

* ይህንን ነጥብ ዘለግ አድርጌ መዳሰስ የፈልግኩት ሸዋል ቢያልፍም እንኳ ቀዳኡን ሳይፆሙ የሸዋልን ስድስት ቀናት መፆም አይቻልም የሚሉ ዑለማዎችን ፈትዋ ነጥለው ትኩረት የሚሰጡ ስላሉ ነው። ቀደም ብዬ እንደጠቀስኩት መፆም ይቻላል የሚለው አቋም የብዙሃን ዑለማእ ምርጫ ነው። በሸይኽ ሙቅቢል ፈትዋ ፅሁፌን ላሳርግ:-