Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.25K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 32

2023-10-06 06:49:21
የሐሰን ታጁ አድናቂ ሆናችሁ የተውሒድን በ3 መከፈል ለምትተቹ እንካችሁ፡፡ እዚሁ ሰፈር ያገኘሁት ነው።
18.4K viewsedited  03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 20:19:34 ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:-
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 235፣ باب القناعة
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
15.5K views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 18:35:23 ከደቂቃዎች በኋላ የሪያድ ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ።
15.6K views15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 12:45:48 ሰሞኑን በኢኽዋን ቡድን በኩል "መዳኺላ መዳኺላ" የሚሉ ጩኸቶች በዝተዋል። የዚህ ቡድን አባላት የጋራ በሽታ የሚጮሁትን ሆኖ አለመኖር ነው። "ስም እየሰጣችሁ አትከፋፍሉን" ይልና ዞሮ "ጃሚያ" "መድኸሊያ" እያለ ይወነጅላል። "ዑለማእ አትሳደቡ" እያለ የሱና ዑለማዎችን ግን "የቤተ መንግሥት ቅጥረኞች" እያለ እጅግ ፀያፍ ውንጀላ ይወነጅላል።
ከሰሞኑ ያደረጉትም ይህንኑ ነው። ምንም ዓይነት ቡድናዊ ይዘት በሌለው ጉዳይ ላይ ከብዙ ጩኸት መሃል ነጥለው "መዳኺላ" እያሉ ቡድናዊ ታርጋ መለጠፍ ላይ ተጠምደው አይተናል። አንዱ ኢኽዋኒም ስለ መዳኺላ ሊያብራራ እየተዘጋጀ እንደሆነ ፅፎ አይቻለሁ። ይህንን ካየሁ በኋላ ይህንን የዲን ነጋዴ ቡድን በተከታታይ ለመቆንጠጥ እያሰብኩ ነው። እነሱ ውንጀላቸውን በለቀቁ ቁጥር እየተከተሉ መከላከል አልታየኝም። ከዚያ ይልቅ የቡድኑንና የቁንጮ አካላቱን ጉዳጉድ በድምፅ ትምህርት ለመዘርዘር እያሰብኩ ነው። ሸይኽ ሙቅቢል - ረሒመሁላህ - "እኔ ማጥቃት ነው ደስ የሚለኝ። እንጂ መከላከል አይደለም" የሚሉት ወደው አይደለም። ባይሆን ጊዜየን ብዙም በነሱ ላይ ማጥፋት ስለማልፈልግ አለፍ አለፍ እያልኩ በሚመቸኝ ጊዜ ነው የማቀርበው፣ ኢንሻአላህ።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
13.0K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-05 10:47:51 ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች
~
① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ።
"አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።"
"ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።"

② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚገድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የሃንዳውት፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ።

③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። የማንም ሙገሳ ከፍ እንደማያደርግህ ሁሉ የማንም ትችትም ዝቅ አያደግህም። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው።
"ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።"

④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው።
"ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።"

⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ እራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ እንዳለው ተረዳ።
"Education is a better safeguard of liberty than a standing army."

⑥ እራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ እንጂ። አንተ'ኮ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም።
"እራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።"

⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም ። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሐብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል።
እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮች ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው።
"ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።"
"አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ እራስህ እያለፍክ ነው።"

⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ እራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ።
"ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።"

⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ።
ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ። "መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ።
"ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።"

(10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ እንደ ቴኳንዶ ያሉ ራስን መከላከያ ሥልጠና፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ።
"ራስን ብቁ ዜጋ ማድረግ ለሀገርም ለወገንም እሴት መጨመር ነው።"

(11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን።
"ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።"
"ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።"

(12) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በተልካሻ ቆሻሻ ነገሮች አይታሰርም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ኣ? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። እራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም።
"እራስን በሱስ በመጉዳትና እራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።"

(13) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል" ይባላል።
"የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።"
13.7K views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-03 21:28:04 ሳይከካ ተቦካ
~
ካሚልም ውቅያኖስ አይደለም። የሱን ሃሳብ የነቀፈው ህዝብም እፍኝ አፈር አይደለም። በርግጠኝነት ከካሚል ስህተት ይልቅ የያሲን ኑሩ ንቀትና እብሪት ይበልጥ ያበሽቃል። ይህን ያክል እብሪት ያዘለ ቃል የሚሰነዝረው ምንም ቢናገር ከጎኑ የሚቆም መንጋ እንዳፈራ ማሰቡ ነው። የሚገርመው ለህዝበ ሙስሊሙ በጠላት የሚቀርብለት ፋታ የማይሰጥ ተደራራቢ አጀንዳ አልበቃ ብሎ ራሳቸውን አጀንዳ የሚያደርጉ አካላት መኖራቸው ነው።
1- የያሲን ኑሩ ጥፋት ሀ ብሎ የሚጀምረው "ውቅያኖስ" አይትተችም ብሎ ሲነሳ ነው። ወንድሜ ያንተ ውቅያኖስ ቀርቶ ሶሐቦች ይሳሳታሉ። "ሁላችንም አራሚዎች እና ታራሚዎች ነን" ያሉት ኢማሙ ማሊክ ናቸው።
2- ደግሞም እወቅ! በኢስላም ግለሰባዊ ቅድስና የለም። ከነብያት ውጭም ፍፁምነት (ዒስማ) የለም። አንድ ሰው ባደባባይ ለታየ ስህተቱ እርምት መሰጠቱን ስብእና መግደል እንደሆነ ማሰብ ጥራዝ ነጠቅነት ነው። ይህንን እከክልኝ ልከክልህ በቡድን ማሰብ አቁሙ።
3- ደግሞም ከውግዘት በፊት ማጣራት የምትለው ምኑን ነው? በሚስጥር የተነገረ ሳይሆን በምስል የታጀበ ባደባባይ የተነገር ድምፅ ሰምቶ ነው ሰው የተቸው። ይዘት በሚቀይር መልኩ የተቆረጠበት ካለ እርምት መስጠት የሱ ድርሻ ነው። የተናገረው ነገር ለቀረበበት መድረክ የማይመጥን፣ ወቅታዊ ፈተናዎችን ከግንዛቤ ያላስገባ፣ የጉዳዩ ሰለባ የሆኑ ሙስሊም ወገኖቹን ስሜት ያልጠበቀ ነው። ይህንን መንቀፍ ነው እፍኝ አፈር የሚያሰኘው?
ደግሜ እላለሁ! የካሚል ንግግር ስህተት ከመሆኑ ጋር እንዲህ አይነት እብሪት የለውም።
ለማንኛውም ህዝቡ እያለ ያለው አጭርና ግልጽ ነው። ምናልባት እናንተን ካልታያችሁ አናውቅም እንጂ እየደረሰብን ያለ ጥቃት አለ። ጥቃትና መድሎ ለሚያደርሰው አካል በፍጆታነት የሚያገለግል ንግግር ከመናገር ተቆጠቡ ነው። አሁን ይሄ ሃሳብ ለመረዳት ሩቅ ነው? ይገርማል! ሌላው አካል አላማው ስለሆነ ነው የሚጎዳን። እናንተ ምንድነው የምትፈልጉት?

"ምሳርማ ምን ያርግ የብረቶች ልጅ
ያ የኛ ወልጋዳ አስጨረሰን እንጂ!"

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
17.5K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-03 21:27:58
13.8K views18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-03 16:00:28
15.0K views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-02 19:27:44 ዐምር ብኑል ዓስ - ረዲየላሁ ዐንህ - በዘመነ ጃሂሊያ ከቁረይሽ ፈረሰኞችና ጀግኖች ውስጥ አንዱ ነበር። እጅግ ብልህና የተካነ ፖለቲከኛ ነበር። ዐምር ብኑል ዓስ የሑደይቢያ ስምምነት የተደረገ አመት ነው የሰለመው። ከኻሊድ ብኑል ወሊድና ከዑሥማን ብኑ ጦልሐ ጋር ወደ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ በመምጣት ነው አብረው የሰለሙት። የዛቱ ሰላሲል ዘመቻ ላይ በመካፈል በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሆነ ቦታ ላይ አሚር ሆኖ ተሹሟል። መካ የተከፈተች አመት ደግሞ የሁዘይል ጎሳ ወደሚያመልኩት የሱዋዕ ጣዖት ልከውት ሄዶ አፈራርሶ ተመልሷል። በዑመር፣ በዑሥማን እና በሙዓዊያ ተሹሞ አገልግሏል። በዑመር ዘመነ ኺላፋ ግብፅን በድል የከፈታት እሱ ነው። በመጨረሻም በ90 አመት እድሜው በ43 ዓመተ ሂጅራ ይህቺን ዓለም በሞት ተለይቷል። ረዲየላሁ ዐንሁ ወአርዷህ።
[ሚንሓቱል ዐላም፣ ሸይኽ ዐብደላህ አልፈውዛን፡ 8/95]

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
15.4K viewsedited  16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-02 17:58:05 አንድ የኛን ነባራዊ ሁኔታ ገላጭ የሆነ እንዲህ የሚል ግጥም አለ:-

"ዝም ያለው ዘመዴ - እኔ ሳጣጥር፣
ሞተ ቢሉት መጣ - አልቅሶ ሊቀብር።"
.
በቅርቡ አንድ ዳዒያ ለህክምና ወደ ቱርክ በሄደበት የሞቱ ዜና ሲዘዋወር ነበር፣ አላህ ይማረውና። በርግጥ ይህንን ወንድም ቀድሜ ከነ ጭራሹ አላውቀውም። ግን ረዘም ላለ ጊዜ በህመም ላይ እንደቆየና ማንም ከጎኑ እንዳልነበረ አሁን ከሞተ በኋላ ሲወራ ሰማሁ። በጣም የሚያሳዝን ነው። ለምንድነው ግን በዚህ መጠን ሰው በቁሙ እያለ ከመጠየቅ ይልቅ ሩጫችን ብዙም በማይጠቅምበት ባለቀ ሰዓት መዋከብ ወይም ሞቱ ሲሰማ ጊዜ መጯጯህ የሚቀናን? ያሳዝናል።
ለማንኛውም አሁንም ከምናውቃቸው መሻይኾችና ኡስታዞች ውስጥ ጤናቸውና ኑሯቸው ፈተና ውስጥ የሆኑ ይኖራሉና ቀረብ ብሎ መጠየቅ ይልመድብን። በርግጥ እንዲሁ ሰሞንኛ ስሜቴን ለመግለፅ ያህል እንጂ ዞረን እዚያው እንደሆንን ይገባኛል። ብቻ ባለቀ ሰዓት መሯሯጥ ወይም ሞታቸውን ጠብቆ ከንፈር መምጠጥ ትርጉም የለውምና ሊበቃን ይገባል። ይሄ አካሄድ ከሞቱት ባልተናነሰ ያሉትንም ጭምር ሞራላቸውን በመጉዳት፣ ተስፋቸውን በማደብዘዝ፣ ልባቸውን በሃዘን በመስበር የሚገድል ነው። አላህ ልብ ይስጠን!

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
15.0K views14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ