Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.25K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 30

2023-10-16 11:14:36
ለምን ግን ይሁ^ዶችን ይደግፋሉ?
~
"ጭቆናና በደል እየደረሰብኝ ነው" የሚል አካል ፈፅሞ ያቺን የበደል ቋት አገር አይደግፍም ነበር። በተለይ ደግሞ ይሁ ^ዶች ጌታችንን ሰቅለዋል የሚል ህዝብ ከበደለኞች ጎን ሲሰለፍ ማየት ሊገርም ይችላል። በእለታዊ ቅዳሴው ጭምር ይሁ ^ዶች የሚያመልከውን አምላክ እንደሚጠሉ እየተናገረ እንዴት እዚህ ይደርሳል? በዚያ ላይ ይ ሁዶቹ ዘንድ ክርስቲያኖች ጣ'ዖት አምላኪዎች እንደሆኑ ሲታይ የበለጠ ይገርማል። ይህ ሁሉ በሆነበት የሃይማኖታቸውን ቀኖና፣ የተአምረ ማርያምን አስተምህሮ ደፍጥጠው የበደል ዶፍ ለሚያወርዱት ይሁ ^ዶች የሚወግኑበት ቢያንስ ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች አሏቸው።

1ኛና ዋናው ምክንያት ለኢስላምና ለሙስሊሞች ያላቸው ለከት የለሽ ጥላቻ ነው። ሙስሊሞችን የሚያጠቃን አካል እንኳን ይሁ ^ድ ሆኖ ማንም ቢሆን ይደግፉታል። ሂት ^ለር ራሱ በይሁ ^ዶች ቦታ ሙስሊሞችን ቢሆን ኖሮ የጨፈ -ጨፈው ቅዱስ ያደርጉት ነበር። ይህንን ማረጋገጥ ከፈልግክ 30 ሺ አካባቢ የወሎ ሙስሊሞችን የጨፈ -ጨፈው አፄ ዮሐንስ እነሱ ዘንድ ያለውን ቦታ ማወቅ ነው።
2ኛው ምክንያት ደግሞ ይሁ ^ዶችን ቅዱስ ፍጡር የሚያደርጉ መሆናቸው ነው። ለዚያም ነው ከዝሙት ጋር የተያየዘ የውሸት ተረት ፈጥረው በቀዳማዊ ምንሊክ በኩል ይሁ ^ዶች ነን የሚሉት። "ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ #ይሁዳ" የሚለውን መፈክራቸውን አስታውሱ።

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
16.5K viewsedited  08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-16 09:31:58
የጥላቻን መርዝ እድሜ አይለውጠውም። የ71 አመት አዛውንት ነው ይህንን ለአይን እንኳ የሚያሳሳ አንድ ፍሬ እምቦቀቅላ 26 ጊዜ በስለት በሳስቶ የገደለው። ገዳዩ ሙስሊም ስላልሆነ፣ ከምንም በላይ ደግሞ ሟቹ ሙስሊም ስለሆነ ጉዳዩ ከሽብር ጋር አይያያዝም፡፡ በስሱ ካልሆነ በስተቀርም የረባ ሸፋን አያገኝም። አስመሳይነት የነገሰበት ዓለም።
15.6K views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-15 16:23:50 ቀልብ የፅድቅም የጥፋትም የእዝ ማዕከል
~~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
ጀነት ነፍስ በምትጠላቸው ነገሮች ተከባለች፤ ጀሀነም ደግሞ ነፍስ በምትወዳቸው ሸይጧን በሚያስውባቸው አማላይ ነገሮች፡፡ በብዙ ሁኔታዎቻችን ከአረሕማን ይልቅ ለሸይጧን የቀረብን ነን፡፡ ዐይኖቻችን፣ ጆሮዎቻችን፣ እጆቻችን፣ እግሮቻችን፣ እንዲሁም ምላሳችን ለሸይጧናዊ ተልእኮ የሰሉ ናቸው፡፡ ቀላሉን አምላካዊ ክልከላ መታገስ አቅቶን ከባባድ ሸይጧናዊ ልፋት ላይ እንተጋለን፡፡ ሁሉም የሰውነታችን ክፍሎች ለጥፋት ሲተባበሩ፣ አንዳቸው ብቻ ለሚበቁት ኸይር ግን ተባብረውም ይዝላሉ፡፡ ይሄ ሁሉ የሚሆነው እንግዲህ ማዕከሉን “ዋግ” ሲመታው ነው፡፡ ቀልብ በሺርክ፣ በቢድዐ፣ በስሜት፣ ለሙስሊሞች በምታረግዘው ክፋት፣ … ከተበከለች ታማ፣ ታውካ፣ አመርቅዛ ትሞታለች። ታዲያ ቀልብ ስትሞት ሞቷ ለኸይሩ እንጂ ለሸሩማ ኢንኩቤተር ትሆናለች - ክፉ የሸር መፈልፈያ። ብቻ ሂወቷ በኢማን ካልኩሌተር ሲሰላ ያለ ኢማን ሂወት የለምና ሞታለች - የምር ሞት! ከዚያስ? ከዚያማ ቀልብ ተበላሽታ ሌላው ሰውነት ምን ጤና ሊኖረው? የአካል እንቅስቃሴ በሙሉ ደመ-ነፍሳዊ ይሆናል። ተንቀሳቃሽ ሙት!!! ግድግዳ የተጠጋ እንጨት ሆኖ ሂወት እንዳለው ያስባል፡፡
ከዚህ በኋላ ዐይንም ዐይን ጆሮም ጆሮ አልሆነም፡፡ የሰማያትና የምድር አፈጣጠር፤ የሌሊትና የቀን መተካካት ለሱ ከታክሲዎች መተላፍ፣ ሽንት ቤት ደርሶ ከመመለስ ብዙም ልዩነት የለውም፡፡ ችግሩ ከማዕከሉ ነዋ!

(أَفَلَمۡ یَسِیرُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ فَتَكُونَ لَهُمۡ قُلُوبࣱ یَعۡقِلُونَ بِهَاۤ أَوۡ ءَاذَانࣱ یَسۡمَعُونَ بِهَاۖ فَإِنَّهَا لَا تَعۡمَى ٱلۡأَبۡصَـٰرُ وَلَـٰكِن تَعۡمَى ٱلۡقُلُوبُ ٱلَّتِی فِی ٱلصُّدُورِ)
((ለነርሱም በነርሱ የሚያውቁባቸው ልቦች ወይም በነርሱ የሚሰሙባቸው ጆሮዎች ይኖሩዋቸው ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን እነሆ ዐይኖች አይታወሩም። ግን እነዚያ በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ይታወራሉ፡፡)) (አልሐጅ፡ 46)

በሌላ በኩል ልብ ከተስተካከለች፣ በኢማን ከተዋበች፣ በተቅዋ ካሸበረቀች መላ ሰውነት ጤና ይኖረዋል፡፡ ፊትም ኑር ይላበሳል፡፡ ዐይኖች በሐራም አይገግሙም፡፡ ጆሮዎች ለሙዚቃ አይቆሙም፡፡ ምላስም የሀሜት ማሽን አትሆንም፡፡ ከውጭ ሙስሊም ያልሆነ ገፅታ እየተስተዋለ ምላስ “ዋናው ልብ ነው” እያለች አታሽቃብጥም፡፡ ማዕከሉ ነቅቶባታላ!
ልብ ስትስተካከል እውነተኛ ማንነት ይገኛል፡፡ ከውስጥም ሙስሊም፣ ከውጭም ሙስሊም! በሐያእ የለሰለሰ፣ በውጭ ገፅታው ያልተኮፈሰ፣ በልቡ የመጠቀ፣ ከእንቶ ፈንቶ የራቀ ልዩ ስብእና!!! አቡበክር አሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ከሌሎች የመጠቁት በሶላትና በፆማቸው ብዛት አልነበረም፡፡ ይልቁንም ልባቸው ውስጥ በፀደቀ ነገር ነበር። ኢማን! የቀልብ ልዩ ክብር!!!
ባጭሩ ጥፋታችንም ልማታችንም ከልብ ጋር የተሳሰረ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ እኔና እርሶ የቱጋ ነን? ሰገነት ወይስ ጫማ ተራ? ነው ወይስ መሀል ሰፋሪ? በሌላ አነጋገር ልባችን ጤነኛ ነው? በሽተኛ ነው? ወይስ ሙት ነው?
ለካ ይህንንም ለማወቅ ልብ ያስፈልጋል፡፡ ((ባለ ልቦናዎቹ እንጂ አይገነዘቡም)) አይደል ያለው ኻሊቁ?
አንተ ልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታችን ሆይ! ልቦቻችንን ወደ ትእዛዝህ አዙርልን። በዲንህም ላይ አፅናን፡፡ አላሁመ ኣሚን፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ 2001)
https://t.me/IbnuMunewor
16.1K views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-15 15:21:01 ደርስ
~
* መንሀጁ ሳሊኪን
* ክፍል:-
* የደርሹ መነሻ፦ باب نواقض الوضوء
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
13.4K views12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-13 21:25:28 ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:-
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 244፣ ሐዲሥ ቁ.
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
17.5K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-13 18:34:21 ከደቂቃዎች በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል፤ ኢንሻአላህ።
12.6K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-13 14:58:41 ባመቱ በድጋሜ የተለጠፈ
~
በቅርቡ በወጣው የ12ኛ ክፍል የማትሪክ ውጤት ላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ወይም ሙሉ ተማሪ ለዩኒቨርሲቲ ያሳለፉት አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንደሆኑ ሰምተናል። እንደ አፋር፣ ሶማሊ፣ ቤኒሻንጉል፣ ምስራቁ የኦሮሚያ ክፍል፣ ... መሰል አካሄድ ቢከተሉ ብዬ ተመኘሁ። በዚህ ዘመን በትምህርት፣ በጤና፣ በሌሎችም ማህበረሰባዊ አገልግሎቶችን በሚሰጡ ተቋማት ላይ አድምቶ መስራት ለወገን ትልቅ ውለታ መዋል ነው። ፖለቲከኞች በህዝብ ስም የዘር ጥላቻ እየጋቱ ለወገናቸው ጠላት ከሚያፈሩ ኑሮውን የሚያሻሽል ልማት ላይ ትኩረት ቢሰጡ ይሻል ነበር።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
13.4K views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-13 09:13:05
12.6K views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-13 09:10:46 ዑመሩል ፋሩቅ ሸይጧን የሚሸሸው ሶሐቢይ!
~
ሶሐቢዩ ሰዕድ ብኑ አቢ ወቃስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፡-
በአንድ ወቅት ዑመር ብኑል ኸጧብ ከነቢዩ (ﷺ) ቤት ሊገቡ ፍቃድ ጠየቁ፡፡ ከነቢዩ (ﷺ) ዘንድ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚያወሩ ሴቶች ነበሩ፡፡ የዑመርን ድምፅ ሲሰሙ ሒጃባቸውን አስተካክለው ሊለብሱ ተሯሯጡ፡፡ ረሱል (ﷺ) እየሳቁ ለዑመር እንዲገቡ ፈቀዱላቸው፡፡
ዑመር፡ “አላህ ጥርስህን ያስቀው የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አሏቸው፡፡
ነብዩ (ﷺ)፡ “እነዚህ እኔ ጋር የነበሩ ሴቶች ገረሙኝ፡፡ ድምፅህን ሲሰሙ ወደ ሒጃባቸው ተሯሯጡኮ” አሉ፡፡
ዑመር፡ “አንተ ነህ ልትከበርና ልትፈራ የሚገባህ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!!” ካሉ በኋላ “እናንተ የነፍሶቻችሁ ጠላቶች! እኔን ትፈራላችሁ የአላህ መልእክተኛን አትፈሩምና?!” አሉ ለሴቶቹ።
ሴቶቹ፡ “አዎ ከረሱል (ﷺ) ይልቅ አንተ ደረቅና ሃይለኛ ነህ” አሉ፡፡
ከዚያም ረሱል (ﷺ) ለዑመር እንዲህ አሏቸው:– “ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ ይሁንብኝ! ሸይጧን በአንድ መንገድ ላይ በጭራሽ አያገኝህም፣ መንገድ ቀይሮ በሌላ መንገድ ቢሄድ እንጂ!” [ቡኻሪ፡ 3294] [ሙስሊም፡ 2396]

ይሄ ሐዲሥ ለዑመር ጠላቶች ምቾት የሚነሳ ነው፡፡ ሺዐዎች የዑመር ስም ሲነሳ በጥላቻ እብደታቸው እንደሚነሳ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ድረስ ይሄ ነገር በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ እ.ኢ.አ በ2005 ኢራቅ ውስጥ 15 ሰዎች ስማቸው ዑመር ስለሆነ ብቻ በሺዐዎች ተገድለዋል፡፡ በቅርቡም ኢራን ውስጥ በርካታ ዑመሮች በሌላ ሳይሆን በስማቸው ብቻ ከስራ እንደተባረሩ ተነግሯል፡፡ ይሄ ለዑመር ያላቸው ጥላቻ እጅግ የመረረ እንደሆነ የሚያመላክት ነው።

ሌላ ነገር፡፡ መዲና ውስጥ የሚገኘው የነብዩ (ﷺ) መስጂድ ካሉት በርካታ በሮች ውስጥ አንዱ “ባቡ ዑመር" ነው፣ "የዑመር በር”፡፡ ታዲያ ሺዐዎች ምን አሉ? “ለዑመር ካለን ጥላቻ የተነሳ ወደ መስጂዱ ስንገባ በዑመር በር በኩል አንገባም” አሉ። ይህንን የሰማ አንድ ሸይኽ ምን አለ ታዲያ? “ረዲየላሁ ዐንከ ያ ዑመር! ሸይጧን በህይወትህ ሳለህ ብቻ አይለም ሞተህም ይሸሽሃል!”
አላሁ አክበር!!!

(ኢብኑ ሙነወር፣ 03/02/2005)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
14.6K views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-12 20:20:08 ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:-
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 241፣ باب الكرم والجود
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
13.3K views17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ