2023-10-19 11:38:56
ማስታወቂያ
~
በጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ህክምና ኮሌጅ በ 2016 ዓ.ል የትምህርት ዘመን ህክምና /Medicine/ ትምህርት ለመማር ማመልከት ለምትፈልጉና ከዚህ በታች የሚስፈልጉትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የኮሌጁን ማህበራዊ ትስስር ግፆች ገብታችሁ ማየት ትችላላሁ፡፡
ለማመልከት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፤
1. በ2015 ዓ.ል በመደበኛ ትምህርት ፕሮግራም 12ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀ/ያጠናቀቀች
2.በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና፤1
ከስር ከተዘረዘሩት ክልልና ዞኖች ውጪ ያሉ ሁሉም ክልሎች -
ለወንድ 500 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው
ለሴት 475 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት
• ለአፋር ክልል፣ ለቦረና ዞን (ኦሮሚያ ክልል)፣ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ለጋምቤላ ክልል፣ ለሱማሌ ክልል፣ ለደቡብ ኦሞ ዞን ፣ ለዋግእምራ ዞን (አማራ ክልል) እና ለምእራብ ኦሞ ዞን (ደቡብ ክልል)
ለወንድ 450 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው
ለሴት 425 እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላት
3. ከ9ኛ-12ኛ ክፍል አማካይ የትራንስክሪፕት ውጤት 80% እና በላይ
ማሳሰቢያ
1. ማመልከት የሚቻለው Online ብቻ ነው
2. የማመልከቻ ጊዜ ጥቅምት 7 - ጥቅምት15, 2016 ዓ.ል 11 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው
3. ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃ የኮሌጁን Facebookpage/ ቴሌግራም ፔጅ ይጎብኙ ወይንም የኮሌጁን ሬጅስራር ቢሮ ይደውሉ፤
• ስልክ፡- 251 118 96 5125
PLEASE VISIT https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement FOR ONLINE APPLICATION. APPLICATION will be accepted only ONLINE. DO NOT COME PHYSICALLY TO THE COLLEGE.
13.6K viewsedited 08:38