Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.07K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-05-04 21:00:33 ስለ ጥንቃቄ፣ ስለ መረጋጋት፣ ስለ ማረጋገጥ፣ ... ስናወራ የቢድዐ አንጃዎችን እንለፍ፣ እንተላለፍ እያልን አድርገው የሚያስቡ ወገኖች አሉ። እንደዚያ እየመሰላቸው በአንድ በኩል "ተደመራችሁ" የሚሉ አሉ። በሌላ ማዶም "በሰላችሁ" የሚሉ አሉ። ቢድዐን አቃፊ የሆነን "መብሰል።" በዚህ መልኩ የሚመጡት ሁለቱም ልክ አይደሉም።
እርግጥ ነው ሰው ከእድሜም፣ ከልምድም፣ ከእውቀትም የሆነች ያክል በጨመረ ቁጥር መብሰል ሊኖረው ይገባል። መብሰል እንዲኖረውም መጣር አለበት። አካሄዱ ላይ መታረም ያለበት ነገር እንዳለ ካስተዋለም "ካፈርኩ አይመልሰኝ" ማለት ለማንም አይጠቅምም።
የሆነ ሆኖ በመብሰል ስም በሺርክና ቢድዐ ላይ መለሳለስ አይገባም። ቢድዐ ላይ በመጠንከር እና ለሱና በመቆርቆር ስም እንደ ተናካሽ ውሻ ያለፈ ያገደመው ላይ ሁሉ ልንጮህም አይገባም። አካሄዳችንን እንፈትሽ። መታረም ያለበት ካለ የሰዎች ሃሳብ ሳያስጨንቀን እናስተካክል። የትኩረታችን ማዕከል ህዝብ ይሁን። ሰፊውን ወገናችንን መጥቀም። ከሺርክና ከቢድዐ እንዲወጣ ሳያሰልሱ መስራት። ዲኑን እንዲገነዘብ መረባረብ። አዎ ለተሻለ ውጤት የተናጠል ጥረት ሳይሆን የጋራ ርብርብ ያስፈልጋል። ርብርቡ ካላዋጣ ወይም ከዚያ ይልቅ የጎንዮሽ መጓተትን የሚያስቀድም ከበዛ ስለማንም ሳይጨነቁ የራስን ድርሻ ለመወጣት መጣር ነው። አላህ ማስተዋሉን ያድለን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
13.9K views18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 18:03:42 አኺል ከሪም!
~
ሰለፎች ቢድዐ እና ሙብተዲዕ ላይ ብርቱዎች ነበሩ። ይህ ማለት ባልተረጋገጠ ወሬ ሰዎችን ይከሱ ነበር፣ በእውር ድንብር ተብዲዕ ያደርጉ ነበር ማለት አይደለም። ሰዎችን ከሱና ለማስወጣት አትቸኩል ስትባል አይክፋህ። የዚህ መልእክቱ ለቢድዐም ለሙብቱዲዕም ጥብቅና እንቁም የሚል አይደለም። እንደዚያ አድርገህ ብትረዳ ራስህን ነው የምትጎዳው።
ቢድዐ እና ሙብተዲዕ ላይ ጠንካራ መሆን ይገባል። ለዚህም የሰለፎችን ብርቱ ማሰጠንቀቂያዎች ማሰራጨት ሁነኛ አማራጭ ነው። ይህንን ስናደርግ ግን ሌላ መልክ ያለው ቡድንተኝነት፣ ጥላቻን መሰረት ያደረገ ፍረጃና ዘመቻ፣ የሰዎችን ንግግር ሆነ ብሎ ገልብጦ እየተረጎሙ ወከባ ማብዛት አይገባም። ይሄ ከሰለፎች አካሄድ ያፈነገጠ ግና በሰለፎች ስም እየተፈፀመ ያለ የስነ ምግባር ዝቅጠት ነው። የራሳችንን የረከሰ ስነ ምግባር ወደ ሰለፎች ከማስጠጋት መቆጠብ አለብን። ከአጥፊዎች ጥፋት ባልተናነሰ የኛ ባህሪ ራሱ ሰዎችን ከሱና እያስበረገገ ነው። መሬት ላይ ያሉ ችግሮችን ለማረም ሌላ ፅንፍ መርገጥ አያስፈልግም።
በሌላ ጫፍ ለትክክለኛው ኢስላማዊ ዐቂዳ ዋጋ የማይሰጥ፣ ሺርክና ቢድዐ የማይጎረብጠው፣ የቢድዐ አጫፋሪዎች መነካት ምቾት የሚነሳው አካል እንዳለ ይታወቃል። ይህንን ብኩን አካሄድ የምናኮላሸው ራሳችን ጤነኛ አካሄድ ሲኖረን ነው። በዙሪያው ካለ ህዝብ የተኳረፈ፣ እርስ በርስ በመዘራጠጥ የሚታወቅ፣ መስለሐና መፍሰዳ የማይገባው፣ አልፎ አልፎ ሌሎችን ለመክሰስ መረማመጃ ለማድረግ ያክል ብቻ ከሚያነሳቸው የቢድዐ አንጃዎች በበለጠ የተሻለ ለሚቀርቡት የከፋ ጥላቻ ያረገዘ፣ አብይ መታወቂያው ሃሰተኛ ክስና ፍርደ ገምድል ውንጀላ የሆነ ስብስብ የክፋት አካሄዱን በሰለፎች ስም ሲያቀርብ ያሳፍራል። እውነት ለመናገር ብዙዎቻችን ጣት ከምንሰነዝርባቸው አካላት ባልተናነሰ ወይም በባሰ ተበክለናል። ራሳችንን አንዘንጋ። መልእክቱ ለራሴም ጭምር ነው።
በመጨረሻም አደራ! ያልተፃፈ እንዳታነብ! ራስህን ነው የምትጎዳው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
16.1K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 12:41:47
ማሽቃበጥ እግር አውጥቶ ሲሄድ
~
ይህንን ቪዲዮ በተለያየ ጊዜ ሙሉውን ልሰማው ፈልጌ ደጋግሜ ሞክሬያለሁ። ወላሂ እላለሁ አንዴ እንኳን ጨርሼ ልሰማው አልቻልኩም። አሳፋሪ፣ አሸማቃቂ! የማሽቃበጥ፣ የአስጠጪነት ጥግ! ቁርኣንና ሐዲሥን ተከትለው "አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን የሚያከ ^ፍሩት አሕባሾች "መለስ ዜናዊ የጀነት ነው" እያሉ ነው። አንጀቴ ነባሩ እስልምናi
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
15.5K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 08:52:13 ሟቹ "ጌታ!"
~
ወሎ ውስጥ ነው። አንድ ቆለኛ ሙስሊምና አንድ ደገኛ ክርስቲያን ጓደኛሞች ይሆናሉ። ክርስቲያኑ ሙስሊሙን ግብዣ ጠራው። የገና በአል ነበር። ሙስሊሙ ሲመጣ ምግቡ፣ መጠጡ፣ ሁሉ ነገር ተትረፍርፏል። ሰዎቹ ፌሽታ በፌሽታ፣ ፈንጠዝያ በፈንጠዝያ ሆነዋል።
·
* ሙስሊሙ:– "ድግሱ ምንን ምክንያት በማድረግ ነው?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተወልዶ ነው" አሉት።
·
ለሙስሊሙ ይሄ አስደንጋጭ ነበር። ጌታ ይወለዳል?! ግን ከሰው ቤት ነው ያለው ምን ይላል? "ህምምም" ብሎ የሆዱብ በሆዱ አድርጎ ዝም ይላል። ይህን ጉድ አይቶ ተመለሰ።
·
ሌላ ጊዜ ተጠራ። ጥምቀት ነበር። ሲመጣ ድግሱ አሁንም እንደባለፈው የደመቀ ነው። ሰዎቹም ደስታ በደስታ ናቸው።

* "እሄስ በአል ምንድን ነው ምክንያቱ?" ብሎ ጠየቀ።
– "ጌታ ተጠምቆ ነው" አሉት። ዘንድሮ ጉድ ተአምር እያየ ነው። እንዲያም ነው፤ እንዲህም ነው ሳይል ወደ ቤቱ ተመለሰ።
·
አሁንም ተጠራ። ስቅለት ነበር። ሲመጣ ከወትሮው የተለየ ነገር አየ። ሰዎቹ የባለፈው አይነት ደስታ አይታይባቸውም። አዝነዋል። በባዶ እግር ይሄዳሉ። የሚበሉት ንፍሮ ነው። ግንባራቸውን በሳር መሳይ ነገር አስረዋል። ምን ጉድ ነው?! ቆለኛው ግራ ገብቶታል።
·
* "ምንድን ነው የሆናችሁት?" አላቸው።
– "ጌታ ሞቶ ነው" አሉት።

* "ያ ባለፈው የተወለደው?" ሲል ጠየቀ።
– "አዎ" አሉት።
·
ከዚያ ምን ቢል ጥሩ ነው:–
"እኔኮ ቀድሞም ፌሽታ ስታበዙ እንደማያድግ አውቄያለሁ!!"

የታሪኩ ምንጭ አንድ የደሴ ክርስቲያን ነው።

መወለድ፣ ማደግ፣ መሞት ለፈጣሪ የማይመጥኑ የደካማ ፍጡሮች መታወቂያ ናቸው። እባካችሁ ያገሬ ሰዎች ቆም ብላችሁ አስቡ። "ፍፁም ሰው፣ ፍፁም አምላክ" እያሉ "ተጨፈኑ እናሙኛችሁ" ሲሉ እጅ አትስጡ። "ሁሉን ምርምሩ። መልካሙን ያዙ።" በአባቶች የውርስ ጋቢ ተጠቅልላችሁ፣ በይሉኝታ ጆሯችሁን ደፍናችሁ፣ በምስጢረ ሥላሴ ትብታብ ታስራችሁ እንጂ ህሊናችሁን ፋታ ሰጥታችሁ በእርጋታ ብታዳምጡት የሚነግራችሁ ሐቅ አለ።
"ዝግ ብሎማ ያሰበ እንደሁ ይነግርሀል አንዳች እውነት" ይላል ገጣሚው።
·
ዳሰሳ ከማርቆስ ወንጌል ምዕ. 12 ቁ 29 እስከ 34።
----------
"ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። #ከትእዛዛቱ_ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ #ጌታ_አምላካችን #አንድ_ጌታ ነው፥" (የማርቆስ ወንጌል 12:29)
·
ማነው ይህን ያለው? እየሱስ እራሱ!! "ጌታ አምላካችን" ማለቱን አስምርበት። እየሱስ ፍጡር እንጂ ጌታ እንዳልሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ጥቅስ ነው። ይሄ ቀዳሚ ትእዛዝ ግን በክርስቲያኖች ተገፍቷል። እንቀጥል።

"አንተም በፍጹም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ በፍጹምም አሳብህ በፍጹምም ኃይልህ ጌታ አምላክህን ውደድ የምትል ናት። ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት።" (የማርቆስ ወንጌል 12:30)
·
ልብ በል! በዚህ መልኩ "ጌታህን ውደድ" እያለ የሚያስተምረው እየሱስ እራሱ ነው። ይህም እሱ አስተማሪ እንጂ ጌታ እንዳልሆነ የሚያሳይ ነው። እንቀጥል።

"ሁለተኛይቱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።

ጻፊውም። መልካም ነው፥ መምህር ሆይ፤ #አንድ_ነው። #ከእርሱም_በቀር_ሌላ_የለም ብለህ በእውነት ተናገርህ፤" (ማርቆስ 12:31–32)

እያስተዋልክ ነው?!
እውነት የምትፈልግ ከሆንክ "አምላክ አንድ ነው። ከርሱ በቀር ምንም የለም" ብለህ በልብህ ዝከር። በምላስህ አስተጋባ። በተግባር ኑር። ይሄ በኢስላም "ላ ኢላሀ ኢለላህ" ("ከአላህ በስተቀር እውነተኛ አምላክ የለም") ከሚለው ምስክርነት ጋር መሳ ነው። እንቀጥል።

"በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኃይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው አለው።" (ማርቆስ 12:33)

ይህን ነው የምልህ። ስላሴ፣ ቅብጥርሴ የሚባለውን ወደ ኋላህ አሽቀንጥረህ ጣልና ለመፅሐፋዊ መልእክቱ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም አእምሮህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኃይልህ እደር። ሥላሴ ልብ ወለድ እንጂ እውነታ አይደለም። ሥላሴ ጤነኛ ጭንቅላት የማይፈታው እንቆቅልሽ እንጂ ምክንያታዊ አይደለም። "ያልገባህ መንፈስ ቅዱስ ስላላደረብህ ነው" እያሉ አይሸውዱህ። ይሄ ምእመኑ እንዳይመረምር የሚያስተኙበት የእንቅልፍ ክኒን ነው። በክኒኑ እራሳቸውን ያስተኙበት። አንተ ግን ንቃ። ይህን ስታደርግ፣ ወደ አእምሮህ ስትመለስ "ለመንግስተ ሰማያት" ትቀርባለህ። አብረን እናንብብ።

"ኢየሱስም በአእምሮ እንደ መለሰ አይቶ። አንተ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅህ አይደለህም አለው። ከዚህም በኋላ ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።" (ማርቆስ 12:34)

(ኢብኑ ሙነወር፣ የካቲት 11/2011)
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
14.4K views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 18:58:16 ከደቂቃዎች በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ።
12.7K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 16:44:54 ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:-
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 451፣ كتاب الجهاد
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
13.0K views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 11:59:44 ለእየሱስ ባሪያዎች!
~
የመሲህ ባሮች ሆይ - አንድ ጥያቄ አለን
የተረዳው ካለ - መልሱን እንሻለን
ጌታ ግፍ አቅቶት - ሰዎች ከገደሉት
አለቀ አከተመ - የታል አምላክነት?!
ሰዎች የሰሩትን - በሱ ላይ ሲያደርሱ
ጌታ ግብራቸውን - ፈቅዶ ነው በራሱ?
እንዲያ ከሆነማ - ምንኛ ታደሉ?!
ፍቅሩን ይቸራሉ - ፈቃዱን ሲሞሉ።
ባደረሱት ሁሉ - አልፎ ከተከፋ
እንግዲህ ምን ይባል?
ሀይሉ ከኮሰሰ - ሀይላቸው ከሰፋ?!
ግን እንጠይቃለን - ለመልስ አትንፈጉ
ማለባበስ ይቅር - ይመለስ በወጉ
ፈጣሪዋን አጥታ - ዐለም ስትዋትት
ሰው ወደ ማን ነበር - የሚያስበው ፀሎት?
ፍጡር ፈጣሪውን - ካፈር ሲያደባየው
ሰባቱን ሰማያት - ማነበር ያቆየው?
ምስማር ተቸንክሮ - ሲያሸልብ ፈጣሪ
ዓለም ቀርታ ነበር - ያለ አስተናባሪ?
የሰማይ መላእክት - ምንኛ ለገሙ?!
እጁ ተቸንክሮ - ዋይታውን ሲሰሙ?
እንጨቱም ታምር ነው - አቅሙ መቋቋሙ
አምላክ ያክል ነገር - ችሎ መሸከሙ
ስለቱስ ጭቃኔው - ብረቱ ምስማሩ
አካሉን ሰንጥቆ - ስቃይ ማሳደሩ
ጉድ በሉ እሄን ጌታ - በአይሁድ የሚረታ
ማጅራቱን ታንቆ - ታስሮ የሚመታ
ኋላስ ራሱ ነቃ - ከሞት አንሰራራ
ወይስ ጌታ አገኘ - ህይወት የሚዘራ?!
ጉድ በሉ ለቀብር - ጌታ አቅፎ ለያዘ
የባሰም ሆድ አለ - አምላክ ያረገዘ
ዘጠኝ ወር ታሽጎ - ሲኖር በጨለማ
ሐይድ እየተጋተ - ደም እየተጠማ
ብልት ቀዶ ወጣ - አቡሻ ህፃኑ
አፉን ለጡት ከፍቶ - አቤት ማሳዘኑ!
አስቡ እሄን አምላክ - ሲጠጣ ሲበላ
ከዚያም ያስገባውን - ሲያስወጣ በሌላ
ጌታዬ ከፍ አለ - ከነሳራ ቅጥፈት
ሁሉም ይጠየቃል - ለቀባጠረበት
የመስቀል ባሮች ሆይ! - ግራ ገባኝ እኔ
ያሽቀነጠረው ሰው - ፅድቅ ነው ኩነኔ
ማቃጠል ሰባብሮ - ፈቃጁን ጨምሮ
ህሊና ከዚህ ውጭ - ይፈርዳል አምርሮ?
አምላክ አቅም አንሶት - ለተጠፈረበት
ሰብሮ እንደማቃጠል - ጭራሹን አምሎኮት?!
እውነትም እርጉም ነው - ለምንስ ይዘንጋ?
በመሳለም ሳይሆን - በእግር ይሰጥ ዋጋ!
ለተዋረደበት - ጌታህ ከነነፍሱ
አንተ ካመለክከው - የሱ ነህ የነሱ?
‘ጌታን ስላዘለ’ - ከሆነ አክብሮቱ
አስተዋሽ ቅርፃቅርፅ - ቢሆን እንጂ እንጨቱ
መስቀሉ ከጠፋ - ሺ ስንት አመታቱ?!
እንዲያ ከሆነማ - ሂሳቡ ቀመሩ
ለመስገድ አትቦዝን - ለየመቃብሩ
ያስታውሳልና - ነገረ ስርኣቱ
"ጌታህ" ካፈር በታች - ለነበረበቱ።
የመሲህ ባሪያ ሆይ! - ንቃ ተረጋጋ
ይሄ ነው እውነታው - ካ'ልፋ እስከ ኦሜጋ፡፡

የኢብኑል ቀዪም አልጀውዚያህ “አዑባደል መሲሒ ለና ሱኣሉን” ድንቅ ግጥም ግርድፍ ትርጉም፡፡ ግጥሙን “ኢጋሠቱል ለህፋን ኪታክ ገፅ: 2/290 ላይ ያገኙታል፡፡ የግጥሙን አሪፍ የቪዲዮ ቅንብር ደግሞ ከፍቺው ጋር ከስር ይመልከቱ፡፡

ኢብኑ ሙነወር
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
16.8K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 22:16:31
ቤተሰብ በእጅጉ ተጨንቀዋል #ሼር በማድረግ ተባበሩን

ይህቺ ከላይ በፎቶ ያያቿት ልጅ ዛሬ ሚክሲኮ አደባባይ አከባቢ ከቀኑ 7:30 ገደማ ከእናቱዋ እያለች በእናቷ አምልጣት ጠፍታለች ስሟ ሂዳያ በድሩ ትባላለች በሰኣቱ የለበሰችው ልብስ ከስር ቀላ ያለ ከላይ ነጭ ቀሚስና ሂጃብ አድርጋለች።

የሚያሳዝነው ሌላኛው ደግሞ እናቷም ከጠፋችባት ቦኃላ ደንግጣ ስልኳን ዘግታ ወደ ቤት አልተመለሰችም ቤተሰብ በጣም በጭንቀት ውስጥ ነው።

#ሼር በማድረግም በመፖሰትም በዱኣም ተባበሩኝ ቤተሰብ ናት
የአባቷ ስልክ በድሩ መሐመድ 0912409463
አ/ወሃብ መሐመድ 0928021661
22.0K views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 21:45:20 ሙሐመድ ሸምሰዲንን "ሙጀዲድ"፣ "ሸይኹል ኢስላም" እያለ የሚገልፅ ሰው በርግጠኝነት የነዚህን ቃላት ሐቂቃ እና ጥልቀት አያውቅም። እነዚህ ቃላት ለሙሐመድ ሸምሰዲን ብጤ ቀርቶ ከሱ በብዙ መጠን ለሚርቁ ዑለማዎች ራሱ በዘፈቀደ የሚሰጡ አይደለም። ጅህልናችንን አገር እንዲያይልን ባናውጅ መልካም ነው። ለሚያስተውል ሰው ከኢስላም ሊቃውንት ውስጥ እነዚህ ማእረጎች ለጥቂቶች መዋላቸው የሚሰጠው ጥቆማ አለ። ሙሐመድ ሸምሰዲን ሐቅ ላይ ነው ቢባል እንኳ ፈፅሞ ለነዚህ ማእረጎች የሚቀርብ ሰው አይደለም።
ለማንኛውም የሙሐመድ ሸምሰዲንን እና ዐብደላህ አልኹለይፊን ስራዎች እየተከታተላችሁ ያላችሁ ወንድሞች በሁለቱ አካላት ላይ የሚሰጡ ምላሾችንም ብትመለከቱ መልካም ነው። አንዳንዴ ጠንካራ የመሰለን አቋም ብዙ መረጣና ሸፍጥ የተዘነቀበት ይሆናል። ሁለቱንም ለማታውቁ ግን ይቅሩባችሁ ነው የምለው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
13.2K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-02 18:30:27 ከመግሪብ በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ።
የሚተላለፍበት የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
14.2K views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ