Get Mystery Box with random crypto!

ሙሐመድ ሸምሰዲንን 'ሙጀዲድ'፣ 'ሸይኹል ኢስላም' እያለ የሚገልፅ ሰው በርግጠኝነት የነዚህን ቃላት | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ሙሐመድ ሸምሰዲንን "ሙጀዲድ"፣ "ሸይኹል ኢስላም" እያለ የሚገልፅ ሰው በርግጠኝነት የነዚህን ቃላት ሐቂቃ እና ጥልቀት አያውቅም። እነዚህ ቃላት ለሙሐመድ ሸምሰዲን ብጤ ቀርቶ ከሱ በብዙ መጠን ለሚርቁ ዑለማዎች ራሱ በዘፈቀደ የሚሰጡ አይደለም። ጅህልናችንን አገር እንዲያይልን ባናውጅ መልካም ነው። ለሚያስተውል ሰው ከኢስላም ሊቃውንት ውስጥ እነዚህ ማእረጎች ለጥቂቶች መዋላቸው የሚሰጠው ጥቆማ አለ። ሙሐመድ ሸምሰዲን ሐቅ ላይ ነው ቢባል እንኳ ፈፅሞ ለነዚህ ማእረጎች የሚቀርብ ሰው አይደለም።
ለማንኛውም የሙሐመድ ሸምሰዲንን እና ዐብደላህ አልኹለይፊን ስራዎች እየተከታተላችሁ ያላችሁ ወንድሞች በሁለቱ አካላት ላይ የሚሰጡ ምላሾችንም ብትመለከቱ መልካም ነው። አንዳንዴ ጠንካራ የመሰለን አቋም ብዙ መረጣና ሸፍጥ የተዘነቀበት ይሆናል። ሁለቱንም ለማታውቁ ግን ይቅሩባችሁ ነው የምለው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor