Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.07K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-28 18:20:01 ለበይክ አላሁመ ለበይክ
~
ሐጅ የኢስላም ልዩ መስህብ የሚሰተዋልበት፣ ድንቅ የአላህ ተዐምር የሚታይበት፣ የተውሒድ ነፀብራቅ ጎልቶ የሚነግስበት፣ ባእድ አምልኮ ከፍ ባለ ድምፅ ባደባባይ የሚወገዝበት ድንቅ ስርአት ነው። ሴት ወንዱ፣ ነጭ ጥቁሩ፣ መሪው ተመሪው በተመሳሳይ ቦታ እኩል ለአላህ የሚሰለፍበት ትንግርት። ሐጅ - አምስተኛው የኢስላም ምሰሶ።
በሐጅ "በሰዎችም ውስጥ በሀጅ ትእዛዝ ተጣራ" ለሚለው የአላህ ጥሪ “ለበይክ አላሁመ ለበይክ፣ ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ፣…” /አቤት ጌታችን ሆይ አቤት፣ አቤት ጥሪህን ተቀብለን መጥተናል/” እያሉ መልስ በመስጠት ሚሊዮኖች ይተማሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ “ከአላህ ሀገራት ሁሉ ይበልጥ አላህ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ። ከአላህ ሀገራት ሁሉም እኔ ዘንድ የተወደድሽ ነሽ። ህዝቦችሽ ካንቺ ባያስወጡኝ ኖሮ አልወጣም ነበር” የሚለውን የነብዩን ﷺ የቁጭት ንግግር፣ አሜኬላ የበዛበት ህይወታቸውን ልበዎ በሀዘን እየተከፈለ ያስታውሳሉ።

* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ አስራ አራት ክፍለ-ዘመናት ወደ ኋላ አጠንጥነው የተውሒድ ጮራ ሲፈነጥቅ በአይነ-ህሊናዎ ይመለከታሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የመካ ሙሽ - ሪኮችን ለከት የለሽ ጭካኔና የነዚያን ፈርጥ የሆኑ ሰሐቦች ከብረት የጠነከረ ፅናት እያሰቡ በትዝታ ይነጉዳሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የነ ቢላልን ስቃይ፣ የነ ሱመያን የጣር ድምፅ አይነዎ እንባ እያቀረረ በሰመመን ያያሉ። ልበዎ በቁጭት እየደማ ይሰማሉ።
* ከዚያ ጭው ካለ በረሃ የአላህ የመጀመሪያ ቤት አለ - የሙስሊሞች ቂብላ፣ ከአለም ሁሉ ምርጡ ቦታ፣ መካ።
إِنَّ أَوَّلَ بَيْتٍ وُضِعَ لِلنَّاسِ لَلَّذِي بِبَكَّةَ مُبَارَكًا وَهُدًى لِلْعَالَمِينَ (96) فِيهِ آيَاتٌ بَيِّنَاتٌ مَقَامُ إِبْرَاهِيمَ وَمَنْ دَخَلَهُ كَانَ آمِنًا
"በርግጥም ለሰው ዘር (መፀለያ) ሆኖ መጀመሪያ (ምድር ላይ) የተኖረው ቤት ያ በበካህ (በመካ) ያለው የተባረከና ለዓለማት ሁሉ መመሪያ የሆነው ነው። በውስጡ (እንደ) የኢብራሒም መቆሚያ (ያሉ) ግልፅ የኾኑ ተዓምራቶች አልሉ። ወደ ውስጡ የገባም ሰው ደህንነቱ የተጠበቀ ሆኗል።" [ኣሊ ዒምራን፡ 96]

- መስጂደል ሐራም መጤው ካገሬው እኩል የሚሆንበት ተአምራዊ ቦታ። የተውሒድ ቦታ፣ የእዝነት ቦታ። የኢብራሂም፣ የሐጀር፣ የኢስማዒል ትዝታ።
- መስጂደል ሐራም በረከት የበዛበት፣ ሰላም የሰፈነበት፣ እዝነት የነገሰበት፣ ተውሒድ የፈነጠቀበት ቅዱስ ቦታ።
- መስጂደ ልሐራም ልቦች ዘወትር የሚናፍቁት፣ አይኖች አይተውት የማይጠግቡት፣ ያላዩት ሊያዩት የሚቋምጡት ድንቅ ቦታ።
- መስጂደል ሐራም! “የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም” የሚለው ሀገርኛ ብሂል ፉርሽ የሚሆንበት ልዩ መስህብ። ለካስ ይናፍቃል! ደካማ አዛውንቶች በሽተኞች ሳይቀሩ ህመም ድካማቸውን ረስተው፣ ስቃይ እንግልቱን ዘንግተው፣ ባላዩት ሀገር ናፍቆት ተብሰክስከው፣ እልፍ አእላፍ ማይሎችን አቋርጠው ይተማሉ።
وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَاهِيمَ مَكَانَ الْبَيْتِ أَنْ لَا تُشْرِكْ بِي شَيْئًا وَطَهِّرْ بَيْتِيَ لِلطَّائِفِينَ وَالْقَائِمِينَ وَالرُّكَّعِ السُّجُودِ
"ለኢብራሂምም የቤቱን (የካዕባን) ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ “በኔ ምንንም አታጋራ፣ ቤቴንም ለሚዞሩትና ለሚቆሙበት ሩኩዕ ሱጁድ ለሚያበዙት ንፁህ አድርግላቸው” (ባልነው ጊዜ አስታውስ)።" [አልሐጅ፡ 26]
ከዕባ፣ ሐጀረል አስወድ፣ መቃም ኢብራሂም፣ ሶፋና መርዋ፣ ሚና፣ ዐረፋ፣ ሙዝደሊፋ፣… የሙስሊሞችን ቀልብ የሚማርኩ ልዩ የዒባዳ አውድማዎች ናቸው። ተልቢያ፣ ጦዋፍ፣ ሶላት፣ ዱዐ፣ እርድ፣ የጠጠር ውርወራ፣… ለፈፀማቸው ቀርቶ ለተነገረው የሚያጓጉ ሐጅ ላይ የሚፈፀሙ፤ ተቅዋን የሚያላብሱ የዚያኛው ዓለም ስንቆች ናቸው። (ذَلِكَ وَمَنْ يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِنْ تَقْوَى الْقُلُوبِ)
ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ አላህ አድሎት የተዋጣለት ሐጅ ያደረገ እናቱ ስትወልደው እንደነበረው እንደ ህፃንነቱ ከወንጀል ሙሉ በሙሉ እንደሚፀዳ ነው መልእክተኛው ﷺ ያመላከቱት። በሐጅ ልቦች በኢማን ይታደሳሉ፣ አማኞች ከወንድሞቻቸው ጋር ይተዋወቃሉ፣ ደካሞች ይታገዛሉ፣ ሙስሊሞች ከቅዱሱ ስፋራ፣ ከበረሃው፣ ከሐጁ ስርአት፣ ከተዳሚው ሁኔታ፣ ከዚያ የሚሊዮኖች ስብሰባ ብዙ ተፈኩር ይወስዳሉ።
አላህ አድሎት የሐጅ ስነ-ስርኣት ላይ ለተካፈለ ሰው ልብሳቸው የበሰበሰ፣ ሰውነታቸው የኮሰሰ፣ ኑሮ ያጎሳቆላቸው ስንት አይነት ሰዎችን ከተለያዩ የአለም አፅናፋት ታድመው ይመለከታል። አንዳንዶቹ ለዘመናት አጠራቅመው ለዚህ ስኬት እንደበቁ ሲቃ እየተናነቃቸው ይናገራሉ። በተሽከርካሪ ወንበር የሚገፉ፣ በጀርባ የታዘሉ አዛውንቶችን ሲመለከቱ፣ አቅሙም ጤናውም ተሟልቶ ከሐጅ ስለቀረው ወገን በእጅጉ ያዝናሉ። ሐጅ የወጀበባችሁ ወገኖቼ ሆይ! ጤናን አቅምን ያደላችሁ ጌታ፣ ሐጅን ግዴታ አድርጎባችኋል። ወንድሞቼ እህቶቼ፣ አባቶቼ እናቶቼ ሆይ! ለአላማ እንደተፈጠራችሁ አትዘንጉ። የተሰጣችሁ ገንዘብ ያንን አላማ ማሳኪያ እንጂ መጎረሪያም መባከኛም አይደለም። ሐጁን ብትፈፅሙት ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው። ወንጀላችሁ ይረግፋል፣ ልባችሁ ይፀዳል፤ የዒባዳ ወኔያችሁ ይነሳሳል። እመኑኝ አንዴ ቆርጣችሁ ከፈፀማችሁት በያመቱ ገና ጊዜው ሲቃረብ ነው ልባችሁ የሚቆመው። “ወዴት” እንዳትሉኝ። ወላሂ ስንቶች ናቸው ሐጅ አጠናቀው መካን ሲለቁ፣ በእንባ የሚታጠቡት! ባትፈፅሙትስ ማነው የሚጎዳው? በርግጠኝነት አላህ ምንም አይቀርበትም! መቼስ ከሚታረደው እርድ አይደርሰው ነገር! ያበላል እንጂ አይበላምና። ከፍጡር ሁሉ የተብቃቃ ጌታ ነውና።
وَلِلَّهِ عَلَى النَّاسِ حِجُّ الْبَيْتِ مَنِ اسْتَطَاعَ إِلَيْهِ سَبِيلًا وَمَنْ كَفَرَ فَإِنَّ اللَّهَ غَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
"ለአላህም በሰዎች ላይ ወደርሱ መሄድን በቻለ ሁሉ ላይ ቤቱን መጎብኘት ግዴታ አለባቸው። የካደም ሰው አላህ ከዓለማት ሁሉ የተብቃቃ ነው።" [ኣሊ ዒምራን: 97]
ዱዓቶች ሆይ ሰዎችን ቀስቅሱ። አላህ የጣለባችሁን ሀላፊነት አድርሱ። ተሳክቶላችሁ በናንተ ሰበብ አንድ ሰው ለሐጅ ቆርጦ ቢነሳ የሚኖራችሁን አጅር አስታውሱ። ወገን ወደ ግራም ወደ ቀኝም ተመልከት። ከራሳችን፣ ከቤተሰብ፣ ከጎረቤት ብዙ ሐጅ ያላደረጉትን ፍቀድ። ዘንድሮ ባይደርስ ለቀጣይ አስታውስ። "አስታውስ ማስታወሱ አማኞችን ይጠቅማልና።" [አዛሪያት፡ 55]
ባይሆን አደራ!
ለሐጅ ቆርጠው ከተነሱ፡- በሚገባ ይዘጋጁ። ስለሐጅ ይጠይቁ፣ ይወቁ፣ ያንብቡ፣ የሚያነቡትም ይያዙ። ከተቻለም ቀድሞ ሐጅ ያደረገ የዲን ግንዛቤ ያለው ሰው ጓደኛ ማድረገዎን አይርሱ።
"ወደ ኸይር ያመላከተ (ኸይሩን) እንደሚሰራው ሰው ነው (አጅሩ አለው)" ይላሉ ነብዩ ﷺ።

ለበይክ አላሁመ ለበይክ
ለበይከ ላሸሪከ ለከ ለበይክ
ኢነል ሐምደ
ወኒዕመተ
ለከ ወልሙልክ
ላሸሪከ ለክ!
.
ያ ረሕማኑ ቤትህን ለመጎብኘት አንተ ወፍቀን።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጳጉሜ 3/2006)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
15.2K views15:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 18:19:57
12.9K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-28 08:42:29 የ 3ኛ ወገን አስገዳጅ መድንዎን አድሰዋል? ካደሱ ጥሩ ካላደሱ አሁኑኑ ያድሱ!!
√ ለማደስ የሚያስፈልጉ ሰነዶች
የባለቤትነት መታወቂያ ወይም ሊብሬ ሲሆን ሊብሬ የያዘ ማንኛውም ሰው ለያዘው ተሽከርካሪ የኢንሹራንስ እድሳትና አዲስ ኢንሹራንስ መግባት ይችላል።

ልብ ይበሉ የ3ኛ ወገን አስገዳጅ መድን ባጋጣሚ ሳያድሱ 1 ቀን ቢያልፍ መኪናዎትን አቁመው በሌላ ተሽከርካሪ ነው ሄደዉ ማደስ የሚችሉት። ያን ሳያደርጉ ቢያዙ
- በመጀመሪያ ወደ ጣቢያ ይወሰዳሉ።
- መኪናዎት ይታሰራል።
- ከዛ ኢንሹራንስ አድሰው ሲመጡ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣሉ።
- ከዛ ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
ከዚህ ሁሉ እንግልት እና ውጣ ውረድ አስቀድመው ይጠንቀቁ!!

በተጨማሪም የቦሎ ወይም አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ለማድረግ የሚያስፈልገው
1 ሊብሬ
2 በታወቀ የመመርመሪያ ድርጅት አስመርምሮ የሚሰጠውን የምስክር ወረቀት መያዝ
3 ፖስታ ቤት እና ባንክ የመንገድ ፈንድ መክፈል
4 የባለቤትነት ሊብሬ እና የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ኮፒና ዋናውን መያዝ እንዲሁም ለንግድ ተሽከርካሪዎች ክሊራንስ መያዝ
5 እነዚህን ስታሟሉ የተሽከሪው ፋይል ወዳለበት የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ በመቅረብ ቦሎ ማደስ ይቻላል

Driving in ADDIS ፔጅ
13.7K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 20:03:03 ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:-
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ (በ pdf ) በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 448፣ كتاب الحج
* የሚሰጥበት ቦታ፦ አሸዋ ሜዳ፣ መስጂደል ዋሊደይን
* የሚሰጥበት ጊዜ:- ሐሙስ እና ጁሙዐ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
13.8K views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 17:33:54
ምሰሶው ራሱ የሆነ ወሃቢ ነገር ነውi ምርቃናቸውን አናጠባቸውኮ!
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
13.0K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-27 17:17:53 ብንሞት ምን የማይቋረጥ መልካም ስራ አለን?
~
ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ:–

"የሰው ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል። ከሶስት ሲቀር።
① ቀጣይነት ያለው ሶደቃ፣
② ወይም ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት፣
③ ወይ ደግሞ ዱዓ የሚያደርግለት ጥሩ ልጅ።" [ሙስሊም]

የቱ ጋር አለህ? የቱ ጋር አለሽ?
① ከቻልን አጅሩ የማይቋረጥ ህዝብ የሚጠቅም ሶደቃ ጥለን እንለፍ።
② ወይ ደግሞ እውቀትን በማሰራጨት ላይ ድርሻ ይኑረን። (ይህም በሁለት መልኩ ሊሆን ይችላል። ተምሮ በማስተማር። ያወቁትን በማካፈል። ወይም የዑለማዎችን እውቀት በማሰራጨት።)
③ ወይ ደግሞ ልጆቻችንን በጥሩ ሁኔታ ኮትኩተን እናሳድግ።
ከሁሉም አለመኖር ግን አሳዛኝ ብክነት ነው። ከነገ በፊት ዛሬ እንመልከት። ከነዚህ መስኮች ውስጥ የቱ ላይ አለን?
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
13.1K views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-26 09:11:49 ማስታወቂያ
~
ተቋርጦ የነበረው በሑዘይፋ መስጂድ ዘወትር እሁድ ረፋድ ላይ የሚሰጠው ሳምንታዊ የደርስ ፕሮግራም የፊታችን እሁድ ይጀምሯል ፣ ኢንሻአላህ። መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩን።
20.4K views06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 19:00:57 ከደቂቃዎች በኋላ የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል ኢንሻአላህ።
16.0K views16:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-25 09:25:52 ሶላት የተወ ሰው የሚኖረውን ብይን (ሑክም) በተመለከተ ከጥንት ጀምሮ በዑለማእ መካከል የሃሳብ ልዩነት አለ።
1፦ ከፊሎቹ ከኢስላም ይወጣል ሲሉ
2፦ ሌሎቹ ደግሞ ወንጀለኛ ቢሆንም ከኢስላም አይወጣም ብለዋል።
በሁለቱም አቋሞች በኩል ታላላቅ ዑለማኦች አሉ። አቅሙ ያለው ሰው መረጃዎቹን ፈትሾና አበጥሮ ከሁለቱ አቋሞች ውስጥ ሚዛን የሚደፋውን መውሰድ ይጠበቅበታል። ከዚህ አልፎ ጉዳዩን በሌላኛው በኩል ያሉትን ዓሊሞች በቢድዐ ለመወንጀል ማዋል ግን ተገቢ አይደለም። ይሁን እንጂ አንዳንዶች "ሶላት የተወ ሰው ከኢስላም አይወጣም" የሚሉ ዓሊሞችን በኢርጃእ ሲወነጅሉ ይታያሉ። ይሄ የተሳሳተ አካሄድ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
12.6K viewsedited  06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-24 07:01:01 በተለይ ወደ ዳዕዋ የቀረባችሁ ወንድሞች ክፉ ምሳሌ እንዳትሆኑ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላሀ

        t.me/Darutewhide
14.1K views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ