Get Mystery Box with random crypto!

የ 3ኛ ወገን አስገዳጅ መድንዎን አድሰዋል? ካደሱ ጥሩ ካላደሱ አሁኑኑ ያድሱ!! √ ለማደስ የሚ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የ 3ኛ ወገን አስገዳጅ መድንዎን አድሰዋል? ካደሱ ጥሩ ካላደሱ አሁኑኑ ያድሱ!!
√ ለማደስ የሚያስፈልጉ ሰነዶች
የባለቤትነት መታወቂያ ወይም ሊብሬ ሲሆን ሊብሬ የያዘ ማንኛውም ሰው ለያዘው ተሽከርካሪ የኢንሹራንስ እድሳትና አዲስ ኢንሹራንስ መግባት ይችላል።

ልብ ይበሉ የ3ኛ ወገን አስገዳጅ መድን ባጋጣሚ ሳያድሱ 1 ቀን ቢያልፍ መኪናዎትን አቁመው በሌላ ተሽከርካሪ ነው ሄደዉ ማደስ የሚችሉት። ያን ሳያደርጉ ቢያዙ
- በመጀመሪያ ወደ ጣቢያ ይወሰዳሉ።
- መኪናዎት ይታሰራል።
- ከዛ ኢንሹራንስ አድሰው ሲመጡ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣሉ።
- ከዛ ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።
ከዚህ ሁሉ እንግልት እና ውጣ ውረድ አስቀድመው ይጠንቀቁ!!

በተጨማሪም የቦሎ ወይም አመታዊ የተሽከርካሪ ምርመራ ለማድረግ የሚያስፈልገው
1 ሊብሬ
2 በታወቀ የመመርመሪያ ድርጅት አስመርምሮ የሚሰጠውን የምስክር ወረቀት መያዝ
3 ፖስታ ቤት እና ባንክ የመንገድ ፈንድ መክፈል
4 የባለቤትነት ሊብሬ እና የቀበሌ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ኮፒና ዋናውን መያዝ እንዲሁም ለንግድ ተሽከርካሪዎች ክሊራንስ መያዝ
5 እነዚህን ስታሟሉ የተሽከሪው ፋይል ወዳለበት የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ በመቅረብ ቦሎ ማደስ ይቻላል

Driving in ADDIS ፔጅ