Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.07K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2024-04-06 20:16:40 ትላንት ማታ በረመዷን 27 ጎንደር ቀበሌ 8 አዲስ ዓለም በሚባለው ሰፈር ሰይድ በሺር የተባለ አንድ ወንድማችን ተገድሏል። አላህ የጀነት ያድርገው። ሌላ ደግሞ ቀበሌ 10 በአታ አካባቢ አንድ ወንድማችንን ቤት ሰብረው ገብተው አግተው ሲወስዱት አምልጧቸው ከሰው ግቢ ሲገባ በግርግሩ መሀል አንድ ሰው ተጎድቷል።
ባለፈው ሰሜን ሸዋ ላይ በአካባቢው የተወሰኑ ሙስሊሞችን የአዲሱ የመጅሊስ መዋቅር አባል በመሆናቸው ብቻ የብልፅግና ደጋፊ ተብለው ተገድለዋል።
የፋኖ ትግል አንዱ ዘርፍ ሙስሊሞችን ማሳደድ ሆኗል። የሚደንቀው ቡድኑ በጭፍን ከማስተባበል ውጭ ኃላፊነት የሚሰማው ለምን የሚል አካል የሌለው መሆኑ ነው። ጥፋቱን ለማረም ከመሞከር ይልቅ "የወለጋው ሲሆን... " እያለ አፍ ማስያዝን ቁም ነገር አድርጎታል። ዲስፕሊን የማያውቅ፣ ህዝብን በሃይማኖት ለይቶ የሚያጠቃ፣ ጉልበቱን አቅመ ደካሞች ላይ የሚያሳይ ትግል በርግጠኝነት የትም አይደርስም። ለነዚህ አካላት ድጋፍ የምታደርጉ ወገኖች አሁንስ አትነቁም?!
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
12.6K viewsedited  17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 17:50:34
https://t.me/OkazHijab
12.8K views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 15:38:19 يَدَعونَ قولَ رسولِ الله صلَّى الله عليه وسلَّمَ ويَقولون: قال فُلانٌ! ... وقال اللهُ تعالَى: {أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ}
"የአላህ መልእክተኛን ﷺ ንግግር ትተው 'እከሌ እንዲህ አለ' ይላሉ። ... የላቀው አላህ 'አላህን ታዘዙ። መልእክተኛውንም ታዘዙ ብሏል።" [አልሙግኒ፣ ኢብኑ ቁዳማ]
ከሐሰኑል በስሪይ ግን ተገኝቷል። ቢሆንም የአሕመድ ንግግር ለዚህም ምላሽ ይሆናል። የታቢዒይ ንግግር ከሐዲሥ ጋር ቀርቶ ከሶሐባ ንግግር ጋርም ትይዩ አይቀመጥም። እዚህ ላይ ሲሆን በተለየ የሚወስዱ ከሆነ የታቢዒዩ ዐጧእ ንግግር ከፊታቸው እናቀርባለን። ከአቡ ሐኒፋም ተገኝቷል። ቢሆንም ከሐዲሥ ጋር የሚገጥመው የሌሎች ታላላቆች ንግግር ቅድሚያ ይሰጠዋል።
4.2. ደግሞም ዘካተል ፊጥር ከንብረት ዘካ (ዘካተል ማል) ይለያል።
* ዘካተል ማል ለዘካ መጠን (ኒሷብ) የደረሰ ገንዘብ ላይ ነው ግዴታ የሚሆነው። ከሰብል ምርት ውጭ ባሉት ንብረቶች ላይ ደግሞ አመት መቆየት አለበት። የሚመለከተውም ሁሉንም አይነት ንብረቶች አይደለም። ዘካተል ፊጥር ግን በቂ የእለት ጉርስ ካለ ህፃን ከአዋቂ ሳይለይ በሁሉም የቤተሰብ ቁጥር የተደነገገ ነው።
* ዘካተል ማል ንብረቱ ላይ ነው የሚያነጣጥረው። ዘካተል ፊጥር ግን ሰዎች ላይ ነው የሚያነጣጥረው። ለዚያም ነው ዘካተል ማል በንብረቱ ሂሳብ ታስቦ የሚወጣው። የንብረቱ መጠን ሲጨምር የዘካው መጠን ይጨምራል። ሲያንስ ያንሳል። ከኒሷብ ከወረደ ይቀራል። ዘካተል ፊጥር ግን ሁሉም ሰው እኩል አንድ አንድ ቁና ነው የሚያወጣው።
* ዘካተል ማል በአንፃራዊነት ሃብት ባለው ላይ ነው የተደነገገው። ዘካተል ፊጥር ግን የእለት ጉርስ ካለው ድሃውንም ይመለከታል።

5ኛ:- ዘካተል ፊጥርን በጥሬ ገንዘብ መስጠት በሶሐቦቹ ጊዜም ቢሆን ለሰጪው ቀላል፣ ተቀባዩም ላሰኘው ነገር ስለሚያውለው የተሻለ ነበር። ከመሆኑም ጋር የተደነገገውም የተገኘውም በአይነት መስጠት ነው። ጥሬ ገንዘቡን መስጠት ቢቻል ለምን አያደርጉትም ነበር?!
6ኛ፦ ለዘካተል ፊጥር የተደነገጉት ምግቦች ዋጋቸው መለያየቱም የራሱ ጥቆማ አለው። የገብስ፣ የተምር፣ የዘቢብ፣ የስንዴ፣ የአይቤ፣ ... ዋጋዎች አንዱ ከሌላው የሚለያይ ከመሆኑ ጋር ከሁሉም አይነት አንድ ቁና ነው የታዘዘው። ትኩረቱ ዋጋው ቢሆን ኖሮ ዋጋቸው በሚራራቁ ምግቦች ለሁሉም አንድ ቁና ባልተባለ ነበር። [መዓሊሙ ሱነን፣ አልኸጧቢይ]

ብዥታ፦

በሐዲሥ ለዘካተል ፊጥር የተጠቀሱት የምግብ አይነቶች ተምርና ገብስ ከመሆናቸው ጋር ኋላ ሌሎች እህሎች መካተታቸው በጥሬ ገንዘብ መስጠት እንደሚቻል ያሳያል የሚሉ አሉ። ይህም ልክ አይደለም።
1- ሲጀመር በጊዜው የነበረው አሰራር ተምርና ገብስ ላይ የተገደበ አልነበረም። ዱቄት፣ ዘቢብ፣ አይቤ በተለያዩ መረጃዎች ተጠቁመዋል።
2- በጊዜው እነዚህን ምግቦች ሲሰጡ የነበረው በዘመኑ ምግቦቻቸው እነዚህ የተጠቀሱት ስለሆኑ ነው። [አልቡኻሪይ፡ 1515] እንጂ በብዙ መረጃዎች በደፈናው ምግብ በሚል መጥቷል። ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ሚንበር ላይ ሆነው ኹጥባ እያደረጉ እንዲህ ብለዋል፦
صدَقةُ الفِطرِ صاعٌ مِن طَعامٍ
"የፊጥር ሶደቃ ከምግብ አንድ ቁና ነው።" [ሶሒሑ ነሳኢይ፡ 2509]
ስለዚህ የሚፈለገው በአካባቢው ለምግብነት የሚውል እህል መሆኑ ነው።

ማጠቃለያ:-

ጉዳዩ በዑለማእ መካከል የሃሳብ ልዩነት የተንፀባረቀበት ቢሆንም ልቅ በሆነ መልኩ በገንዘብ መስጠት ይቻላል ያሉት ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው። "በገንዘብ መስጠት አያብቃቃም (ግዴታውን አያወርድም)" ያሉት ግን የነብዩ ﷺ ሐዲሥና የሶሐቦች ተግባራዊ ኢጅማዕ የያዙ ከመሆናቸው ጋር በቊጥርም ብዙሃን ናቸው። ደግሞም ኺላፍ ማስረጃ አይሆንም። ኺላፍ ሲከሰት ወደ ሐዲሥ ነው መመለስ ያለብን።

ለምታወጡት ዘካተል ፊጥር ጥንቃቄ ለምታደርጉ ሁሉ!
ራሳችሁን ኺላፍ ውስጥ አታስገቡ። ያውም እንዲህ አይነት ከአመክኖ በዘለለ ይሄ ነው የሚባል መረጃ የማይደግፈውን ሆድ የማያስነፋ ኺላፍ በሩቅ መሆን ነው የሚሻለው። የዘካተል ፊጥርን መቃሲድ ዛሬም በዱቄት፣ በእህል ሰጥቶ ማሳካት ይቻላል።
ልብ አድርጉ! በእህል ብታወጡ፡
* ማንም ደፍሮ "ዘካችሁ ተቀባይነት የለውም" ማለት አይችልም።
* ከነብያችን ﷺ ከተላለፉ ሐዲሦችም ከሶሐቦች ፈለጎችም ጋር መቶ ለመቶ ገጥማችኋል።
በእህል ሳይሆን በገንዘብ ብታወጡ ግን ዘካችሁ እንደ ብዙሃን ዑለማዎች ድምዳሜ ተቀባይነት የሌለው አፈፃፀም ነው። ግዴታ የሆነውን ዒባዳ ለእንዲህ አይነት ስጋት ከምታጋልጡ ይልቅ በትክክል በመፈፀም ከኺላፍ ቀጠና ብትርቁ የተሻለ ነው።

ማሳሰቢያ፦

"አንዳንዶች በዚህ ርእስ ላይ መነታረክ ለምን አስፈለገ?" ይላሉ።
1ኛ፦ ይሄ ሚዛን የሚደፋውን አቋም አጣርቶ ማሳየት እንጂ መንታረክ አይደለም። ከዚህ ባነሰም ጉዳይኮ ዑለማኦች ብዙ ይፅፋሉ? ለምንድነው ዛሬ እንደ እንግዳ የሚቆጠረው?
2ኛ፦ በጥሬ ገንዘብ ይቻላል የሚሉትስ መቼ ዝም አሉ? ከግላዊ እይታ ውጭ አንድ እንኳ መረጃ ሳይዙ አመት ጠብቀው በጥሬ ገንዘብ መስጠት ይቻላል የሚሉት ተነታራኪ ሳይባሉ እንዴት ነው በሐዲሦችና የሶሐቦች አፈፃፀም ላይ እንቁም የሚሉት ተነታራኪ የሚባሉት? ይሄ አደብ የቀለለው ንግግር ነው።
(ሃሳቡ በጉዳዩ ላይ ከተፃፉ የተለያዩ ስራዎች ተወስዶ የተጠናቀረ ነው።)
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዷን 27/1445)
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
13.1K views12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 10:39:06
አንድ ነጥብ ለአስተውሎት!
~
አማራ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት በደረሰበት ሰዓት "ታቦት የሚሸኙ የአማራ ሙስሊሞች" አይባልም። ኦሮሞ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት በደረሰበት ሰዓት "ኢሬቻ የሚያከብሩ ኦሮሞ ሙስሊሞች" አይባልም። ነውር ነው። የሚባልና የማይባል ነገር እንለይ። ንግግራችን ውስጥ የሆነ እውነት ቢኖር እንኳ የምንናገርበትን ቦታና ጊዜ እንወቅ። ወገናችን ልቡ በደማበት፣ ውስጡ በቆሰለበት ሰዓት ስብራቱን የሚጠግን፣ አለኝታነትን የሚገልፅ ማፅናኛ ቃል እንጂ ይበልጥ የሚያስከፋ ቃል አይሰነዘርም። ጥፋቶችን የምናወግዝበት፣ የሳቱትን የምናርምበት ሌላ በቂ ጊዜ አለ። ጊዜውን እንጠብቅ። እንዲያውም ችግሩ በሚንፀባረቅ ጊዜ አፅንኦት ሰጥተን እናስተምር። አሁንም ቢሆን ማንሳቱ ተገቢ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የተጎዱትን በሚያሸማቅቅ መልኩ አናንሳው።
ደግሞም በጅምላ መወንጀል ውሸትም ነውርም ነው። ታቦት መሸኘቱን የሚያወግዙ በርካታ የአማራ ሙስሊሞች አሉ። ኢሬቻን የሚኮንኑ በርካታ ኦሮሞ ሙስሊሞች አሉ። በጅምላ ፍረጃ ወንድሞቻችንን ነው የምንገፋው፡፡ ጠላት ነው የሚያተርፈው። ወንጀልን ነው የምንሸምተው። እየተስተዋለ!
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
13.4K viewsedited  07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 19:16:23
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
~
"ዛሬ ሌሊት በመኖሪያ ቤታቸው ሌሊት በመግባት በጥይት በስለታም ነገር ሁሉ ወጋግተው ባል ከነ ሚስቱ በሁለት ልጃቸው ፊት ገደሉብን ሀቢቢ"

ከጎጃም ቢቸና የደረሰኝ መልእክት ነው። የሚያሳዝነው ሞታቸው አይደለም። ሞት ለማን ይቀራል?! የሚያመው ገዳዮቻችን በስማችን የሚነግዱ መሆናቸው ነው። በየትኛውም ምድር በፖለቲካም ይሁን በሌላ አላማ ሙስሊሞችን ለይቶ እያጠቃም፣ እየተባበረም፣ ሽፋን እየሰጠም ያለን ሁሉ አላህ ድራሹን ያጥፋው። ፈፅሞ ካሰበው አያድርሰው። በዱንያም በኣኺራም አላህ ብርቱ ቅጣትን ይቅጣው። በበደለኞች ድግምት የተሸውደውን ወገናችንን ደግሞ አላህ ያንቃው። የሞቱትን በጀነት ይካሳቸው። ሸሂድነትን ያድላቸው። ኣሚን።
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
17.7K views16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 17:29:43
27ኛዋ ሌሊት!
~
ስለ ለይለተል ቀድር የትኛውም ቁጥር ቢገመት የ27ኛዋ ግን ይለያል። ከየትኛውም ሌሊት በተለየ ከፍ ያለ ግምት ይሰጣታል። ይቺን ሌሊት ፈፅሞ ዘንግቶና ቸልተኛ ሆኖ ማሳለፍ አይገባም። ስለዚህ ለክብደቷ የሚመጥን ትጋት ይኖረን ዘንድ እንዘጋጅ። ሶላት፣ ቁርኣን መቅራት፣ አዝካር፣ ድምፅን ዝቅ፣ ቀልብን ስብር አድርጎ ደግሞ ደጋግሞ በዱዓእ የሙጥኝ ማለት ያስፈልጋል። ኢኽላስ እና ኹሹዕ መዘንጋት የሌለባቸው ትጥቆች ናቸው። ባይሆን የሱብሕን ነገር አደራ! ብልጥ ነጋዴ ትርፍ ፍለጋ ወረቱን አይጥልም።
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
17.6K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 13:39:18 አጭር ማስታወሻ ስለ ዱዓእ
~
ዱዓእ ተቀባይነት ያገኛሉ ተብለው በሚታሰቡ በላጭ ሰዓቶች ላይ ከፍ ላሉ ጉዳዮች ትኩረት እንስጥ።
* አላህ ቀልባችንን እንዲያስተካክልልንና ዲን ላይ እንዲያፀናን። የነብዩ ﷺ ዱዓእ በብዛት እንዲህ የሚል ነበር፦
يا مُقلِّبَ القلوبِ ثبِّت قلبي على دينِكَ
“አንተ ልቦችን ገለባባጭ ሆይ! ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ።”
* በየትኛውም ዲናዊ ጉዳይ ለተሻለው እንዲመራን። ነብዩ ﷺ የሌሊት ሶላታቸውን በዚህ ዱዓእ ነበር የሚከፍቱት
اللَّهُمَّ رَبَّ جِبْرَائِيلَ، وَمِيكَائِيلَ، وإسْرَافِيلَ، فَاطِرَ السَّمَوَاتِ وَالأرْضِ، عَالِمَ الغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ، أَنْتَ تَحْكُمُ بيْنَ عِبَادِكَ فِيما كَانُوا فيه يَخْتَلِفُونَ، اهْدِنِي لِما اخْتُلِفَ فيه مِنَ الحَقِّ بإذْنِكَ؛ إنَّكَ تَهْدِي مَن تَشَاءُ إلى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ.
“አንተ የጂብራኢል፣ የሚካኢል፣ የኢስራፊል ጌታ የሆንከው፣ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ የሆንከው፣ የሩቁንም የቅርቡንም የምታውቀው አላህ ሆይ!ባሮችህ ሲወዛገቡበት በነበረው ነገር አንተ ትፈርዳለህ፡፡ ከሐቅ ለሚወዛገቡበት ነገር ምራኝ፡፡ አንተ የፈለግከውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትመራለህና፡፡” [ሙስሊም]
* ወንጀላችንን ምሮ ከእሳት እንዲጠብቀን፣ ጀነትን እንዲያድለን:- የሙስሊም ትልቁ ሃሳብ ጭንቀቱ ይሄ ነው መሆን ያለበት።
اللَّهمَّ إنِّي أسألُك الجنَّةَ وأعوذُ بِك منَ النَّارِ
"አላህ ሆይ! እኔ ጀነትን እለምንሀለሁ። ከእሳትም ባንተ እጠበቃለሁ።"
* የአላህን ይቅርታ ለማግኘት መትጋት። እናታችን ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ለነብዩ ﷺ ለይለተል ቀድር መሆኑን ካሰብኩ ምን ልበል ስትላቸው የጠቆሟት ዱዓእ ይሄ ነበር፦
اللَّهمَّ إنَّكَ عفوٌّ، تُحِبُّ العفوَ فاعفُ عنِّي.
"አላህ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ። ይቅር ማለትን ትወዳለህ። ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ።”
* ለዚክር፣ ለምስጋና፣ ላማረ የዒባዳ አፈፃፀም እንዲወፍቀን
اللهمَّ أعني على ذكرِك وشكرِكَ وحسنِ عبادتِكَ
"አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ አንተን በሚመስገን እና አንተን ባማረ መልኩ በመገዛት ላይ አግዛኝ።"
* ለወገኖቻችንም እንዲሁ የጠመሙትን እንዲያቀናልን፣ የሞቱትን እንዲምርልን፣ ለወላጆቻችን እንዲያዝንላቸው፣ በሃገራችን፣ በፊለስጢን፣ በሱዳን፣ በሊቢያ፣ በሌሎችም ቦታዎች መከራ ላይ ያሉትን ከፈተና እንዲያወጣልን፣ ሰላም እንዲሰጠን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል።
* ባጠቃላይ በዱንያም በኣኺራም መልካሙን እንዲያድለን ጠቅላይ ጠቅላይ ዱዓኦችን መምረጥ መልካም ነው። ነብዩ ﷺ ያዘወትሯቸው ከነበሩ ዱዓኦች ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር፦
اللَّهُمَّ رَبَّنَا آتِنَا في الدُّنْيَا حَسَنَةً، وفي الآخِرَةِ حَسَنَةً، وقِنَا عَذَابَ النَّارِ.
"አላህ ሆይ! በዱንያም መልካምን፣ በኣኺራም መልካም ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።"
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
12.6K viewsedited  10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 11:23:32 ረስቶ የሚበላን ወይም የሚጠጣን ፆመኛ ማስታወስ
~
ፆመኛ ሰው ረስቶ ቢበላ ወይም ቢጠጣ ፆሙ አይበላሽም። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
من نسي وهو صائم فأكل أو شرب فليتم صومه فإنما أطعمه الله وسقاه
"ፆመኛ ሆኖ ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ፆሙን ባለበት ይቀጥል። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነው።" [አልቡኻሪይ፡ 1933] [ሙስሊም፡ 1155]

ይህንን መነሻ በማድረግ ረስቶ የሚበላና የሚጠጣን ሰው ማስታወስ አይገባም የሚሉ አሉ። እንደማጠናከሪያም የኢብኑ ዑመርን 'አሠር' ያጣቅሳሉ።
ኢብኑ ዑመር አስታወኩና [ሊበሉ ሲሉ] "ፆመኛ አይደለህ?" አሏቸው ዐብዱላህ ብኑ ዲናር። በዚህን ጊዜ "አላህ ሊያበላኝ ሸቶ ነበር ከለከልከኝ" አሉ። [አልሙሐላ፣ ኢብኑ ሐዝም 6/221]

ይህንን አሠር' ከጠቀሰ በኋላ እንዲህ ያለ አለ፡
"ሶሒሕ ነው። ከሶሐባም፣ ከታቢዒይም ከተከታዮቻቸውም የተቃረነው አላውቅም። አንዳንድ ዓሊም ግን 'ማስታወስ ይገባል። ይሄ በበጎ ነገርና አላህን በመፍራት ላይ መተባበር ርእስ ውስጥ ይገባል' ይላል። በዚህ ላይ ትክክለኛው ሊያስታውሱት አይገባም የሚለው ነው። ምክንያቱም እሱ ጥፋት አልፈፀመምና። ጥፋት ቢሆን ኖሮ ከነብዩ ﷺ በተላለፈው ረስቶ ከበላና ከጠጣ ፆሙን ባለበት ይቀጥል' በሚለው ሐዲሥ ላይ 'ያበላውና ያጠጣው አላህ ነው' የሚል ቃል ባልኖረ ነበር" [አተሕጂል፡ 154]

ይሄ ንግግር ሙሉ ለሙሉ ስህተት ነው።

1ኛ:- ከሰነድ አንፃር፦

1.1. ሰነዱ ከመነሻው የተቆረጠ እንደሆነ ሙሐላ ላይ በግልፅ ይታያል። ኢብኑ ሐዝም ዘግይተው ነው የመጡት። የዘገቡት ግን ከወኪዕ፣ ከሹዕባ ፣ ... ብለው ነው። ከወኪዕ ጋር ዘመናቸው በጣም የተራራቀ እንደሆነ ይታወቃል፡። ይሄ እየታወቀ ጫፉን ብቻ በመመልከት ሶሒሕ ነው ማለት ተገቢ አይደለም።
1.2. ይሄ ዘገባ ከኢብኑ ሐዝም ውጭ በኢባዲያና መሰል ሀሰተኛ ስራዎች ላይ እንጂ አይታወቅም ይላሉ አጥኚዎች።
1.3. "አላህ ሊያበላኝ ሸቶ ነበር ከለከልከኝ" የሚለው ቃልም ጤነኛ አይደለም። የአላህ መሻት በፍጡር መሻት የሚሰናከል አይደለምና።

2ኛ፦ ከሌሎች ሰለፎች 'ኣሣሮች' አንፃር፦

ይህንን ደካማ ዘገባ የሚቃረኑ ሌሎች መረጃዎች ከሰለፎች በተጨባጭ ተገኝተዋል። ምሳሌ ልጥቀስ:-
2.1. ዐብዱላህ ብኑ ሸቂቅ ረሒመሁላህ ለአቡ ዘር ረዲየላሁ ዐንሁ "ፆመኛ ነህ ወይ?" ብዬ ጠየቅኳቸው ይላሉ። እሳቸውም "አዎ" አሉ። ቤት ስንገባ ግን አብረው መብላት ያዙ። ከዚያ ግን በእጄ እየነቀነቅኩ #አስታወስኳቸው ይላሉ። [አሱነኑል ኩብራ፣ በይሀቂይ፡ 4/293]
2.2. አቡ ጦልሐ በፆም በረዶ ሲበሉ አነስ "ፆመኛ አይደለህንዴ?" ብለው #አስታውሰዋቸዋል። ሸይኹል አልባኒይ "በቡኻሪይና ሙስሊም መስፈርት መሰረት የተዘገበ ትክክለኛ ነው" ብለውታል። [አዶዒፋህ: 1/154]
ማስታወስ እንደሚገባ ከሶስት ሶሐባ አገኘን ማለት ነው። አቡ ዘር፣ አቡ ጦልሐ እና አነስ። እንዲሁም ከዐብዱላህ ብኑ ሸቂቅ። ከኢብራሂም አነኸዒይ፣ ከዐብዱላህ ኢብኑል ሙባረክ፣ ከአሕመድና ከሌሎችም ሰለፎች ማስታወስ እንደሚገባ እንደተገኘ አጥኚዎች ገልፀዋል።
ማስታወስ አይገባም የሚለው ግን ቀደምቶች ዘንድ አይታወቅም። ኋላ ላይ የመጡት ዘንድ ነው የተስተዋለው።

3ኛ፦ ከጭብጥ አንፃር

ረስቶ የበላና የጠጣን ሰው አላህ ነው ያበላውና ያጠጣው የሚለው በድርጊቱ ውስጥ ስህተት የለም ለማለት አይደለም። ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ በዚህ መልኩ ተርጉሞ ማስታወስ አይገባም የሚል አለ ተብለው ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ ነበር የመለሱት፦
الذي يقول هذا الكلام جاهل؛ لأنَّ الله تعالى أطعمه وسقاه باعتبار نفسه هو؛ لأنه ناسٍ، أما أنت فأنت عالم، فلا بد أن تنبهه، هذا مثل الذي يقول: إذا رأيت القط يأخذ حمامة شخص فلا تنقذها منه؛ لأنَّ هذا رزق القط، هل هذا صحيح؟ لا.
"ይህንን ንግግር የሚናገር ሰው መሀይም ነው። ምክንያቱም 'የላቀው አላህ አበላው አጠጣው' የሚባለው ከራሱ አንፃር ነው። የረሳ ነውና። አንተ ግን ፆመኛ መሆኑን ታውቃለህ። ስለሆነም የግድ ልታስታውሰው ይገባል። ይሄ 'ድመት የአንድን ሰው እርግብ ስትበለ እንዳታስጥላት። ምክንያቱም ይሄ የድመቷ ሲሳይ ነውና' እንደሚል ሰው ነው። ይሄ ትክክል ነው? በጭራሽ!" [ሊቃኡል ባቢል መፍቱሕ፡ 18]

ስለዚህ የሐዲሡ ጭብጥ ዒባዳ የሚያበላሽን ነገር ረስቶ እየፈፀመ ያለን አካል ማስታወስ አይገባም ማለት አይደለም። በረመዷን ቀን ላይ መመገቡ ስህተት ነው። "አላህ ነው ያበላውና ያጠጣው" ማለት የረሳ ስለሆነ ተጠያቂ አይደለም ለማለት እንጂ በመርሳት የሚፈፀም ስህተት ኢንካር አይደረግም ለማለት አይደለም። ረስቶ ስህተት የሚሰራን ሰው ማስታወስ ይገባል። ሶላት ላይ የሚጋጥምን ስህተት አስመልክቶ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ:-
إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ أَنْسَى كَمَا تَنْسَوْنَ، فَإِذَا نَسِيتُ فَذَكِّرُونِي
"እኔ ሰው ነኝ። እንደምትረሱ እረሳለሁ። ስረሳ ጊዜ አስታውሱኝ።" [አልቡኻሪይ፡ 401] [ሙስሊም፡ 572]
ልብ በሉ! ይሄ አካሄድ ሶላት ላይ ብቻ የሚገደብ አይደለም። ሁሉንም ዒባዳ ይመለከታል። ይህንን ቃዒዳ እናስታውስ፦
العبرة بعموم اللفظ، لا بخصوص السبب
በዒባዳ ላይ የረሳን ማስታወስ ጠንካራ መሰረት ያለው ኢስላማዊ መርህ ነው። ረስቶ ወይም ተኝቶ ሶላት ያለፈው ሰው ወንጀለኛ አይደለም። ይሄ ማለት ግን "አላህ ነው ያስተኛው" ብለን ወቅት እያለፈ ዝም እንለዋለን ማለት አይደለም።
ከዚህ በተቃራኒ ዒባዳን የሚያበላሽ ስህተት በመርሳት ሲፈፀም አታስታውሱ የሚል አንድም መረጃ የለም።

ሳጠቃልል ከዘመናችን ታላላቅ ዑለማኦች ውስጥ ሸይኹል አልባኒይ፣ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን ፆመኛ ረስቶ ሲመገብ ማስታወስ ይገባል ይላሉ። ወላሁ አዕለም።
(ኢብኑ ሙነወር: ረመዷን 25/1445)
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
13.5K viewsedited  08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 13:58:19 ዘካተል ፊጥርን የሚመለከቱ ነጥቦች
~
1- ምንነቱ፦ ሙስሊሞች ከዒደል ፊጥር በፊት ለችግረኞች የሚሰጥ የእህል / የምግብ ሶደቃ ነው።
2- ሑክሙ፦ በሚችል ሰው ላይ ግዴታ ነው። [አልቡኻሪይ፡ 1503] [ሙስሊም፡ 984]
3- በማን ላይ ነው ግዴታው?
3.1. በትንሽ በትልቁ፣ በሴት በወንዱ፣ በሁሉም ሙስሊም በሆኑ የቤተሰብ አባላት ቁጥር የሚወጣ ሶደቃ ነው።
3.2. ገና ያልተወለደ ፅንስ እዚህ ግዴታ ውስጥ አይገባም።
3.3. አንድ ሰው የሌሎችን ዘካተል ፊጥር (ለምሳሌ ከሱ ጋር ያልሆኑ ቤተሰቦቹን ወይም የአገልጋዮችን) ማውጣት ይችላል። ግን እንደሚያወጣላቸው ማሳወቅ ይገባል።

4- ምን ያህል አቅም ባለው ላይ ነው ግዴታ የሚሆነው? ለራሱም ለቤተሰቡም ለዒድ ሌሊትና ቀን የሚበቃ ቀለብ ባለው ላይ ግዴታ ነው።
5- ለማን ነው የሚሰጠው? የእለት ጉርስ ለሌለው ድሃ።
5.1. ዘካ እና ዘካተል ፊጥር የሚሰጠው ለሙስሊም ብቻ ነው። ሌሎች ሶደቃዎችን ሙስሊም ላልሆኑ አካላት መስጠት ይቻላል።
5.2. ሑክሙን ባለማወቅ ወይም የሚግገባው አካል ስለማያገኙ ለሰራተኞቻቸው ዘካተል ፊጥር የሚሰጡ ሰዎች አሉ። ሰራተኞቻቸው የማይገባቸው ከሆኑ የተሰጣቸውን ለሚግገባቸው አሳልፈው መስጠት ይኖርባቸዋል።

6- የሚሰጡ የእህል / የምግብ አይነቶች፦ ተምር፣ ዘቢብ፣ አይቤ እንዲሁም በሃገር በአካባቢው ለቀለብነት የሚውሉ፣ ረዘም ላለ ጊዜ ሳይበላሹ መቆየት የሚችሉ የእህል / የምግብ አይነቶች ሁሉ ይገባሉ። ምክንያቱም "ከምግብ አንድ ቁና" የሚል ሐዲሥ አለና። [አልቡኻሪይ፡ 1508] [ሙስሊም፡ 985] በዒዱ እለት መመገብ የሚችሉት አይነት ቢሆን ተመራጭ ነው።
7- መጠኑ፦ አንድ ቁና (ሷዕ) ነው። በአራቱ ኸሊፋዎች ዘመን በዚህ መልኩ ነው ሲፈፀም የኖረው።
7.1. በራስ ፈቃደኝነት ጨምሮ ቢሰጥ ይቻላል።
7.2. የሚሰጠው መጠን በኪሎ ግራም:- በሐዲሥ የመጣው በስፍር ስለሆነ የክብደት መለኪያ ስንጠቀም እንደ እህሉ አይነት መጠኑ ይለያያል። ወደ ኪሎ ሲቀየር ዱቄት ላይ 2.5 ኪሎ አቅራቢያ ይመጣል። ይሄ የአንድ ሰው መጠን ነው። 10 ቤተሰብ ያለው ሰው 25 ኪሎ ማለት ነው።

8- ጊዜው፦ ግዴታ የሚሆነው የረመዷን ወር የመጨረሻ እለት ተጠናቆ የዒዱ ሌሊት ሲገባ ነው። ልብ በሉ! በኢስላማዊው አቆጣጠር የአንድ እለት ቀዳሚው ክፍል ቀኑ ሳይሆን ሌሊቱ ነው።
8.1. ከዒድ ሶላት ማሳለፍ አይፈቀድም። ረስቶ በጊዜው ያላወጣ ሰው ሲያስታውስ ቢሰጥ ወንጀል አይኖርበትም። አውቆ ወይም ችላ ብሎ ወቅት ካሳለፈ ግን ወንጀል ላይ ወድቋል። ቢሆንም ግን የድሃ ሐቅ ስለሆነ ወቅቱ ቢያልፍም ሊያወጣ ይገባል።
8.2. ተቀባዩ በመራቁ የተነሳ በእለቱ ለማድረስ የሚቸገር ሰው "የት ላድርግልህ?" ብሎ ይጠይቅና ከወከለበት ቦታ ያደርግለታል። በዚህን ጊዜ በእለቱ ባይወስድም ችግር የለውም።
8.3. አስቀድሞ መስጠት ይቻላል? ለሚሰበስቡ አካላት አንድ ቀን ሁለት ቀን ቀድሞ መስጠት ይቻላል። ከዚህ ውጭ በጊዜው መስጠት እየተቻለ ቀደም ብሎ መስጠት አይገባም። ነገር ግን በእለቱ ለመስጠት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲኖሩ ትንሽ ቀደም ብሎ መስጠት ይቻላል። እንዲሁም በውጭ ሃገራት ያሉ ሰዎች ለሚሰጥላቸው አካል ቀደም ብለው መላክ ይችላሉ። ወኪሉ ግን በተቻለ መጠን ወቅቱን መጠበቅ አለበት።
9. ከቤተሰብ ርቃችሁ ለምትገኙ ተማሪዎች ወላጆቻችሁ ዘካተል ፊጥር የማያወጡላችሁ ከሆነና የማውጣት አቅሙ ካላችሁ ዘካተል ፊጥር ማውጣት እንዳትረሱ።
10. አስገዳጅ ወይም አንገብጋቢ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር በገንዘብ ማውጣት አይቻልም። ዝርዝሩ በቀጣይ የሚታይ ይሆናል ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
19.2K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 13:58:13
13.6K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ