Get Mystery Box with random crypto!

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! ~ 'ዛሬ ሌሊት በመኖሪያ ቤታቸው ሌሊት በመግባት በጥይት በስለታ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!
~
"ዛሬ ሌሊት በመኖሪያ ቤታቸው ሌሊት በመግባት በጥይት በስለታም ነገር ሁሉ ወጋግተው ባል ከነ ሚስቱ በሁለት ልጃቸው ፊት ገደሉብን ሀቢቢ"

ከጎጃም ቢቸና የደረሰኝ መልእክት ነው። የሚያሳዝነው ሞታቸው አይደለም። ሞት ለማን ይቀራል?! የሚያመው ገዳዮቻችን በስማችን የሚነግዱ መሆናቸው ነው። በየትኛውም ምድር በፖለቲካም ይሁን በሌላ አላማ ሙስሊሞችን ለይቶ እያጠቃም፣ እየተባበረም፣ ሽፋን እየሰጠም ያለን ሁሉ አላህ ድራሹን ያጥፋው። ፈፅሞ ካሰበው አያድርሰው። በዱንያም በኣኺራም አላህ ብርቱ ቅጣትን ይቅጣው። በበደለኞች ድግምት የተሸውደውን ወገናችንን ደግሞ አላህ ያንቃው። የሞቱትን በጀነት ይካሳቸው። ሸሂድነትን ያድላቸው። ኣሚን።
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor