Get Mystery Box with random crypto!

አንድ ነጥብ ለአስተውሎት! ~ አማራ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት በደረሰበት ሰዓት 'ታቦት የሚሸኙ የአማራ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

አንድ ነጥብ ለአስተውሎት!
~
አማራ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት በደረሰበት ሰዓት "ታቦት የሚሸኙ የአማራ ሙስሊሞች" አይባልም። ኦሮሞ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት በደረሰበት ሰዓት "ኢሬቻ የሚያከብሩ ኦሮሞ ሙስሊሞች" አይባልም። ነውር ነው። የሚባልና የማይባል ነገር እንለይ። ንግግራችን ውስጥ የሆነ እውነት ቢኖር እንኳ የምንናገርበትን ቦታና ጊዜ እንወቅ። ወገናችን ልቡ በደማበት፣ ውስጡ በቆሰለበት ሰዓት ስብራቱን የሚጠግን፣ አለኝታነትን የሚገልፅ ማፅናኛ ቃል እንጂ ይበልጥ የሚያስከፋ ቃል አይሰነዘርም። ጥፋቶችን የምናወግዝበት፣ የሳቱትን የምናርምበት ሌላ በቂ ጊዜ አለ። ጊዜውን እንጠብቅ። እንዲያውም ችግሩ በሚንፀባረቅ ጊዜ አፅንኦት ሰጥተን እናስተምር። አሁንም ቢሆን ማንሳቱ ተገቢ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የተጎዱትን በሚያሸማቅቅ መልኩ አናንሳው።
ደግሞም በጅምላ መወንጀል ውሸትም ነውርም ነው። ታቦት መሸኘቱን የሚያወግዙ በርካታ የአማራ ሙስሊሞች አሉ። ኢሬቻን የሚኮንኑ በርካታ ኦሮሞ ሙስሊሞች አሉ። በጅምላ ፍረጃ ወንድሞቻችንን ነው የምንገፋው፡፡ ጠላት ነው የሚያተርፈው። ወንጀልን ነው የምንሸምተው። እየተስተዋለ!
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor