Get Mystery Box with random crypto!

يَدَعونَ قولَ رسولِ الله صلَّى الله عليه وسلَّمَ ويَقولون: قال | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

يَدَعونَ قولَ رسولِ الله صلَّى الله عليه وسلَّمَ ويَقولون: قال فُلانٌ! ... وقال اللهُ تعالَى: {أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ}
"የአላህ መልእክተኛን ﷺ ንግግር ትተው 'እከሌ እንዲህ አለ' ይላሉ። ... የላቀው አላህ 'አላህን ታዘዙ። መልእክተኛውንም ታዘዙ ብሏል።" [አልሙግኒ፣ ኢብኑ ቁዳማ]
ከሐሰኑል በስሪይ ግን ተገኝቷል። ቢሆንም የአሕመድ ንግግር ለዚህም ምላሽ ይሆናል። የታቢዒይ ንግግር ከሐዲሥ ጋር ቀርቶ ከሶሐባ ንግግር ጋርም ትይዩ አይቀመጥም። እዚህ ላይ ሲሆን በተለየ የሚወስዱ ከሆነ የታቢዒዩ ዐጧእ ንግግር ከፊታቸው እናቀርባለን። ከአቡ ሐኒፋም ተገኝቷል። ቢሆንም ከሐዲሥ ጋር የሚገጥመው የሌሎች ታላላቆች ንግግር ቅድሚያ ይሰጠዋል።
4.2. ደግሞም ዘካተል ፊጥር ከንብረት ዘካ (ዘካተል ማል) ይለያል።
* ዘካተል ማል ለዘካ መጠን (ኒሷብ) የደረሰ ገንዘብ ላይ ነው ግዴታ የሚሆነው። ከሰብል ምርት ውጭ ባሉት ንብረቶች ላይ ደግሞ አመት መቆየት አለበት። የሚመለከተውም ሁሉንም አይነት ንብረቶች አይደለም። ዘካተል ፊጥር ግን በቂ የእለት ጉርስ ካለ ህፃን ከአዋቂ ሳይለይ በሁሉም የቤተሰብ ቁጥር የተደነገገ ነው።
* ዘካተል ማል ንብረቱ ላይ ነው የሚያነጣጥረው። ዘካተል ፊጥር ግን ሰዎች ላይ ነው የሚያነጣጥረው። ለዚያም ነው ዘካተል ማል በንብረቱ ሂሳብ ታስቦ የሚወጣው። የንብረቱ መጠን ሲጨምር የዘካው መጠን ይጨምራል። ሲያንስ ያንሳል። ከኒሷብ ከወረደ ይቀራል። ዘካተል ፊጥር ግን ሁሉም ሰው እኩል አንድ አንድ ቁና ነው የሚያወጣው።
* ዘካተል ማል በአንፃራዊነት ሃብት ባለው ላይ ነው የተደነገገው። ዘካተል ፊጥር ግን የእለት ጉርስ ካለው ድሃውንም ይመለከታል።

5ኛ:- ዘካተል ፊጥርን በጥሬ ገንዘብ መስጠት በሶሐቦቹ ጊዜም ቢሆን ለሰጪው ቀላል፣ ተቀባዩም ላሰኘው ነገር ስለሚያውለው የተሻለ ነበር። ከመሆኑም ጋር የተደነገገውም የተገኘውም በአይነት መስጠት ነው። ጥሬ ገንዘቡን መስጠት ቢቻል ለምን አያደርጉትም ነበር?!
6ኛ፦ ለዘካተል ፊጥር የተደነገጉት ምግቦች ዋጋቸው መለያየቱም የራሱ ጥቆማ አለው። የገብስ፣ የተምር፣ የዘቢብ፣ የስንዴ፣ የአይቤ፣ ... ዋጋዎች አንዱ ከሌላው የሚለያይ ከመሆኑ ጋር ከሁሉም አይነት አንድ ቁና ነው የታዘዘው። ትኩረቱ ዋጋው ቢሆን ኖሮ ዋጋቸው በሚራራቁ ምግቦች ለሁሉም አንድ ቁና ባልተባለ ነበር። [መዓሊሙ ሱነን፣ አልኸጧቢይ]

ብዥታ፦

በሐዲሥ ለዘካተል ፊጥር የተጠቀሱት የምግብ አይነቶች ተምርና ገብስ ከመሆናቸው ጋር ኋላ ሌሎች እህሎች መካተታቸው በጥሬ ገንዘብ መስጠት እንደሚቻል ያሳያል የሚሉ አሉ። ይህም ልክ አይደለም።
1- ሲጀመር በጊዜው የነበረው አሰራር ተምርና ገብስ ላይ የተገደበ አልነበረም። ዱቄት፣ ዘቢብ፣ አይቤ በተለያዩ መረጃዎች ተጠቁመዋል።
2- በጊዜው እነዚህን ምግቦች ሲሰጡ የነበረው በዘመኑ ምግቦቻቸው እነዚህ የተጠቀሱት ስለሆኑ ነው። [አልቡኻሪይ፡ 1515] እንጂ በብዙ መረጃዎች በደፈናው ምግብ በሚል መጥቷል። ኢብኑ ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ ሚንበር ላይ ሆነው ኹጥባ እያደረጉ እንዲህ ብለዋል፦
صدَقةُ الفِطرِ صاعٌ مِن طَعامٍ
"የፊጥር ሶደቃ ከምግብ አንድ ቁና ነው።" [ሶሒሑ ነሳኢይ፡ 2509]
ስለዚህ የሚፈለገው በአካባቢው ለምግብነት የሚውል እህል መሆኑ ነው።

ማጠቃለያ:-

ጉዳዩ በዑለማእ መካከል የሃሳብ ልዩነት የተንፀባረቀበት ቢሆንም ልቅ በሆነ መልኩ በገንዘብ መስጠት ይቻላል ያሉት ግን በጣም ጥቂቶች ናቸው። "በገንዘብ መስጠት አያብቃቃም (ግዴታውን አያወርድም)" ያሉት ግን የነብዩ ﷺ ሐዲሥና የሶሐቦች ተግባራዊ ኢጅማዕ የያዙ ከመሆናቸው ጋር በቊጥርም ብዙሃን ናቸው። ደግሞም ኺላፍ ማስረጃ አይሆንም። ኺላፍ ሲከሰት ወደ ሐዲሥ ነው መመለስ ያለብን።

ለምታወጡት ዘካተል ፊጥር ጥንቃቄ ለምታደርጉ ሁሉ!
ራሳችሁን ኺላፍ ውስጥ አታስገቡ። ያውም እንዲህ አይነት ከአመክኖ በዘለለ ይሄ ነው የሚባል መረጃ የማይደግፈውን ሆድ የማያስነፋ ኺላፍ በሩቅ መሆን ነው የሚሻለው። የዘካተል ፊጥርን መቃሲድ ዛሬም በዱቄት፣ በእህል ሰጥቶ ማሳካት ይቻላል።
ልብ አድርጉ! በእህል ብታወጡ፡
* ማንም ደፍሮ "ዘካችሁ ተቀባይነት የለውም" ማለት አይችልም።
* ከነብያችን ﷺ ከተላለፉ ሐዲሦችም ከሶሐቦች ፈለጎችም ጋር መቶ ለመቶ ገጥማችኋል።
በእህል ሳይሆን በገንዘብ ብታወጡ ግን ዘካችሁ እንደ ብዙሃን ዑለማዎች ድምዳሜ ተቀባይነት የሌለው አፈፃፀም ነው። ግዴታ የሆነውን ዒባዳ ለእንዲህ አይነት ስጋት ከምታጋልጡ ይልቅ በትክክል በመፈፀም ከኺላፍ ቀጠና ብትርቁ የተሻለ ነው።

ማሳሰቢያ፦

"አንዳንዶች በዚህ ርእስ ላይ መነታረክ ለምን አስፈለገ?" ይላሉ።
1ኛ፦ ይሄ ሚዛን የሚደፋውን አቋም አጣርቶ ማሳየት እንጂ መንታረክ አይደለም። ከዚህ ባነሰም ጉዳይኮ ዑለማኦች ብዙ ይፅፋሉ? ለምንድነው ዛሬ እንደ እንግዳ የሚቆጠረው?
2ኛ፦ በጥሬ ገንዘብ ይቻላል የሚሉትስ መቼ ዝም አሉ? ከግላዊ እይታ ውጭ አንድ እንኳ መረጃ ሳይዙ አመት ጠብቀው በጥሬ ገንዘብ መስጠት ይቻላል የሚሉት ተነታራኪ ሳይባሉ እንዴት ነው በሐዲሦችና የሶሐቦች አፈፃፀም ላይ እንቁም የሚሉት ተነታራኪ የሚባሉት? ይሄ አደብ የቀለለው ንግግር ነው።
(ሃሳቡ በጉዳዩ ላይ ከተፃፉ የተለያዩ ስራዎች ተወስዶ የተጠናቀረ ነው።)
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረመዷን 27/1445)
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M