Get Mystery Box with random crypto!

27ኛዋ ሌሊት! ~ ስለ ለይለተል ቀድር የትኛውም ቁጥር ቢገመት የ27ኛዋ ግን ይለያል። ከየትኛውም | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

27ኛዋ ሌሊት!
~
ስለ ለይለተል ቀድር የትኛውም ቁጥር ቢገመት የ27ኛዋ ግን ይለያል። ከየትኛውም ሌሊት በተለየ ከፍ ያለ ግምት ይሰጣታል። ይቺን ሌሊት ፈፅሞ ዘንግቶና ቸልተኛ ሆኖ ማሳለፍ አይገባም። ስለዚህ ለክብደቷ የሚመጥን ትጋት ይኖረን ዘንድ እንዘጋጅ። ሶላት፣ ቁርኣን መቅራት፣ አዝካር፣ ድምፅን ዝቅ፣ ቀልብን ስብር አድርጎ ደግሞ ደጋግሞ በዱዓእ የሙጥኝ ማለት ያስፈልጋል። ኢኽላስ እና ኹሹዕ መዘንጋት የሌለባቸው ትጥቆች ናቸው። ባይሆን የሱብሕን ነገር አደራ! ብልጥ ነጋዴ ትርፍ ፍለጋ ወረቱን አይጥልም።
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor