Get Mystery Box with random crypto!

ትላንት ማታ በረመዷን 27 ጎንደር ቀበሌ 8 አዲስ ዓለም በሚባለው ሰፈር ሰይድ በሺር የተባለ አንድ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ትላንት ማታ በረመዷን 27 ጎንደር ቀበሌ 8 አዲስ ዓለም በሚባለው ሰፈር ሰይድ በሺር የተባለ አንድ ወንድማችን ተገድሏል። አላህ የጀነት ያድርገው። ሌላ ደግሞ ቀበሌ 10 በአታ አካባቢ አንድ ወንድማችንን ቤት ሰብረው ገብተው አግተው ሲወስዱት አምልጧቸው ከሰው ግቢ ሲገባ በግርግሩ መሀል አንድ ሰው ተጎድቷል።
ባለፈው ሰሜን ሸዋ ላይ በአካባቢው የተወሰኑ ሙስሊሞችን የአዲሱ የመጅሊስ መዋቅር አባል በመሆናቸው ብቻ የብልፅግና ደጋፊ ተብለው ተገድለዋል።
የፋኖ ትግል አንዱ ዘርፍ ሙስሊሞችን ማሳደድ ሆኗል። የሚደንቀው ቡድኑ በጭፍን ከማስተባበል ውጭ ኃላፊነት የሚሰማው ለምን የሚል አካል የሌለው መሆኑ ነው። ጥፋቱን ለማረም ከመሞከር ይልቅ "የወለጋው ሲሆን... " እያለ አፍ ማስያዝን ቁም ነገር አድርጎታል። ዲስፕሊን የማያውቅ፣ ህዝብን በሃይማኖት ለይቶ የሚያጠቃ፣ ጉልበቱን አቅመ ደካሞች ላይ የሚያሳይ ትግል በርግጠኝነት የትም አይደርስም። ለነዚህ አካላት ድጋፍ የምታደርጉ ወገኖች አሁንስ አትነቁም?!
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor