Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.07K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-04-08 19:04:38 ዛሬ የሸዋል ጨረቃ እንዳልታየች የሰዑዲያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አረጋግጧል። ስለዚህ ዛሬ የመጨረሻውን የተራዊሕ ሶላት እንሰግዳለን ኢንሻአላህ። ዒዱ ረቡእ ይሆናል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
23.4K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 18:34:15 ጨረቃ የሚታየው በብዙ ማእከላት ነው። እስካሁን በብዙዎቹ አልታየም። የቀሩ ግን አሉ። የሚወሰነው በሁሉም ሳይታይ ሲቀር ነው:: ይህን የሚያረጋግጠው ደግሞ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ነው።
18.2K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 18:23:10 እስካሁን ገና ነው። እየወጡ ያሉ ዜናዎች የተቻኮሉ ናቸው።
17.5K views15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 18:11:02 የፆም መያዣም ይሁን መፍቻው በጨረቃ እይታ ነው የሚወሰነው። በስነ ፈለክ ምሁራን ድምዳሜ ላይ አንጠለጠልም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
لا تصوموا حتى تَرَوُا الهلالَ ، ولا تُفْطِروا حتى تَرَوْهُ ، فإن غُمَّ عليكم فاقْدُروا له
"ጨረቃን ሳታዩ አትፁሙ። ሳታዩትም አታፍጥሩ። በጉም ከተሸፈነባችሁ (ሰላሳውን) አስቡ።" [አልቡኻሪይ፡1906] [ሙስሊም፡ 1080]
የሆነ ሆኖ የረመዷን ፍጻሜ ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ የሚታወቅ ይመስላል። የማገኘውን መረጃ እዚህ ለመለጠፍ እሞክራለሁ ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
18.2K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 15:08:54 የፋኖ ትግል የሃይማኖት ነው
~
ወደ ዋናው ነጥብ ከመግባቴ በፊት ትላንት ከመግሪብ ሶላት መልስ የተገደሉት ወንድሞቻችን 3 እንደሆኑ ገልጬ ነበር። ኋላ ላይ በደረሰኝ መረጃ ግን ሟቾቹ አምስት ናቸው። ሙሔ ሰሜ፣ አበባው ሙሄ፣ ሙሉ ሀብት ሙሄ፣ ብርሀኑ ሙሄ እና ኢድሪስ መኮነን ናቸው። አላህ ሸሂድነትን ይወፍቃቸው።

ወደ ነጥቤ ስመለስ የዚህ ገዳይ ስብስብ አላማ ሃይማኖት ተኮር ነው። ተወደደም ተጠላም እውነታው ከዚህ የራቀ አይደለም። መሬት ላይ ያለ ተጨባጭ በሸንጋይ ቃላት አይሸፈንም። አላማቸው ሃይማኖት እንደሆነ የሚያሳዩ ብዙ ማሳያዎች አሉ። የተወሰኑትን እንይ፦

1ኛ፦ ፋኖዎች በተደጋጋሚ ትግላቸው ለማተባቸው እንደሆነ ገልፀዋል። ይሄ ግልፅ መልእክት የያዘ ነው።
2ኛ፦ በተደጋጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሙስሊምነት መክሰሳቸውም የልጅ እያሱን ዘመን ያስታውሰናል። ልጅ እያሱ በሙስሊምነት ተከስሶ ነው ከመንበሩ የተፈነገለው። ሙስሊምነት ለቤተ መንግስት የማያበቃ ወንጀል ነው። ይሄ ክሳቸው ለሙስሊሞች ምን አይነት እይታ እንዳላቸው፣ ምናባቸው ውስጥ ባለችው ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስሊሞች ምን አይነት ቦታ እንዳላቸው የሚጠቁም ነው።
3ኛ፦ በተደጋጋሚ የፋኖ ደጋፊ ቄሶች በቲቪ ቀርበው ከግራኝ ዘመን የከፋ ጊዜ ላይ ነው ያለነው ሲሉ ነበር። ይህም ራሱ ደረሰብን የሚሉትን ጭቆና ከእምነት ጋር እያያያዙትና ከሙስሊሞች ጋርም እያነካኩት እንደሆነ ነው የሚያሳየው።
4ኛ፦ በተደጋጋሚ ሙስሊሞችን ለይተው እያጠቁ ነው። በርካቶች ተገድለዋል። በርካቶች የትውልድ ቀያቸውን ጥለው ሸሽተዋል። በርካቶች እየታገቱ የተጋነነ ገንዘብ እየተጠየቁ የቻሉ ከፍለው ሲወጡ ያልቻሉ ተገድለዋል። አንዳንዶቹ የተጠየቁትን ገንዘብ ከፍለውም አልተለቀቁም። ሰሜን ሸዋ ላይ አንድ ሙስሊም ባለሃብት ታግቶ ሶስት ጊዜ ጠመንጃ አስገዝተውታል። ሆኖም ግን እስከ ቅርብ ጊዜ ባለኝ መረጃ አልለቀቁትም። አሁን ደግሞ እገታው መልኩን ቀይሮ ሌሊት ላይ በቡድን ሆነው እየመጡ በር እየሰበሩ ነው እያገቱ ያሉት።
5ኛ፦ በተደጋጋሚ መስጂዶች ላይ ጥቃት እየፈፀሙ ነው።
6ኛ፦ ይህ ሁሉ ሲሆንም ቡድኑና ደጋፊዎቹ ለይስሙላ ያክል እንኳ በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን የተናጠል ጥቃት አምነው ሲያወግዙ አይሰሙም። ይህን ከማድረግ ይልቅ ሽምጥጥ አድርገው መካድን የሙጥኝ ብለዋል። አሁን አሁን መረጃዎች እየበዙ ሲመጡ ደግሞ መንግስት ነው አውቆ ሙስሊሞችን እየገደለ ልዩነት ለመፍጠር የሚሰራው እያሉ ነው። ይሄ አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው። ብዙ ቦታ ላይ በስም ተለይተው የሚታወቁ ፋኖዎች ጭምር ናቸው ጥቃቱን እየፈፀሙ ያሉት። የመንግስት ጥፋት እነዚህ አረመኔዎች ላይ በቂ እርምጃ አለመውሰዱ ነው።
7ኛ፦ በተደጋጋሚ “ነባሩ እስልምና” እና “ወሃብያ” እያሉ በሙስሊሙ የውስጥ ጉዳይ ገብተው እያቦኩ ነው። በተደጋጋሚ ልክ ለኢስላምና ለሙስሊሞች የሚቆረቆሩ ይመስል “ነባሩ እስልምና ተገፋ" እያሉ ለአሕባሽ ውግንናቸውን እያሳዩ ነው። ይህን የሚያደርጉት ለሁለት አላማ ነው። አንድም በዘር ትብታብ የተጠለፉ ሙስሊሞችን ለማደንዘዝ ነው። ሁለትም ሙስሊሞችን ለማጥቃት የአሕባሽ ቡድን ጥሩ አጋር ስለሚሆናቸው ነው።
8ኛ፦ ጊዜያዊውን መጅሊስ የብልፅግና መንግስት ደጋፊ ነው በሚል ማመሃኛ በመጅሊሱ መዋቅር ውስጥ የገቡ ሙስሊሞችን እስከመግደል ደርሰዋል።
9ኛ፦ ሰሜን ሸዋ ላይ አርጎባዎችን አብራችሁን ካልተሰለፋችሁ በሚል ተደጋጋሚ ዛቻዎችንና ትንኮሳዎችን ፈፅመዋል። ስለ ምክንያቶቹ ዝርዝር ማጣራት የሚሹ ቢሆኑም የተፈፀሙ ግድያዎችም አሉ።
10ኛ፦ ቤተ ክርስቲያናትና ገዳማትን የመሳሪያ ማከማቻና የጥቃት ማቀነባበሪያ ማዕከላት ካደረጉ በጣም ቆይተዋል።

ይህን ሁሉ እያደረገም “ወለጋ ላይ አማራ ሙስሊሞች በብሄራቸው ሰበብ ሲገደሉ የት ነበራችሁ?” የሚል ቁማር እየተጫወተ ነው። ቁማሩ ሰርቶለት አንዳንድ በዘር ትብታብ የተተበተቡ ሞኞችን ጠልፎለታል።
1ኛ፦ ብሄር እያዩ በሬሳ ቁማር መስራት የፖለቲከኛ ስራ ነው። ኦሮሞ ሆኑ አማራ ወይም ሌላ፡ ዘር እያዩ ጥላቻና ውግንና ከሚያሳዩት ጋር ይህን ብትሉ ልክም ባይሆን የሆነ ያክል ስሜት ይሰጥ ነበር። ትላንት ስንጮህ ለነበርነው ግን ይህን ማለት አትችሉም።
2ኛ፦ የወለጋውን ኬዝ የምታነሱትም ለማታገያነት ስለሚጠቅማችሁ እንጂ ለሰለባዎቹ ተቆርቁራችሁ አይደለም። ብትቆረቆሩማ በብሄር የሚመስሏችሁን አካላት በእምነት እየለያችሁ ባላጠቃችሁ ነበር።
3ኛ፦ ሂሳባችሁ የጅል ሂሳብ ነው። ኦሮሚያ ውስጥ ሲገደሉ ዝም ስላላችሁ አማራ ውስጥ ስንገድልም አትናገሩን ነው እያላችሁ ያላችሁት። ይህም ብልጠት ሆኖ ሰው ሲሸውድ አስቡት እንግዲህ።

የሚደንቀው በእንዲህ አይነት ጅላጅል ብልጠታቸው የጠለፉት ሙስሊም መኖሩ ነው። በነገራችን ላይ እነዚህን አካላት እየደገፉ ያሉ ሙስሊሞች 3 አይነት ናቸው።
1ኛው፦ በመጅሊስ ጉዳይ ያኮረፈ አሕባሽ ነው። እነዚህ በማህበራዊ ሚዲያ ብቻ አይደለም ለፋኖ እየታገሉ ያሉት። ይልቁንም ጫካ ጭምር ገብተው አብረው የተሰለፉ አሉ። በአንዳንድ ቦታዎች ሙስሊሞች ላይ ከሚደርሱ ጥቃቶች ጀርባ የእነዚህ አካላት ጥቆማና ተሳትፎ አለ።
2ኛው ክፍል ምክንያቱ ብሄር ወለድ ቅራኔ ነው። የመንግስትን ፖለቲካ፣ ኦሮሚያ ላይ የደረሱ ዘር ተኮር ጥቃቶችን እንደ ግብአት ይጠቀማል። ይሄ ክፍል በክልሉ ውስጥ ሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እያወቀ አንዴ መንግስት ነው፣ አንዴ ውሸት ነው እያለ ራሱን የሚያታልል ነው። ውጭ ሃገር ሆነው የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉትም ብዙዎቹ በዚህ ምድብ ስር የሚካተቱ ናቸው።
3ኛው ክፍል፦ በተለያዩ የአስተዳደር ችግሮች መነሻ በክልሉ ውስጥ ወይም በታችኛው የመንግስት መዋቅር ላይ ያቄመ አካል ነው። ነገሮችን አርቆ የሚመለከትበት በቂ ንቃት የለውም። የሌሎችን ጩኸት ከማስተጋባት ባለፈ የረባ የተዋቀረ ሃሳብም የለውም። ጉዞው እንዲሁ የደመነፍስ ነው።

ለጊዜው እዚህ ላይ ላቁም። ምናልባት በቀሪ ሃሳቦች ልመለስ እችላለሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
19.4K viewsedited  12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 13:25:56 ከሰው ተበድሮ ስራ የሚሰራ ሰው ዘካ የሚመለከተው ከእዳው ውጭ ባለው ቀሪ ገንዘብ ላይ ነው። እጁ ላይ ያለው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ የሰው እዳ ከሆነ ወይም ከዘካ መጠን ያነሰ ከሆነ ምንም ዘካ የለበትም። ይህንን ነጥብ ቀደም ብዬ ገልጨዋለሁ። ደግሜ የማነሳው እጃችሁ ላይ ባለ የብድር ገንዘብ ዘካ ማውጣት አለባችሁ የሚሉ ሰዎችን ስለሰማሁ ነው። በርግጥ ይህንን ሃሳብ ያንፀባረቁ ዓሊሞች አሉ። ቢሆንም ግን ልክ አይደለም።
1ኛ:- ይሄ አሰራር ሰዎች የራሳቸው ባልሆነ ገንዘብ ላይ ዘካ ያውጡ ማለት ነው። ዘካ የሚመለከተው ባለ ገንዘቡን ነው።
2ኛ፦ በዚያ ላይ አንድ የብድር ገንዘብ አበዳሪው ቢጠይቅ የሚያገኘው ከሆነ ዘካ ሊያወጣበት ይገባል። ተበዳሪውም የዚሁኑ ገንዘብ ዘካ ያውጣ ከተባለ ግን ከአንድ ገንዘብ ላይ በአንድ አመት ውስጥ ሁለት ጊዜ ዘካ ማውጣት ይገባል ማለት ነው። ይሄ ልክ ያልሆነ አሰራር ነው።
ዝርዝር የፈለገ የሸይኽ ሙሐመድ 0ሊይ ኣደምን አልበሕሩል ሙሒጥ ኪታብ ይመልከት።
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
16.7K views10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 22:38:43 ዛሬ እሁድ መግሪብ ሰዓት ላይ ባህር ዳር ከተማ ውስጥ 3 ሙስሊም ባለ ሃብቶች በፋኖ ተገድለዋል። ሟቾቹ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው። (አባትና ሁለት ወንድማማቾች ናቸው።) ግድያው የተፈፀመው በከተማው ቀበሌ 14 ውስጥ ነው። የግድያው መንስኤ ብር ካላመጣችሁ የሚል ነው። በዚህ የገዳይ ስብስብ ፕሮፖጋንዳ የተጠለፉ እስከሚነቁ ድረስ ማንቃታችንን እንቀጥላለን፣ ኢንሻአላህ።
የሞቱትን አላህ ይማራቸው።
=
ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
19.8K views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 18:22:03 ይድረስ!
~
1- ይድረስ ሚስትህን ለፈታኸው፡
ልጆችህን ለዒድ አስበሃቸዋል? ወይስ እነሱንም ከናታቸው ጋር ፈተሃቸዋል?

2- ይድረስ የየቲሞች አጎት ለሆንከው፡
የሟች ወንድምህን ልጆች ትጠይቃለህ? ወይስ ከቀበርከው ወንድምህ ጋር ረስተሃቸዋል?

3- ይድረስ ባሏ የሞተባት እህት ያለችህ :
እህትህን ትኑር ትሙት ጠይቀሀል? በልታለች ወይስ ተርባለች? ወይስ እህትነቷ ቁጥር ብቻ ነው?

ይድረስ ለሁላችን፡

እጃችንን የሚጠብቁ፣ ከኛ የቀረበ ሰው የሌላቸው ቤተሰቦቻችን በምን ላይ ናቸው? በዒድ በምን መልኩ እንዲያስታውሱን እንፈልጋለን? ያቅማችንን ያክል ከልባቸው ውስጥ ደስታ ማስገባት ያሳስበናል? ወይስ ሀዘን ትካዜያቸው ምንም አይመስለንም?!
-
ተነካክቶ ከዐረብኛ የተመለሰ
=
https://t.me/IbnuMunewor
13.9K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 10:01:24 በየተክቢራዎቹ እጅን እስከ ትከሻ ወይም ጆሮ ድረስ ማንሳት ከሰለፎች ተገኝቷል። [ሙሶነፍ ዐብዲረዛቅ፡ 5699] ይሄ የብዙሃኑ ዑለማእ አቋም እንደሆነም በገዊይ ጠቅሰዋል። [ሸርሑ ሱናህ፡ 4/310]
4.9. በየተክቢራዎቹ መሃል የሚባልን ዚክር በተመለከተ ከነብዩ ﷺ የተላለፈ ሶሒሕ ማስረጃ የለም። (ክፍተቱ ካለ) አላህን ማመስገንና በነብዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማውረድ እንደሚቻል ከኢብኑ መስዑድ ተገኝቷል። [አልኢርዋእ፡ 642]
4.10. የተክቢራዎቹን ቁጥር የተጠራጠረ እርግጠኛ የሆነበትን ዝቅተኛውን ይዞ ቀሪውን ይሞላል።
4.11. ልክ እንደሌሎች ሶላቶች የመክፈቻ ዱዓእ መቅራቱ ተገቢ ሲሆን ቦታውም ከመክፈቻው ተክቢራ ቀጥሎ ከተጨማሪዎቹ ተክቢራዎች በፊት መሆን እንዳለበት የብዙሃን ዑለማዎች እይታ ነው።
4.12. ፋቲሐን መቅራት ግዴታ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለኢማሙ ሱረቱል አዕላን እና ሱረቱል ጋሺያን ወይም ሱረቱል ቃፍና ሱረቱል ቀመርን መቅራቱ ከሱና ነው። [ሙስሊም] ለኢማሙ በቂራአህ ድምፅን ከፍ ማድረግ ሱና ነው።
4.13. የዒድ ሰላት ያለፈው ሰው ሳይሰላመት ከደረሰ ያገኘውን አብሮ ሰግዶ ያለፈውን ይሞላል። ከተሰላመተ በኋላ የደረሰ ደግሞ ካገኘ ከሰዎች ጋር ካልሆነ ብቻውንም ቢሆን ይሰግዳል። በሆነ ምክንያት ወደ መስገጃው ቦታ መውጣት ያልቻሉ ከቤታቸውም ቢሆን መስገድ ይችላሉ። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 369]፣ [ቡኻሪይ፣ ተዕሊቅ፡ 2/471]
4.14. ከዒድ ሶላት በፊትም በኋላም ከመስገጃው ቦታ የሚሰገድ መደበኛ ሱና የለም። ቤት ከተመለሱ በኋላ ግን ነብዩ ﷺ 2 ረከዐ ይሰግዱ ነበር። [ቡኻሪይ]፣ [አልኢርዋእ፡ 3/100] የዒዱ ሶላት የሚሰገደው መስጂድ ውስጥ ከሆነ ግን መስጂድ እንደገባን የዒድ ሱና ሳይሆን “ተሒየተል መስጂድ” መስገድ አለብን።
4.15. ዒድ መሆኑ ከእኩለ-ቀን በኋላ ከታወቀ በቀጣዩ ቀን ይሰገዳል። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1050]
4.16. ዒድድና ጁሙዐ በአንድ ቀን ከገጠሙ፡- የዒድ ሶላትን የሰገደ ሰው ጁሙዐ ሰላት ላይ የመገኘት ግዴታ የለበትም። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 984]

5. ኹጥባ፡-
5.1. የሚደረገው ከሶላት በኋላ ነው። [ቡኻሪይ፡ 963] [ሙስሊም፡ 888]
5.2. ለኹጥባው ሚንበር ይዞ መውጣት ከሱና አይደለም። [ቡኻሪይ፡ 956]
5.3. ኹጥባው አንዳንዶች እንደሚሉት አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ነው። ከሰለፎች የተገኘው በዚህ መልኩ ነው። ኢብኑ ሐዝም የዑለማእ ስምምነት አለበት ብለዋል። [አልሙሐላ: 3/543] ዝርዝር የፈለገ በዚህ ሊንክ ይግባ። https://rb.gy/m3wrx
5.4. ኹጥባውን ማዳመጡ ግዴታም ባይሆን ተወዳጅ ነው። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2289]
5.5. ኹጥባው እየተደረገ ወሬ ማውራት አይገባም።

6. የዒድ ቀን ምግብ፡-
6.1. ዒደል ፊጥርን እና ዒደል አድሐን መፆም ፈፅሞ አይፈቀድም! [ቡኻሪይና ሙስሊም] እንዲሁም ከዒደል አድሐ በኋላ ያሉትን ሶስቱን ቀናትም (አያመ ተሸሪቅ) ሐጅ ላይ ሆኖ እርድ ያላገኘ ሰው ካልሆነ በስተቀር ለሌሎች መፆም አይፈቀድም። [ቡኻሪይ] [አሶሒሐ፡ 3573]
6.2. በዒደል ፊጥር ቀን ወደ ሶላት የሚውወጣው ከተመገቡ በኋላ ነው። የዒደል አድሐ ቀን ግን ሳይመገቡ ወጥቶ ከሶላት በኋላ መመገብ ከሱና ነው። [ቡኻሪይና ሙስሊም] [ሙስነድ አሕመድ፡ 23042]
6.3. በዒደል ፊጥር የምንመገበው ተምር ቢሆንና በተናጠል በዊትር ብንበላው የነብዩ ﷺ ሱና ነው። [ቡኻሪይ] ተምር ከሌለ ቤት ያፈራውን በመቅመስ በልቶ የመውጣቱን ሱና ልንተገብር ይገባል።
6.4. በዒደል አድሐ ቀን ከሶላት መልስ መጀመሪያ የሚፈፀመው መመገብ ሳይሆን ኡዱሒያን ማረድ ነው። [ሙስነድ አሕመድ፡ 23042]
አላህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን። ኣሚን።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 22/2007)
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
15.0K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-07 10:01:24 ዒድ - ህግጋትና ስርአቱ
~
በኢስላም አመታዊ በአሎቻችን ሁለት ናቸው። እነሱም ዒደል ፊጥርና ዒደል አድሐ። የመጀመሪያው ረመዳን እንዳለቀ በሸዋል ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ ይውላል። ሁለተኛው - ዒደል አድሐ- ደግሞ የዙልሒጃ ወር በ10ኛው ቀን ላይ። ነብዩ ﷺ መዲና ሲገቡ የመዲና ሰዎች የሚጫወቱባቸው ሁለት በአላት ነበሯቸው። “ምንድን ናቸው እነኚህ ቀናት?” ሲሉ ጠየቁ መልእክተኛው ﷺ። እነሱም “ከጃሂሊያህ ዘመን ጀምሮ የምንጫወትባቸው ቀናት ናቸው” ብለው መለሱ። ነብዩ ﷺ “አላህ ከነሱ በተሻሉ ቀናት ተክቷችኋል፡- በአድሐ ቀን እና በፊጥር ቀን” አሉ። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1039]

ጥቂት ስለዒድ፡-

1. ቀኑ የደስታ ቀን ነው፡-
1.1. “ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም” እያሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጥ ከሶሐቦች ተገኝቷል። [አልፈታዋ፡ 24/253]
1.2. ልጃገረዶች እየዘፈኑ መጫወት ይችላሉ። [ቡኻሪ፡ 949] [ሙስሊም፡ 892]
1.3. እለቱ የደስታ፣ የመብያና የመጠጫ ቀን ነው። [ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 777]
1.4. ስለሆነም ቀብር ዚያራና የመሳሰሉ የእለቱን የደስታ ድባብ የሚያደፈርሱ ድርጊቶችን መፈፀም አይገባም። [አልኢብዳዕ፡ 263]
1.5. የምንደሰትበት ግን ፈፅሞ በሐራም ነገር መሆን የለበትም። “የትም ብትሆን አላህን ፍራ!” የሚለው ሐዲሥ አይረሳ።

2. ተክቢራ፡-
2.1. የሚባልበት ጊዜ፡-
* በዒደል ፊጥር - የረመዷን ወር መጨረሻ ቀን ፀሐይ ከጠለቀችበት ወይም የሸዋል ጨረቃ ከታየችበት ጊዜ ጀምሮ ነው። ምክንያቱም አላህ ተክቢራውን ከረመዷን ፍፃሜ ጋር አያይዞ ነውና የገለፀው። [አልበቀረህ፡ 185] ተክቢራው እስከ ዒድ ሰላት ድረስ ይዘልቃል።
* በዒደል አድሐ - ደግሞ ከዐረፋ ቀን ፈጅር ሶላት አንስቶ እስከ ዙልሒጃ 13 ዐስር ድረስ ከግዴታ ሰላቶች በኋላ ተክቢራ ማድረጉ ከሶሐቦች ተገኝቷል። [አልኢርዋእ፡ 653] እንዲያውም ኢጅማዕ (ወጥ ስምምነት) የመጣበት ጉዳይ እንደሆነ ነወዊይና ኢብኑ ረጀብ ጠቅሰዋል። [አልመጅሙዕ፡ 5/32] [ፈትሑል ባሪ] በዒደል ፊጥር ጊዜ ከግዴታ ሶላቶች በኋላ ተክቢራ ማድረጉ በቂ ማስረጃ የለውም።
2.3. አደራረጉ፡- ሁሉም በየፊናው እንጂ አንዱ እያወጣ ሌሎች በመከተል በህብረት ባንድ ድምፅ አይባልም። [መጅሙዑፈታዋ ኢብኒ ባዝ፡ 13/21] ባይሆን ይሄ ጉዳይ በዑለማዎች የተለያየ ሀሳብ የተሰነዘረበት ፊቅሃዊ ጉዳይ እንደመሆኑ ጉዳዩን በልኩ መያዝ ይገባል።
2.4. ድምፅን በተክቢራ ከፍ ማድረግ የተወደደ ነው። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 4934]
2.5. ተክቢራው ሴቶችንም በተመሳሳይ የሚመለከት ነው። [ቡኻሪና ሙስሊም] ድምፃቸውን ግን ዝቅ ሊያደርጉ እንደሚገባ ዑለማዎች ይመክራሉ።
2.5. አንዳንድ አካባቢዎች እንደሚታየው በተክቢራ ሙሉ ሌሊቱን ሳይተኙ ማሳለፍ፣ ሰፈር ጎረቤቱን በከፍተኛ ድምፅ ማወክ ማስረጃ የሌለው ስራ ነው። “የሁለቱን ዒድ ሌሊቶች ነቅቶ ያደረ ሰው ልቦች በሚሞቱበት ቀን ልቡ አይሞትም” የሚለው “ሐዲሥ” በነብዩ ﷺ ላይ የተቀጠፈ እንጂ ጤነኛ መረጃ አይደለም። [አዶዒፋህ፡ 520]
2.6. ከሶሐቦች የተለያዩ የተክቢራ አፈፃፀሞች የመጡ ሲሆን የተለየ አይነት ገደብ የለውም። ከሰሐቦች የተገኙትን መያዙ በላጭ ነው።
2.7. እነዚህን ተክቢራዎች ማለት በጀማዐ ለሰገደም፣ ብቻውን ለሰገደም የተወደደ ነው። ግዴታ ግን አይደለም። [ሸርሑል ሙምቲዕ፡ 5/165]

3. ወደ መስገጃው ቦታ መውጣት፡-
3.1. ወደ መስገጃ ቦታ ሲወጣ መታጠብን፣ ሽቶ መቀባትን የሚመለከት ከሶሐቢዩ ኢብኑ ዑመር ተገኝቷል። [አልኢርዋእ፡ 104] ከነብዩ ﷺ ግን ምንም የለም። የመታጠቢያ ጊዜውም ከእለቱ ፈጅር ሶላት መልስ ቢሆን ይመረጣል። ይህን የሚያመላክት ከሰለፎች ተገኝቷል። [አልመጣሊቡል ዓሊያህ፡ 2753]፣ [አሕካሙል ዒደይን ሊልፊርያቢይ፡ 16] ትጥበቱም ሴት ከወንድ፣ ህፃን ከአዋቂ ሳይለይ ሁሉንም እንደሚመለከት ነወዊይ ጠቁመዋል። [አልመጅሙዕ፡ 2/233]
3.2. በእለቱ አቅም በፈቀደ ባማረ ልብስ ሽክ ማለት ተወዳጅ ነው። [ቡኻሪና ሙስሊም]
3.3. ለቻለ ሰው ወደ መስገጃው ቦታ በእግር መሄዱ ሱና ነው። [አልኢርዋእ፡ 636]
3.4. የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ወደ መስገጃው ሜዳ መውጣታቸው ከሱና ነው። ከመስገጃው ቦታ ግን ገለል ይላሉ። [ቡኻሪ] ሴቶች ወደ መስገጃው ቦታ ሲወጡ ሽቶ ከመቀባትና ካላስፈላጊ አለባበስ መራቅ አለባቸው።
3.5. ስጋትና እንቅፋት ከሌለ ልጆችም ሊወጡ እንደሚችሉ የሚጠቁም ማስረጃ አለ። [ቡኻሪ፡ 977] ባይሆን ሰጋጆችን እንዳይበጠብጡ ወላጆች ሊቆጣጠሯቸው ይገባል።
3.6. ከመስገጃው ቦታ ሲመለሱ መንገድ ቀይሮ መመለሱ በላጭ ነው። [ቡኻሪ፡ 986]

4. የዒድ ሶላት፡-
4.1. ሶላቱን በተመለከተ ሚዛን የሚደፋው አቋም “ግዴታ ነው” የሚለው እንደሆነ ኢብኑ ተይሚያ፣ ሶንዓኒይ፣ ሲዲቅ ሐሰን ኻን፣ ሸውካኒይ፣ አልባኒይ፣ ኢብኑ ዑሠይሚን እና ሌሎችም አስረግጠው ተናግረዋል።
4.2. ወቅቱ፡- ፀሀይ ወጥታ የጦር ቁመት ያክል ከፍ ካለች ጀምሮ በአናት ትይዩ እስከምትሆን ድረስ ያለው ነው። የዒደል ፊጥር ሶላት ዘግየት፣ የዒደል አድሐ ደግሞ ቀደም ቢል ተመራጭ ነው። [አተልኺስ፡ 144] [ሙስነዱ ሻፊዒይ፡ 74] ምክንያቱም የዒደል ፊጥር ጊዜ ዘግየት ማለቱ ዘካተል ፊጥር ለሚሰጡ ሰዎች ጊዜ እንዲኖራቸው ሲያደርግ የዒደል አድሐ ጊዜ ቀደም ማለቱ ደግሞ ከሶላት ቶሎ ተመልሰው ኡዱሒያ የሚያርዱበት ጊዜ እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል።
4.3. የሚሰገድበት ቦታ፡- ዝናብ፣ የፀጥታ ስጋት፣ ወዘተ ካልኖረ ወጣ ያለ ሰፊ ሜዳ ላይ መሆኑ ሱና ነው። [ቡኻሪይና ሙስሊም]
4.4. ለዒድ ሶላት አዛንም ኢቃማም አይደረግም። [ቡኻሪይ፡ 962] [ሙስሊም፡ 886]
4.5. የረከዐው ብዛት፡- 2 ነው። [ቡኻሪይ፡ 964] [ሙስሊም፡ 884]
4.6. የዒድ ሶላት ውስጥ ያሉት ተጨማሪ ተክቢራዎቹ ሙስተሐብ እንጂ ግዴታ አይደሉምና በመርሳትም ሆነ ሆን ተብሎ ቢቀሩ ሶላቱ አይበላሽም። [አልሙግኒ፡ 3/275]
4.7. ቁጥራቸውም የመጀመሪያው ረከዐ ላይ ከመክፈቻው ተክቢራ ውጭ 7፤ ሁለተኛው ረከዐ ላይ ደግሞ ከመነሻው ተክቢራ ውጭ 5 ተክቢራ ነው። ይሄ ከብዙሃኑ ሶሐቦችና አኢማዎች የተገኘው እንደሆነ ኢብኑ ተይሚያ ገልፀዋል። [አልፈታዋ፡ 24/220] ብዙሃኑ ዑለማዎች ያሉትም እዚህ ላይ ነው። ባይሆን የመጀመሪያውን 7 የሁለተኛውን ስድስት፣ የመጀመሪያውን 6 የሁለተኛውን 5 ማድረጉም ተገኝቷል። 4፣ 11፣ 12፣ 13 ተክቢራዎችን ማለት እንደሚቻልም ከሰለፎች ተገኝቷል። ከዚህ በመነሳት ነገሩ ሰፊ እንደሆነና በሶሒሕ ማስረጃ በመጡት ሁሉ መስራት እንደሚቻል ያሳያል ይላሉ ሸይኹል አልባኒይ ረሒመሁላህ። [አልኢርዋእ፡ 639]
4.8. በተጨማሪ የዒድ ተክቢራዎች ላይ እጅን ማንሳት ከሶሐቦች፣ ከዐጣእ፣ አውዛዒይ፣ አቡ ሐኒፋህ፣ ሻፊዒይ፣ አሕመድና ሌሎችም ተገኝቷል። ነብዩ ﷺ ደግሞ ጥቅል በሆነ መልኩ የሶላት ተክቢራዎች ላይ እጃቸውን ያነሱ እንደነበር ማስረጃ አለ። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 715]
13.3K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ