Get Mystery Box with random crypto!

በየተክቢራዎቹ እጅን እስከ ትከሻ ወይም ጆሮ ድረስ ማንሳት ከሰለፎች ተገኝቷል። [ሙሶነፍ ዐብዲረዛቅ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

በየተክቢራዎቹ እጅን እስከ ትከሻ ወይም ጆሮ ድረስ ማንሳት ከሰለፎች ተገኝቷል። [ሙሶነፍ ዐብዲረዛቅ፡ 5699] ይሄ የብዙሃኑ ዑለማእ አቋም እንደሆነም በገዊይ ጠቅሰዋል። [ሸርሑ ሱናህ፡ 4/310]
4.9. በየተክቢራዎቹ መሃል የሚባልን ዚክር በተመለከተ ከነብዩ ﷺ የተላለፈ ሶሒሕ ማስረጃ የለም። (ክፍተቱ ካለ) አላህን ማመስገንና በነብዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማውረድ እንደሚቻል ከኢብኑ መስዑድ ተገኝቷል። [አልኢርዋእ፡ 642]
4.10. የተክቢራዎቹን ቁጥር የተጠራጠረ እርግጠኛ የሆነበትን ዝቅተኛውን ይዞ ቀሪውን ይሞላል።
4.11. ልክ እንደሌሎች ሶላቶች የመክፈቻ ዱዓእ መቅራቱ ተገቢ ሲሆን ቦታውም ከመክፈቻው ተክቢራ ቀጥሎ ከተጨማሪዎቹ ተክቢራዎች በፊት መሆን እንዳለበት የብዙሃን ዑለማዎች እይታ ነው።
4.12. ፋቲሐን መቅራት ግዴታ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ለኢማሙ ሱረቱል አዕላን እና ሱረቱል ጋሺያን ወይም ሱረቱል ቃፍና ሱረቱል ቀመርን መቅራቱ ከሱና ነው። [ሙስሊም] ለኢማሙ በቂራአህ ድምፅን ከፍ ማድረግ ሱና ነው።
4.13. የዒድ ሰላት ያለፈው ሰው ሳይሰላመት ከደረሰ ያገኘውን አብሮ ሰግዶ ያለፈውን ይሞላል። ከተሰላመተ በኋላ የደረሰ ደግሞ ካገኘ ከሰዎች ጋር ካልሆነ ብቻውንም ቢሆን ይሰግዳል። በሆነ ምክንያት ወደ መስገጃው ቦታ መውጣት ያልቻሉ ከቤታቸውም ቢሆን መስገድ ይችላሉ። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 369]፣ [ቡኻሪይ፣ ተዕሊቅ፡ 2/471]
4.14. ከዒድ ሶላት በፊትም በኋላም ከመስገጃው ቦታ የሚሰገድ መደበኛ ሱና የለም። ቤት ከተመለሱ በኋላ ግን ነብዩ ﷺ 2 ረከዐ ይሰግዱ ነበር። [ቡኻሪይ]፣ [አልኢርዋእ፡ 3/100] የዒዱ ሶላት የሚሰገደው መስጂድ ውስጥ ከሆነ ግን መስጂድ እንደገባን የዒድ ሱና ሳይሆን “ተሒየተል መስጂድ” መስገድ አለብን።
4.15. ዒድ መሆኑ ከእኩለ-ቀን በኋላ ከታወቀ በቀጣዩ ቀን ይሰገዳል። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1050]
4.16. ዒድድና ጁሙዐ በአንድ ቀን ከገጠሙ፡- የዒድ ሶላትን የሰገደ ሰው ጁሙዐ ሰላት ላይ የመገኘት ግዴታ የለበትም። [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 984]

5. ኹጥባ፡-
5.1. የሚደረገው ከሶላት በኋላ ነው። [ቡኻሪይ፡ 963] [ሙስሊም፡ 888]
5.2. ለኹጥባው ሚንበር ይዞ መውጣት ከሱና አይደለም። [ቡኻሪይ፡ 956]
5.3. ኹጥባው አንዳንዶች እንደሚሉት አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ነው። ከሰለፎች የተገኘው በዚህ መልኩ ነው። ኢብኑ ሐዝም የዑለማእ ስምምነት አለበት ብለዋል። [አልሙሐላ: 3/543] ዝርዝር የፈለገ በዚህ ሊንክ ይግባ። https://rb.gy/m3wrx
5.4. ኹጥባውን ማዳመጡ ግዴታም ባይሆን ተወዳጅ ነው። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2289]
5.5. ኹጥባው እየተደረገ ወሬ ማውራት አይገባም።

6. የዒድ ቀን ምግብ፡-
6.1. ዒደል ፊጥርን እና ዒደል አድሐን መፆም ፈፅሞ አይፈቀድም! [ቡኻሪይና ሙስሊም] እንዲሁም ከዒደል አድሐ በኋላ ያሉትን ሶስቱን ቀናትም (አያመ ተሸሪቅ) ሐጅ ላይ ሆኖ እርድ ያላገኘ ሰው ካልሆነ በስተቀር ለሌሎች መፆም አይፈቀድም። [ቡኻሪይ] [አሶሒሐ፡ 3573]
6.2. በዒደል ፊጥር ቀን ወደ ሶላት የሚውወጣው ከተመገቡ በኋላ ነው። የዒደል አድሐ ቀን ግን ሳይመገቡ ወጥቶ ከሶላት በኋላ መመገብ ከሱና ነው። [ቡኻሪይና ሙስሊም] [ሙስነድ አሕመድ፡ 23042]
6.3. በዒደል ፊጥር የምንመገበው ተምር ቢሆንና በተናጠል በዊትር ብንበላው የነብዩ ﷺ ሱና ነው። [ቡኻሪይ] ተምር ከሌለ ቤት ያፈራውን በመቅመስ በልቶ የመውጣቱን ሱና ልንተገብር ይገባል።
6.4. በዒደል አድሐ ቀን ከሶላት መልስ መጀመሪያ የሚፈፀመው መመገብ ሳይሆን ኡዱሒያን ማረድ ነው። [ሙስነድ አሕመድ፡ 23042]
አላህ መልካም ስራዎቻችንን ይቀበለን። ኣሚን።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 22/2007)
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M