Get Mystery Box with random crypto!

ከሰው ተበድሮ ስራ የሚሰራ ሰው ዘካ የሚመለከተው ከእዳው ውጭ ባለው ቀሪ ገንዘብ ላይ ነው። እጁ ላ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ከሰው ተበድሮ ስራ የሚሰራ ሰው ዘካ የሚመለከተው ከእዳው ውጭ ባለው ቀሪ ገንዘብ ላይ ነው። እጁ ላይ ያለው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ የሰው እዳ ከሆነ ወይም ከዘካ መጠን ያነሰ ከሆነ ምንም ዘካ የለበትም። ይህንን ነጥብ ቀደም ብዬ ገልጨዋለሁ። ደግሜ የማነሳው እጃችሁ ላይ ባለ የብድር ገንዘብ ዘካ ማውጣት አለባችሁ የሚሉ ሰዎችን ስለሰማሁ ነው። በርግጥ ይህንን ሃሳብ ያንፀባረቁ ዓሊሞች አሉ። ቢሆንም ግን ልክ አይደለም።
1ኛ:- ይሄ አሰራር ሰዎች የራሳቸው ባልሆነ ገንዘብ ላይ ዘካ ያውጡ ማለት ነው። ዘካ የሚመለከተው ባለ ገንዘቡን ነው።
2ኛ፦ በዚያ ላይ አንድ የብድር ገንዘብ አበዳሪው ቢጠይቅ የሚያገኘው ከሆነ ዘካ ሊያወጣበት ይገባል። ተበዳሪውም የዚሁኑ ገንዘብ ዘካ ያውጣ ከተባለ ግን ከአንድ ገንዘብ ላይ በአንድ አመት ውስጥ ሁለት ጊዜ ዘካ ማውጣት ይገባል ማለት ነው። ይሄ ልክ ያልሆነ አሰራር ነው።
ዝርዝር የፈለገ የሸይኽ ሙሐመድ 0ሊይ ኣደምን አልበሕሩል ሙሒጥ ኪታብ ይመልከት።
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M