Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.25K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 37

2023-09-07 20:50:35 ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:-
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 206፣ باب فضل البكاء
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
12.6K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-07 15:59:36 የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች
~
ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-

* ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

* ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

* ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

* ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

* ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።

3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-

* አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
* አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
* የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
* እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!
የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
16.0K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-07 06:52:07 ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሳቃቸው፣ ፈገግታቸው፣ ቁጣቸው፣ ሃዘናቸው፣ ለቅሷቸው፣ መልካቸው፣ ፂማቸው፣ ፀጉራቸው፣ ሽበታቸው፣ አነጋገራቸው፣ አካሄዳቸው፣ አለባበሳቸው፣ ... ዝርዝር ህይወታቸው በሶሐቦች ተላልፏል። አመት እየጠበቁ መውሊዳቸውን ያከብሩ እንደነበር ግን አንድም መረጃ የለም።

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል
Https://t.me/IbnuMunewor
13.2K views03:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-06 16:12:41 السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

1 # የዓብዱሶመድ ደርሶችን ለማግኘት ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ።

Abdulsemed M/Nur Qiraat
https://t.me/AbdulsemedMohammed

2 # የዓብዱሶመድ የፅሁፍ ፓስቶችን ለማግኘት ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ።

Abdulsemed M/Nur Text
https://t.me/AbdulsemedMNurTextPosts

3 # የዓብዱሶመድ የቪድዮ ደርሶችን እና ትምህርቶችን ለማግኘት ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ።

Abdulsemed M Qiraat Video
https://t.me/AbdulsemedQiraatVideo

4 # የዓብዱሶመድ ያለቁ ደርሶችን ለማግኘት ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ።

Abdulsemed MNur Yalequ Dersoch
https://t.me/AbdulsemedMnYalequ

ቂርኣትን በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት በዚህ ቁጥር ይላኩ።

+251937602141

https://t.me/AbdusomedMNur
13.5K views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-06 06:43:22 ተጨዋች መግዛት
~
ጥያቄ፦ የእግር ኳስ ተጨዋቾችን ከሌሎች ክለቦች በብዙ ሚሊዮኖች መግዛት ብይኑ ምንድነው?

መልስ፦
هذا لا يجوزُ هَذَا كُلُّهُ من أكلِ أموالِ النَّاسِ بالباطِلِ، وإن قالُوا اشتروهُم: هل الإنسَانُ الحُرُّ يشْتَرَى؟ وإذا قالوا يستأْجَرُ: قلنا: يستأجرْ لإيش؟ للعبِ!! اللَّعب فيه فائدَةٌ؟ لا، هذا كُلُّه من أكْلِ أموالِ النَّاسِ بالباطِلٓ.
ይሄ አይፈቀድም። ይሄ ሁሉ የሰዎችን ገንዘብ በከንቱ (ያላግባብ) ከመብላት ነው። "ገዝተናቸው ነው" ካሉ ነፃ የሆነ ሰው ይገዛልንዴ? "ተቀጥሮ ነው" ካሉ "ለምንድነው ነው የሚቀጠረው?" እንላለን። ለጨዋታ?! ጨዋታ ፋይዳ አለው? ፈፅሞ! ይሄ ሁሉ የሰዎችን ገንዘብ በከንቱ (ያላግባብ) ከመብላት ነው።

ሸይኽ ሷሊሕ አልፈውዛን
ምንጭ:-
عبد الملك الإبي

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
12.7K views03:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-04 14:41:31 ከመርከዘ ተውሒድ
~
ሒፍዝ ጨርሰው በወጡ ተማሪዎች ቦታ አዲስ ተማሪዎችን ስለምንቀበል የቁርኣን ሒፍዝ ፍላጎቱ ያላቸው መመዝገብ ይችላሉ።

~ መስፈርት ~

*እድሜ፦ ከ 12 ዓመት ያላነሰ
* በነዞር (በእይታ) የቀራ

ማሳሰቢያ፦ መርከዙ የወንዶች ብቻ ነው።

* ፍላጎቱ ያላችሁ በዚህ ቁጥር ወደወል ትችላላችሁ።
0968911032
16.2K viewsedited  11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-01 21:45:30 ደርስ
~
* ሪያዱ ሷሊሒን
* ክፍል:-
* የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 203፣ ሐዲሥ ቁ. 439
* የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
13.2K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-01 16:21:27 ሱብሀነሏህ እንዴት የሚደንቅ የፅናት ታሪክ ነው
------
በ1977 በኢትዮጵያ በነበረው ድርቅ ምክኒያት የተፈጠረውን ርሃብ ተከትሎ የተከሰተውን ይህን አሳዛኝ ታሪክ ሌላ ሰው ቢያወራው ኖሮ ለማመን ይከብድ ነበር ነገር ግን ይህን ታሪክ የሚናገሩት ኩዌይታዊ ሼኸ ዶ/ር አብዱራህማን አስ-ሰሚጥ ናቸውና ለማመን እንገደዳለን አላህ ይማራቸውና በአፍሪካ አህጉር ከ11ሚሊዮን በላይ ሠዎችን ያሰለሙ ሸይኽ ናቸው

ታሪኩ እንዲህ ነው በ1977 አንድ የክርሰትያን በጎ አድራጊ ማህበር ከሰሜን አሜሪካ እርዳታ ለመሰጠት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣና በቀጥታ ድርቅና ርሃብ ወደ ተከሰተበት ገጠር ሂደው እርዳታ መሰጠት ይጀምራሉ ከዚያም የመስጂድ ኢማም የሆኑ አንድ ትልቅ ሠው እርዳታ ለመቀበል ይመጣሉ አሜሪካዊው እርዳታ ሰጪ ሲያያቸው የሀይማኖት አባት መሆናቸውን አውቆ ክርሰትያን እንዲሆኑ ጠየቃቸው እሳቸውም «ክርሰትያን አልሆንም የምትሰጠኝ ከሆነ ሰጠኝ» አሉት አሜሪካዊውም «እሺ አሁን በህዝብ ፊት በውሸት ክርሰትያን ሁኜያለሁ በል እና የፈለግከውን እሰጥሃለሁ» አላቸው እሳቸውም «በውሸትም በእውነትም አልልም ሀይማኖቴን አልቀይርም አሉት» ሰውየው ተናደደ እና «በቃ የሚሰጥ የለንም» ብሎ መለሳቸው ኢማሙ ባዶ እጃቸውን ወደ ቤታቸው ተመለሱ የሳቸው ቤተሰብም ጨርሶ እርዳታ ሳያገኝ ቀረ ፥

ከ3 ወራት በኋላ ይህን ታሪክ የሰሙት ኩዌታዊ ሸይኽ አብዱራህማን እንዲህ ይላሉ «ይህን ወሬ ከሰማሁኝ በኋላ በቀጥታ ከኩዌት ወደ ኢትዮጵያ ሄድኩኝ እና እኚህ ኢማም ወደ ሚኖሩባት አካባቢ ተጓዝን እንደ ደርሰን በአካባቢው ሰው የሚባል የለም ሁሉም ድርቁን ሽሽት አካባቢውን ለቀውት ሄደዋል ይዘውኝ የሄዱት ሰዎች የኢማሙን ቤት አሳዩኝና በራቸውን አንኳኳን የሚከፍትልን ስናጣ በሩን ገፋ አድርጌ ገባሁ ያየሁት ነገር እጅግ ዘግናኝ እና አስደንጋጭ ነበር አይኔን ማመን ከበደኝ ኢማሙ ሚሰታቸው እና ልጆቻቸው ሁሉም እንደተኙ በርሃብ ሙተዋል የአጥንታቸው ሃይከል ብቻ ተኝቶ አገኘሁት ፥ «በርሃብ እንሞታለን እንጂ ሀይማኖታችንን አንቀይርም» ብለው የሞቱ የሀበሻ ቤተሰብ አይቼ ተመለሰኩኝ ፥ በተጨማሪ እነዚያ በክርሰትና ስም ይዘውት የመጡት እርዳታ የኛ የአረብ አገሮች እና የሌሎች የመላው የአለም ህዝብ አዋጥተን ለተባበሩት መንግሰታት ድርጅት በሰብአዊነት የሰጠነው እርዳታ ነበር እነርሱ ግን በእንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታ አከፋፍለውታል» ሲሉ ታሪኩን ያጠቃልላሉ

Abdulfetah Mahmud
16.1K views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-31 07:40:20 ሃኪሞች በህክምናቸው ላይ ጉዳት ቢያደርሱ ተጠያቂ ናቸውን?
~
በኢስላም ህክምና የሚሰጥ አካል በሚከተሉት ሁኔታዎች ጉዳት ቢያደርስ ተጠያቂ እንደሚሆን ዓሊሞች ያስቀምጣሉ፦
1- ችሎታ ወይም እውቀት ሳይኖረው ህክም ሰጥቶ ጉዳት ካደረሰ ተጠያቂ ነው። ታካሚው ሁኔታውን እያወቀ ከተስማማ ግን ሃኪሙ ተጠያቂ አይሆንም።
2- ሆን ብሎ ጉዳት ካደረሰ ተጠያቂ ነው።
3- በስህተት ጤነኛ አካል ካጎደለ ወይም ነፍስ ካጠፋም ተጠያቂ ይሆናል። ልክ በስህተት ነፍስ ያጠፋ ሰው የተቀመጠውን የነፍስ ዋጋ እንደሚከፍለው ማለት ነው። ስለዚህ አንድ ሃኪም በስህተት ጤነኛ እግር ቢቆርጥ፣ ጤነኛ ጥርስ ቢነቅል፣ ጣት መቁረጥ ሲኖርበት በስህተት እጅ ወይም እግር ቢቆርጥ፣ .... ከፋይ ይሆናል። ልክ እንዲሁ ህክምናው ወይም ቀዶ ጥገናው ባለሙያዎች ዘንድ ከሚታወቀው መጠን አልፎ እርምጃ የወሰደ፣ ህክምናው መካሄድ በሌለበት ጊዜ ወይም ትክክለኛ ባልሆነ መሳሪያ ጉዳት ካደረሰ ተጠያቂ ይሆናል።
4- ያለ ታካሚው ወይም ያለ ቤተሰቡ ይሁንታ እርምጃ ወስዶ ጉዳት ካደረሰም ተጠያቂ ነው።
5- የተሳሳተ መድሃኒት በመስጠቱ ነፍስ ቢጠፋ ወይም አካል ቢጎድል ለጉዳቱ ተጠያቂ ነው።
በስህተት ወይም በግዴለሽነት ለሚያደርሰው ጉዳት ተጠያቂነቱ ለጎደለው አካል ወይም ለደረሰው ጉዳት በሸሪዐ የተቀመጠውን መጠን መክፈል ነው።

ነገር ግን ሃኪሙ:-
1- በሙያው ላይ ብቁ ከሆነ፣
2- ህክምናው የሚጠይቀውን ከፈፀመ፣
3- መተላለፍ ወይም ግዴለሽነት ከሌለው በሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ አይሆንም።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
12.8K views04:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-08-30 09:48:18
የቁርአን ሒፍዝ ምርቃት ፕሮግራም

መርከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዐሪ የቁርአን ሒፍዝ ማእከል ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን እሁድ ነሀሴ  28/2015 ከጠዋቱ 3 ሰአት ጀምሮ በደማቅ ፕሮግራም እንደሚያስመርቅ ስናበስረዎ በታላቅ ደስታ ነው ።

በፕሮግራሙም ላይ የተላያዩ ኡስታዞችና ዱዓቶች የሙሐደራ ግብዣ ይኖራቸዋል ።

በመሆኑም እርሶ የፕሮግራሙ ተካፋይ እንዲሆኑ በክብር ተጋብዘዋል ።

አድራሻ: ጦር ሀይሎች ከ አዲስ አበባ መጅሊስ አከባቢ  ኢሙ ታዎር ህንዓ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ

ማሳሰቢያ: የ አዳራሽ መግቢያ ምንም አይነት ክፍያ ስለሌለው ቦታ ሳይሞላባቹህ ቀድማቹህ እንድትገኙ እናሳስባለን ።

https://t.me/Kurantejwid
https://t.me/Kurantejwid
13.1K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ