Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.07K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 34

2023-09-13 17:18:50 ዘረኝነት ያውራል
~
እሺ እኔ ስለወለጋ አልፃፍኩም እንበል። እና ከኔ ጋር ምን አነታረከህ? አንተ አትፅፈውም'ንዴ?
* ጎንደር ላይ ሙስሊሞች ሲገ^ደሉ መስጂዶች ሲቃጠሉ "ምን ፃፋችሁ?" ብለናችኋል?
* እስቴ፣ ቢቸና ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲደርስ "ምን ፃፋችሁ?" ብለናችኋል?
* ጭልጋ ላይ ሙስሊሞች ሲፈናቀሉ "ምን ፃፋችሁ?" ብለናችኋል?
* አሁን ሰሞኑን በተደጋጋሚ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲደርስ "ምን ፃፋችሁ?" ብለናችኋል?

እኛ "ይህንን ፃፉ፣ ይህንን አትፃፉ" ሳንላችሁ እናንተ የምንፅፈውን ልትመርጡልን የምትሞክሩት ማን ሆናችሁ ነው? "ስለ ወለጋ ፅፈሃል ወይ?" ብለህ ለመጠየቅ ስትመጣ አታፍርምንዴ? "ስለ ፋኖ ጥቃት ለምን አልፃፍክም?" ያለህ የለምኮ። አንተ የምትጠይቀውን መጠየቅ አቅቶኝ ይመስልሃል ዝም የምልህ? በተለያየ ምክንያት ሁላችንም ስለ ሁሉም ልንፅፍ አንችልም። ማንም የማንም ተቆጣጣሪ አይደለም። ገመድ ጉተታህን ጥለህ ክፍተት ያየህበት ላይ ስራ። "የት ነበርክ? " ስትል ግን "አንተስ የት ነህ?" እንደምትባል እወቅ። ከየትኛውም ብሄር ብትሆን ሌላውም ያንተን የዘር አጀንዳ እንዲያነሳልህ አትጠብቅ።
ለመሆኑ እያላችሁት ያላችሁት ምን እንደሆነ ገብቷችኋል? "ሙስሊሞችን እያጠቁ ያሉ አካላትን ለምን ትናገራላችሁ?" ነውኮ እያላችሁ ያላችሁት። ወለጋ ላይ ሙስሊሞችን እያጠቁ ስለነበሩ አካላት ስንከላከል አይተሃል? ከገጠመህ ሂድና ከነሱ ጋር ተመላለስ።
ከዲናቸው ይልቅ ዘራቸውን ባስቀደሙ ዘረኞች በሁለት አቅጣጫ መወጋት ያዝንኮ። ወላሂ ስለ ኢሬቻ፣ ስለ ዘረኝነት፣ ስለ ወለጋ ሙስሊሞች ስፅፍ የኦሮሞን ትግል ለማደናቀፍ ነው ብሎ የዛተብኝ አለ። ስለ መስቀል፣ ስለ አማራ ክልል ሙስሊሞች ስፅፍ ደግሞ ለኦሮሞ ወግነህ ነው ብሎ የሰደበኝ አለ። ሁሉም ግን ሙስሊሞች ናቸው። ደግሞም ቅጥፈታቸው ስለ ጎንደር ሲፃፍ "እኛ እዚሁ ነው ያለነው። አንተ የምትለው የለም" ይላሉ። ቦታው ላይ ያሉት ሙስሊሞችኮ "እባካችሁ ድምፅ ሁኑን" እያሉ ነው። እነዚህ ከእሳቱ ቦታ ርቀው ይዋሻሉ። እኔ ለምሳሌ ያህል ምስራቅ ጎጃም ላይ ካሉ ወንድሞች እየደረሰ ያለውን ግፍና ያሉበትን ጭንቅ ተጨባጭ መረጃ ይዤ ነው የፃፍኩት። "ውሸት ነው" ካላችሁ ሳታጣሩ ለመከላከል ከመሞከር በፊት አጣሩ። ማጣራት ካልቻላችሁ ዝም በሉ። እየሞቱ ያሉት የራሳችሁ ቤተሰቦች ቢሆኑ ብላችሁ አስቡ። ከዚያ ውጭ ፖለቲካችሁ አይመለከተኝም። የአማራም፣ የኦሮሞም፣ የትግሬም ፖለቲካ ለኔ ምኔም አይደለም።
አዑዙ ቢላህ! ሙስሊሞቹ ባሱኮ!

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
14.0K viewsedited  14:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-13 14:28:30 ከሙስሊሞች ህይወት በላይ የፋኖ ክብር አሳስቧቸው የሙስሊሞችን ሞትና በደል የሚያስተባብሉ ሸይ * ጧኖች ጋር አትመላለሱ። በብሎክ ሸኟቸው። ከአኺራ በፊት አላህ በዱንያ የእጃቸውን ይስጣቸው።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
13.3K views11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-13 11:16:42
ምስራቅ ጎጃም ውስጥ ሙስሊሞች ላይ በፋኖ የሚደርሰው ግፍ እንደቀጠለ ነው።
ይሄ ከአካባቢው የተላከልኝ መልእክት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
17.4K viewsedited  08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-13 06:25:34 ‏{ما لَكُم لا تَرجونَ لِلَّهِ وَقارًا}..

قال الإمام ابن القيم رحمه الله :
"ومن وقاره: أن تستحي منه في الخلوة، أعظم مما تستحي من أكابر الناس".
.
: بدائع التفسير [٣/٢٠٤].
14.5K views03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-12 19:01:25 ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ
~
እውነቱን ለመናገር አንዳንድ ችግሮቻችንን እራሳችን ነን የምናውሰበስባቸው። እንዴት 80%፣ 90% ሙስሊም የሆነ ህዝብ "ተጨቆንኩ፣ ተበደልኩ" ብሎ ያለቅሳል?! ወላሂ! 100% ሙስሊም በሆነ ህዝብ ውስጥ በአንድ ተል ካሻ ግለሰብ እምነት ተኮር በደል ሲፈፀም አይቻለሁ። ሰው እንዴት በዚህ መጠን ራሱን ያስደፍራል? "የተናቀ መንደር በአህያ ይወረራል" ይባላል። በዚህ ደረጃ ራሳችንን ካስደፈርን ጩኸት አያምርብንም የሚሆነውን መቀበል ነው። "ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!"
ለማንኛውም እስከዛሬ ከደረሱ እልፍ ክስተቶች ትምህርት እንውሰድ። በሰፈር መፈታት የሚችልን ጉዳይ አገር አቀፍ አጀንዳ ካደረግነው መፍትሄ የማግኘት እድሉ በጣም ይመነምናል። ጎንደርም አፋርም ለሚደርስ ትንኮሳ ምላሻችን እኩል ለቅሶ ብቻ ነው መሆን ያለበት? ስለዚህ አካባቢያዊ ችግሮችን ገና ሳይጎመሩ በፊት አስተማሪ በሆነ መልኩ አካባቢያዊ መፍትሄ እናብጅላቸው። "ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ።"

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
15.5K views16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-12 11:35:32 ኢስላም ብቻ!
~
ሙስሊሞች ነን። አመታዊ በአሎቻችን ሁለት ናቸው። ዒደል ፊጥር እና ዒደል አድሓ። ከዚህ ውጭ
* የሳዑዲም ይሁኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ በዓላት
* የብሄርም ይሁኑ የባህል አውዳመታት አይመለከቱንም።
የአዲስ አመት መግቢያን፣ የዘመን መለወጫን ብናከብር ኖሮ ከክርስትናው እንቁጣጣሽ ይልቅ የኢስላማዊውን ሙሐረምን እናከብር ነበር። በኢስላም መስቀል፣ ጥምቀት፣ መውሊድን (ገና)፣ ኢሬቻ የሚባል በዓል የለም። በዘር ተጎትተን በልማድ ታስረን የምንጓዝበት ስርአት የለም።

ኢስላም ብቻ!

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
14.2K viewsedited  08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-12 06:38:49
እነ ነውር ጌጡ
~
ሙስሊሞች ድግምት ተፅእኖ እንዳለው በማመናቸው ሊሳለቁ እየሞከሩ ነው። እኮ እናንተም? ይሄው ደጋሚ አስተማሪዎቻችሁ ምን እንደሚሉ ስሙ።

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
13.5K viewsedited  03:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-10 17:51:13 አማራ ክልል ውስጥ ፋኖ ነን በሚሉ አካላት በኩል ሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጠናክረው ቀጥለዋል። በተለይም የሙስሊሙ ቁጥር አናሳ በሆነባቸው አካባቢዎች ግድያዎች፣ እገታዎችና ዘረፋዎች ከእለት ወደ እለት እየጨመሩ ነው። ከፋኖ ወይም ከደጋፊዎቹ በኩል እነዚህን እምነት ተኮር ጥቃቶች የሚኮንን ድምፅ እስካሁን አልሰማሁም። ከዚህ ይልቅ እየደረሰ ያለውን በደል ቀድሞ የመሸፋፈንና የማለባበስ ጥረቶች ናቸው የሚታዩት።
በዘር ብቅል የናወዛችሁ አካላት እዚህ መጥቻችሁ ለመከላከል ወይም ለማስተባበል እንዳትሞክሩ። ተጨባጭ መረጃ ይዤ ነው የምፅፈው። እንዲያውም ጫፉን እንጂ የማውቀውን ሁሉ አልፃፍኩም። እኔ የፖለቲካ አላማም ፍላጎትም የለኝምና እዚህ መጥታችሁ "ወለጋ ሲሆን ..."፣ ሸገር ሲሆን ..." እንዳትሉብኝ። እንዲህ አይነት ማሸማቀቂያችሁን ፈርተው ብዙ የተለጎሙ ሙስሊሞችን እያየሁ ነው። ሁላችንም ዝም እንል ዘንድ በእምነት እየተለየ የሚፈፀመውን ጥቃት አስቁሙ። እውነት አላማችሁ ፖለቲካ ከሆነ ፖለቲካ እንዲህ አይሰራም። ቆይ ሙስሊሙ ምን ያርጋችሁ? ምን ይሁንላችሁ? በዘር ተኮር ጥቃቶች ከሆነ የትም ቢሆን ከናንተ በላይ የተጎዳው ሙስሊሙ ነው። የሙስሊሙን በዘር መጠቃት ለብሶት መቀስቀሻ እየተጠቀማችሁበት እንደገና ዞራችሁ እንዴት ታጠቁታላችሁ? ወወላሂ በዚህ ዘመን እንደ አማራ ሙስሊም መከራ የበዛበት የለም። ሌላ ቦታ አማራ ተብሎ ይጨፈጨፋል። ክልሉ ውስጥ በሙስሊምነቱ ይጠቃል። እሺ የት ይሂድ?! ምን ዓይነት ፈተና ነው?!
በመጨረሻም ክልሉ ውስጥ እየደረሱ ስላሉ እምነትን ያነጣጠሩ ጥቃቶች መረጃው ላላችሁ ሙስሊሞች አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። ዝምታችሁ እልባት ላያመጣ ነገር ዝም አትበሉ። ይልቅ ሰለባ እየሆነ ላለው ሙስሊም በጊዜ በምትችሉት ድምፅ ሁኑ። ገዳዩ አካል ይሉኝታ ሳይዘው አጉል ይሉኝታ አይያዛችሁ። ህመማችሁ ህመሙ ላልሆነ ትግል አትጨነቁ። ብዙ ወገን ሙስሊሞች ላይ ተለይቶ እየተፈፀመ ስላለው ጥቃት መረጃ የለውምና ቢያንስ በዚህ ላይ መስራት ከምንም ይሻላል።

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
17.3K viewsedited  14:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-09 11:48:11 በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ?
~
በመውሊድ በዓላት የተነሳ የተከበሩ የአላህ ቤቶች በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ ክብራቸው ይረከሳል፡፡ ይሄ ደግሞ አላህ እንዲህ ሲል ከሃዲዎችን ከወቀሰባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው፡-
(وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَیۡتِ إِلَّا مُكَاۤءࣰ وَتَصۡدِیَةࣰۚ)
"በቤቱ (በከዕባ) ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡" [አልአንፋል፡ 35]

የአራቱም መዝሀብ ተከታዮች ይህንን ድርጊት ያወግዛሉ፡፡ በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ “ወደ አላህ እቃረባለሁ፣ ዒባዳ ነው” የሚል እምነት አደገኛ ብልግና ነው፡፡ እንዲያውም ይሄ ከክርስቲያኖች የተኮረጀ ጥመት ነው፡፡ ዛሬም ዝላይና ጭፈራን አምልኮት ያደረጉት እነሱ ናቸው፡፡ ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና ስሙ እንዲወሳባቸው ባዘዘባቸው መስጂዶች ውስጥ ድቤ መደብደብ፣ ማጨብጨብና መጨፈር እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው፡፡ ይህን ቆሻሻ ተግባር መቃረቢያ አድርጎ ማሰብ ደግሞ የለየለት ጥመት ነው፡፡ እንዲያውም ኢብኑል ጀውዚይ እንዲህ ብለዋል፡-
وقد نفر جماعة من المتصوفة خلقًا من الخلق عن الكسب، وأوحشوا بينهم وبينه، وهو دأب الأنبياء والصالحين، وإنما طلبوا طريق الراحة، وجلسوا على الفتوح، فإذا شبعوا، رقصوا، فإذا انهضم الطعام، أكلوا، فإذا لاحت لهم حيلة على غنيٍّ، أوجبوا عليه دعوةً، إما بسبب شكر، أو بسبب استغفار. وأَطَمُّ الطامات ادعاؤهم أن هذا قربةٌ! وقد انعقد إجماع العلماء أن من ادعى الرقص قربة إلى الله تعالى، كفر،
“በርግጥም ብዙ ሱፍዮች በርካታ ህዝቦችን ስራ ከመስራት አርቀዋል፡፡ በሱ (በስራ) እና በነሱ መካከል ባይተዋርነትን አንግሰዋል፡፡ ግና ስራ የነብያትና የደጋጎች ፈለግ ነው፡፡ እነዚህ የፈለጉት ግን የእረፍትን መንገድ ነው፡፡ በየምግቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ሲጠግቡ ጊዜ ይደንሳሉ፡፡ ምግቡ ሲፈጭ ይበላሉ፡፡ በሃብታም ላይ የሆነ ብልጠት ሲገለጥላቸው በምስጋና ወይም በንስሃ ስም ግብዣ እንዲያዘጋጅ ግድ ያደርጉበታል፡፡ ከመዐቶቻቸው ሁሉ የከፋው መዐት ግን ይህንን (ጭፈራ) መቃረቢያ (ዒባዳ) አድርገው መሞገታቸው ነው፡፡ ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው እንደሚከፍር በርግጥም የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጥሯል፡፡” [ሶይዱል ኻጢር፡ 168]

ኢማሙ ማሊክ፡- “እኛ ዘንድ ሱፍያ የሚባሉ ሰዎች አሉ፡፡ በብዛት ይበሉና ከዚያ ያንጎራጉራሉ፡፡ ከዚያም ተነስተው ይጨፍራሉ” ሲሏቸው
“ህፃናት ናቸው?” ብለው ጠየቁ፡፡
“አይደሉም” አሏቸው፡፡
“እብዶች ናቸው?” ሲሉ
“አይደሉም፡፡ ሸይኾች ናቸው” አሏቸው፡፡
“እኔ ከኢስላም ሰዎች ይህን የሚሰራ አንድም አልሰማሁም” አሉ፡፡ [ተርቲቡል መዳሪክ: 2/53]

አቡበክር አጦርጡሺም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “የሱፍያ አካሄድ ቦዘኔነት፣ መሀይምነትና ጥመት ነው፡፡ ኢስላም ማለት የአላህ ቁርኣንና የመልእክተኛው ሱና እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ዳንስና ውዝዋዜ የመጀመሪያ የፈጠሩት የሳሚሪ ባልደረቦች ናቸው (በነብዩ ሙሳ ዘመን)፡፡ ያኔ ድምፅ ያለው የወይፈን አካልን አምላክ ሲያደርግላቸው ጊዜ መጥተው ዙሪያውን ይጨፍሩና ይወዛወዙ ነበር፡፡ ማለትም ጭፈራ የከሃዲዎችና የወይፈን አምላኪዎች ሃይማኖት ነው፡፡ የነብዩ ﷺ እና የሶሐቦቻቸው ጉባኤ ልክ ከራሳቸው ላይ ወፍ ያረፈ እስከሚመስል መረጋጋት ነበራቸው፡፡ እነዚህን (ጨፋሪ) ሰዎች አሚሩ መስጂድ ውስጥም ይሁን ሌላ ቦታ (ጭፈራቸውን) ከመፈፀም ሊከለክላቸው ይገባል፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ከነሱ ጋር ሊካፈል፣ በጥፋትም ላይ ሊያግዛቸው አይፈቀድለትም፡፡ የማሊክም፣ የአቡ ሐኒፋም፣ የሻፊዒይም፣ የአሕመድም፣ የሌሎችም ሙስሊም ምሁራን መዝሀብ ይህን ነው የሚያዘው፡፡” [ተፍሲሩል ቁርጡቢይ፡ 11/238]

አልዒዝ ኢብኑ ዐብዲሰላምም፡- “ጭፈራ ቢድዐ ነው፡፡ አእምሮው ጎደሎ የሆነ እንጂ አይፈፅመውም” ይላሉ፡፡ [ፈታዋ አልዒዝ ብኒ ዐብዲ ሰላም፡ 318-319]

ይህንን ይዘን በየመውሊዱ መስጂድ ውስጥ አግድም ተሰልፈው፣ ድቤ እየደለቁ፣ ለፉጨት የቀረበ ድምፅ እያወጡ፣ ቀረርቶ በመሰለ ድምፅ እያላዘኑ የሚወዛወዙ የጠመጠሙ መሃይማንን አስቡ፡፡ ከአላህ ቤት ጭፈራ ዲን ሆኖ ሲቀርብ ተመልከቱ፡፡ አላሁል ሙስተዓን!
~
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
16.0K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-08 22:12:11 ማስታወቂያ
~
የፊታችን እሁድ በሑዘይፋ መስጂድ የሴቶች ፕሮግራም እንዳለ ስለተነገረን ሳምንታዊ ደርስ አይኖርም።
15.3K views19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ