Get Mystery Box with random crypto!

ዘረኝነት ያውራል ~ እሺ እኔ ስለወለጋ አልፃፍኩም እንበል። እና ከኔ ጋር ምን አነታረከህ? አንተ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ዘረኝነት ያውራል
~
እሺ እኔ ስለወለጋ አልፃፍኩም እንበል። እና ከኔ ጋር ምን አነታረከህ? አንተ አትፅፈውም'ንዴ?
* ጎንደር ላይ ሙስሊሞች ሲገ^ደሉ መስጂዶች ሲቃጠሉ "ምን ፃፋችሁ?" ብለናችኋል?
* እስቴ፣ ቢቸና ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲደርስ "ምን ፃፋችሁ?" ብለናችኋል?
* ጭልጋ ላይ ሙስሊሞች ሲፈናቀሉ "ምን ፃፋችሁ?" ብለናችኋል?
* አሁን ሰሞኑን በተደጋጋሚ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ሲደርስ "ምን ፃፋችሁ?" ብለናችኋል?

እኛ "ይህንን ፃፉ፣ ይህንን አትፃፉ" ሳንላችሁ እናንተ የምንፅፈውን ልትመርጡልን የምትሞክሩት ማን ሆናችሁ ነው? "ስለ ወለጋ ፅፈሃል ወይ?" ብለህ ለመጠየቅ ስትመጣ አታፍርምንዴ? "ስለ ፋኖ ጥቃት ለምን አልፃፍክም?" ያለህ የለምኮ። አንተ የምትጠይቀውን መጠየቅ አቅቶኝ ይመስልሃል ዝም የምልህ? በተለያየ ምክንያት ሁላችንም ስለ ሁሉም ልንፅፍ አንችልም። ማንም የማንም ተቆጣጣሪ አይደለም። ገመድ ጉተታህን ጥለህ ክፍተት ያየህበት ላይ ስራ። "የት ነበርክ? " ስትል ግን "አንተስ የት ነህ?" እንደምትባል እወቅ። ከየትኛውም ብሄር ብትሆን ሌላውም ያንተን የዘር አጀንዳ እንዲያነሳልህ አትጠብቅ።
ለመሆኑ እያላችሁት ያላችሁት ምን እንደሆነ ገብቷችኋል? "ሙስሊሞችን እያጠቁ ያሉ አካላትን ለምን ትናገራላችሁ?" ነውኮ እያላችሁ ያላችሁት። ወለጋ ላይ ሙስሊሞችን እያጠቁ ስለነበሩ አካላት ስንከላከል አይተሃል? ከገጠመህ ሂድና ከነሱ ጋር ተመላለስ።
ከዲናቸው ይልቅ ዘራቸውን ባስቀደሙ ዘረኞች በሁለት አቅጣጫ መወጋት ያዝንኮ። ወላሂ ስለ ኢሬቻ፣ ስለ ዘረኝነት፣ ስለ ወለጋ ሙስሊሞች ስፅፍ የኦሮሞን ትግል ለማደናቀፍ ነው ብሎ የዛተብኝ አለ። ስለ መስቀል፣ ስለ አማራ ክልል ሙስሊሞች ስፅፍ ደግሞ ለኦሮሞ ወግነህ ነው ብሎ የሰደበኝ አለ። ሁሉም ግን ሙስሊሞች ናቸው። ደግሞም ቅጥፈታቸው ስለ ጎንደር ሲፃፍ "እኛ እዚሁ ነው ያለነው። አንተ የምትለው የለም" ይላሉ። ቦታው ላይ ያሉት ሙስሊሞችኮ "እባካችሁ ድምፅ ሁኑን" እያሉ ነው። እነዚህ ከእሳቱ ቦታ ርቀው ይዋሻሉ። እኔ ለምሳሌ ያህል ምስራቅ ጎጃም ላይ ካሉ ወንድሞች እየደረሰ ያለውን ግፍና ያሉበትን ጭንቅ ተጨባጭ መረጃ ይዤ ነው የፃፍኩት። "ውሸት ነው" ካላችሁ ሳታጣሩ ለመከላከል ከመሞከር በፊት አጣሩ። ማጣራት ካልቻላችሁ ዝም በሉ። እየሞቱ ያሉት የራሳችሁ ቤተሰቦች ቢሆኑ ብላችሁ አስቡ። ከዚያ ውጭ ፖለቲካችሁ አይመለከተኝም። የአማራም፣ የኦሮሞም፣ የትግሬም ፖለቲካ ለኔ ምኔም አይደለም።
አዑዙ ቢላህ! ሙስሊሞቹ ባሱኮ!

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor