Get Mystery Box with random crypto!

አማራ ክልል ውስጥ ፋኖ ነን በሚሉ አካላት በኩል ሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

አማራ ክልል ውስጥ ፋኖ ነን በሚሉ አካላት በኩል ሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጠናክረው ቀጥለዋል። በተለይም የሙስሊሙ ቁጥር አናሳ በሆነባቸው አካባቢዎች ግድያዎች፣ እገታዎችና ዘረፋዎች ከእለት ወደ እለት እየጨመሩ ነው። ከፋኖ ወይም ከደጋፊዎቹ በኩል እነዚህን እምነት ተኮር ጥቃቶች የሚኮንን ድምፅ እስካሁን አልሰማሁም። ከዚህ ይልቅ እየደረሰ ያለውን በደል ቀድሞ የመሸፋፈንና የማለባበስ ጥረቶች ናቸው የሚታዩት።
በዘር ብቅል የናወዛችሁ አካላት እዚህ መጥቻችሁ ለመከላከል ወይም ለማስተባበል እንዳትሞክሩ። ተጨባጭ መረጃ ይዤ ነው የምፅፈው። እንዲያውም ጫፉን እንጂ የማውቀውን ሁሉ አልፃፍኩም። እኔ የፖለቲካ አላማም ፍላጎትም የለኝምና እዚህ መጥታችሁ "ወለጋ ሲሆን ..."፣ ሸገር ሲሆን ..." እንዳትሉብኝ። እንዲህ አይነት ማሸማቀቂያችሁን ፈርተው ብዙ የተለጎሙ ሙስሊሞችን እያየሁ ነው። ሁላችንም ዝም እንል ዘንድ በእምነት እየተለየ የሚፈፀመውን ጥቃት አስቁሙ። እውነት አላማችሁ ፖለቲካ ከሆነ ፖለቲካ እንዲህ አይሰራም። ቆይ ሙስሊሙ ምን ያርጋችሁ? ምን ይሁንላችሁ? በዘር ተኮር ጥቃቶች ከሆነ የትም ቢሆን ከናንተ በላይ የተጎዳው ሙስሊሙ ነው። የሙስሊሙን በዘር መጠቃት ለብሶት መቀስቀሻ እየተጠቀማችሁበት እንደገና ዞራችሁ እንዴት ታጠቁታላችሁ? ወወላሂ በዚህ ዘመን እንደ አማራ ሙስሊም መከራ የበዛበት የለም። ሌላ ቦታ አማራ ተብሎ ይጨፈጨፋል። ክልሉ ውስጥ በሙስሊምነቱ ይጠቃል። እሺ የት ይሂድ?! ምን ዓይነት ፈተና ነው?!
በመጨረሻም ክልሉ ውስጥ እየደረሱ ስላሉ እምነትን ያነጣጠሩ ጥቃቶች መረጃው ላላችሁ ሙስሊሞች አንድ ነገር ማለት እፈልጋለሁ። ዝምታችሁ እልባት ላያመጣ ነገር ዝም አትበሉ። ይልቅ ሰለባ እየሆነ ላለው ሙስሊም በጊዜ በምትችሉት ድምፅ ሁኑ። ገዳዩ አካል ይሉኝታ ሳይዘው አጉል ይሉኝታ አይያዛችሁ። ህመማችሁ ህመሙ ላልሆነ ትግል አትጨነቁ። ብዙ ወገን ሙስሊሞች ላይ ተለይቶ እየተፈፀመ ስላለው ጥቃት መረጃ የለውምና ቢያንስ በዚህ ላይ መስራት ከምንም ይሻላል።

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor