Get Mystery Box with random crypto!

ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ ~ እውነቱን ለመናገር አንዳንድ ችግሮቻችንን እራሳችን ነን የምናውሰበስባቸ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ
~
እውነቱን ለመናገር አንዳንድ ችግሮቻችንን እራሳችን ነን የምናውሰበስባቸው። እንዴት 80%፣ 90% ሙስሊም የሆነ ህዝብ "ተጨቆንኩ፣ ተበደልኩ" ብሎ ያለቅሳል?! ወላሂ! 100% ሙስሊም በሆነ ህዝብ ውስጥ በአንድ ተል ካሻ ግለሰብ እምነት ተኮር በደል ሲፈፀም አይቻለሁ። ሰው እንዴት በዚህ መጠን ራሱን ያስደፍራል? "የተናቀ መንደር በአህያ ይወረራል" ይባላል። በዚህ ደረጃ ራሳችንን ካስደፈርን ጩኸት አያምርብንም የሚሆነውን መቀበል ነው። "ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ!"
ለማንኛውም እስከዛሬ ከደረሱ እልፍ ክስተቶች ትምህርት እንውሰድ። በሰፈር መፈታት የሚችልን ጉዳይ አገር አቀፍ አጀንዳ ካደረግነው መፍትሄ የማግኘት እድሉ በጣም ይመነምናል። ጎንደርም አፋርም ለሚደርስ ትንኮሳ ምላሻችን እኩል ለቅሶ ብቻ ነው መሆን ያለበት? ስለዚህ አካባቢያዊ ችግሮችን ገና ሳይጎመሩ በፊት አስተማሪ በሆነ መልኩ አካባቢያዊ መፍትሄ እናብጅላቸው። "ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ።"

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor