Get Mystery Box with random crypto!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

የሰርጥ አድራሻ: @ibnumunewor
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 77.07K
የሰርጥ መግለጫ

كناشة ابن منور

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-04-15 15:10:21 ልቤ ሆይ!!
~
ልቤ ሆይ ልብ አድርግ - ለመልካሙ ትጋ - ከክፋት ተገታ
ምላሴ ሆይ እረፍ - ጦስህ ያስፈራኛል - በጧትም በማታ
እጄ ሆይ ተመከር - "እጄን በ’ጄ" እንዳልል - በሚያስጨንቅ ቦታ
እግሬ እግር አታብዛ - ታዋርደኛለህ - በጭንቁ ቀን ለታ
አዋጅ ሰምቻለሁ - እጅግ የሚያስፈራ - ከሰማዩ ጌታ።

(يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ) [النور 24]
"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሰሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡" [አንኑር: 24]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
17.6K views12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 19:33:33 ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል
~
ትላንት አንድ "ኡስታዝ" አንዲትን እህት በብሄሯ ምክንያት ከምትማርበት ግሩፕ አባረራት ተብሎ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ይሄው በርካታ ፀረ ኢስላም የሆኑ አካላት ለድሪቶ ፖለቲካቸው ጉዳዩን እየተጠቀሙበት እያየን ነው። ትላንት ጀምረው ጉዳዩን የተለያዩ ክፉ ትርጉሞችን እየሰጡ ማራገብን ተያይዘውታል። እነዚህ ደም መጣጭ የኢስላም ጠላቶች በሙስሊሞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በመሸፋፈን የታወቁ ናቸው። አንድ ማን እንደፃፈው እንኳ የማይታወቅን ፅሁፍ ግን ተቆርቋሪ መስለው እያራገቡ ነው። ለነዚህ አካላት ይህንን ረብ የለሽ ነገር ያቀበሏቸው ደግሞ የኛው በዘር ልክፍት የተለከፉ አካላት ናቸው።
ምን ማድረግ ነበረብን? ጉዳዩ እውነት እንኳ ቢሆን የጠላት መጠቀሚያ እንዳይሆን ከማራገብ ይልቅ በልኩ መያዝ ነበረብን። ይህንን የምለው ከዚህ የተሳከረ የዘር ፖለቲካ ይልቅ ኢስላማቸውን ለሚያስቀድሙ ነው። ፖለቲካው አስክሯቸው ከካ'ፊ'ር ጋር ለተለጠፉ አካላት እንዲህ አይነት ፊትና ቀስቃሽ ቅንብሮች መራገባቸው ለነሱ ስኬት ነው። ነገ ከአላህ ፊት መቅረብን የሚያስብ አማኝ ግን የዘር ጥላቻ ዐቅሉን እስከሚያስተው ድረስ አይዘቅጥም።

ጉዳዩን አጣራን ብለው ያወጡ ሰዎች አይቻለሁ። ያደረጉት ነገር ቢኖር ባለ ጉዳይ የተባለችዋን እህት ደውሎ መጠየቅ ነው። አጠፋ የተባለውንስ ኡስታዝ አናግረዋል? የለም! ነገር እንደዚህ ነውንዴ የሚጣራው? ሰው ለራሱ የማይወደውን አካሄድ እንዴት በሌላው ላይ ያደርጋል? እስኪ በራሳችሁ ላይ አስቡት። አንዲት ሴት በከባድ ዘረኝነት ወነጀለቻችሁ እንበል። ሰዎች ጉዳዩን ማጣራት ፈለጉና እሷ ጋር ደውለው "እውነት ነው ወይ?" ሲሏት "አዎ" አለቻቸው። ከናንተ ማረጋገጫ ሳይወሰድ ያለቀ እውነት ተደርጎ ቢራገብ ደስ ይላችኋል? ማጣራት ማለት እንደዚህ ነው? በጭራሽ! ከሳሽና ተከሳሽ ሲኖር ነገር የሚጣራው ከሁለቱም በኩል ነው። ከከሳሽ በኩል ተጨባጭ ነገር ቢኖር ራሱ በተከሳሽ በኩል ያለውን ማወቅ ይገባል። ምክንያቱም ያገኘነውን እውነታ ሙሉ ይዘቱን የሚቀይር fact ተከሳሽ ዘንድ ሊኖር ይችላልና። "አንድ ከሳሽ 'ይሄው አንድ አይኔ ጠፍቷል፤ ፍረድልኝ' ቢልህ እንዳትፈርድለት። ምናልባትም ተከሳሹ ሁለት አይኑ ጠፍቶ ሊሆን ይችላል" የሚል በዐሊይ ስም የሚወራ የጥበብ ንግግር አለ። የተከሳሹ ብሄር ሌላ ስለሆነ ብቻ ለመፍረድ ልንቸኩል አይገባም።

መረጃ እንዴት ነው የሚጣራው?
በኢስላም ከሳሽና ተከሳሽ ሲኖር ማንም በደመ ነፍስ አይጓዝም። የራሱ ስርአት አለው። ይህንን ስርአት ማክበር ከእያንዳንዱ ሙስሊም የሚጠበቅ ነው። ብዙዎቻችን ጋር ያለው ግን ተከሳሹ የምንጠላው ከሆነ ወይም ጉዳዩ ለምናራግበው የፖለቲካ ፍጆታ የሚያግዝ ከሆነ ከስር ከማጥራት ይልቅ በቀላሉ አምነን ሌሎችንም ልናሳምን መነሳት ነው። መሆን ያለበትስ እንዴት ነው? ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ:–
لو يعطى الناسُ بدعواهم، لادَّعَى رجال أموالَ قومٍ ودماءَهم، ولكن البينة على المدعِي، واليمين على مَن أنكر
"ሰዎች በሙግታቸው ቢሰጣቸው ኖሮ ወንዶች የሌሎች ሰዎችን ገንዘቦች እና ደሞች ይሞግቱ ነበር። ነገር ግን በከሳሽ ላይ ማስረጃ አለበት። ባስተባበለ ላይ ደግሞ መሀላ አለበት።" [በይሀቂይ ዘግበውታል።]

የተከሰተውን ጉዳይ በዚህ ሐዲሣዊ መመሪያ ስንመዝነው:-
1- ከሳሿ እህት:- ተጨባጭ ማስረጃ ወይም ምስክር ማቅረብ ነበረባት። ማንም ሊያቀናብረው የሚችል ፅሁፍ ሳይሆን ጥርጣሬን የሚገፍ መረጃ መኖር ነበረበት። ለምሳሌ ካለ የድምፅ መረጃ። ይህንን ማድረግ ካልቻለችስ? "ዋሽታለች" ብለን እንደመድማለን? አይደለም። ይልቁንም ወደ ሁለተኛው ነጥብ እናልፋለን።
2- ተከሳሹ "ኡስታዝ" (የእውነት ካለ)፦ እንዲያምን ካልሆነ ማስተባበያውን በመሀላ እንዲያፀና ይጠየቃል።

ቀረበ በተባለው ማረጋገጫ ግን ሁለቱም አልተደረገም። እሷም tangible መረጃ አላቀረበችም። ኡስታዙም ከነ ጭራሹ አልተጠየቀም። የተባለው ኡስታዝ ከነመኖሩም ማወቅ አይቻልም። ምክንያቱም ከነጭራሹ ማረጋገጫ አልቀረበምና። ይባስ ብሎ የጉዳዩ መነሻ እህት ታማኝ ትሁን አትሁን የሚታወቅ ነገርም የለም። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوۤا۟ إِن جَاۤءَكُمۡ فَاسِقُۢ بِنَبَإࣲ فَتَبَیَّنُوۤا۟ أَن تُصِیبُوا۟ قَوۡمَۢا بِجَهَـٰلَةࣲ فَتُصۡبِحُوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلۡتُمۡ نَـٰدِمِینَ }
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ሆናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተፀፃቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ።" [አልሁጁራት: 6]
በታማኝነቱ የማይታወቅ እና በአመፀኝነት የሚታወቅ ሰው የሚያመጣውን ወሬ ሳያርጋግጡ ሌሎች ላይ መፍረድ አይቻልም። በተለይ ደግሞ በዚህ የዘር አጀንዳ በከረረበት ጊዜ የበለጠ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
"በድጋሜ ማንሳት ለምን አስፈለገ?" የሚል ሊኖር ይችላል። ምክንያቴ የኢስላም ጠላቶች አሁን ድረስ እያራገቡት ስለሆነ መሰል ጥፋቶች ከአላፊ ክስተትነት ባሻገር የሌሎች መጠቀሚያ ስለሚሆኑ ለሌላ ጊዜ በምን መልኩ መያዝ እንዳለብን ማሳሰብ ነው። "ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባልና።"

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 6/2016)
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
17.7K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 19:33:29
15.7K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 22:25:15 ወደ ፌስቡክ ስገባ አንድ የሚዘዋወር ፀያፍ ፖስት አየሁኝ። ዘወርወር ብዬ ሃሳቦችን ለመቃኘትም ሞክሬያለሁ። የኔ ምልከታ፦

1ኛ፦ እስካሁን ባየሁት ፖስቱ እውነተኛ ለመሆኑ ማረጋገጫ አልቀረበም። መቶ በመቶ ውሸት ነው ብዬ ባልደመድም ለራሴ እውነተኛ መስሎ አልታየኝም። እንዲያውም "ምልልሱ" የአንድ ሰው ድርሰት ነው የሚመስለው። "ሙሉ መረጃውን ከሰዓታት በኋላ አሳያለሁ" ያለውም ወንድም ቢሆን መነሻውም መድረሻውም የማይመስል ነገር ነው የፃፈው። ሙሉ ቀርቶ 1% መረጃም አላመጣም።
ለማረጋገጥ በዚህ ቁጥር አናግሩ ማለትም አስቂኝ ነው። ባለ ቁጥሩ አቀናባሪው ራሱ ይሁን ሌላ ሰው ይሁን፣ ታማኝ ይሁን አይሁን ምን ፍንጭ ይሰጣል? ማረጋገጫ ማለት እንደዚህ ነውንዴ?
ብቻ እውነት ይህንን የሰራ ኡስታዝ ካለ ነገ አላህ ፊት ይቀርባል። ቅንብር ከሆነም ነገ ምላስ ተለጉማ አካሎች በሚመሰክሩበት ቀን ውርደት ይከናነባል። ማንም ቢሆን የዘራውን ማጨዱ አይቀርም። መቼስ ከሞት በኋላ ህይወት፣ ከአላህ ፊት ቀርቦ ሂሳብ እንዳለ እናምናለን።

2ኛ፦ ባይሆን ያለንበት ተጨባጭ ከዚህ የባሰ እንጂ ያነሰ አይደለም። የቀረበው "ድርሰትም" እውነትም ሆነ ውሸት ላለንበት ችግር አንድ ማሳያ ሊሆን ይችላል። የመስጂድ ኢማሞች፣ ኡስታዞች ኧረ እንዲያውም በእድሜ የገፉ ሸይኾች ሳይቀሩ ከዚህ የባሰ ዘረኝነት ላይ የወደቁ ብዙ አሉ። ባህር አቆራርጠው ዒልም ፍለጋ የከተሙ ወጣቶች ላይ አስቀያሚ ዘር ወለድ ችግሮችን በራሴ ታዝቤያለሁ። ከታማኝ ወንድሞችም ብዙ ሰምቻለሁ። ሱብሒ ሶላት ሳይቀር ከሰው በፊት ቀድሞ መስጂድ የሚጣድ ሰው እዚህ ላይ ልገልፀው የሚሰቀጥጥ ተግባር በዘረኝነት ተነሳስቶ ሲፈፅም ባይኔ ተመልክቻለሁ። ላኢላሀ ኢለላህ ከሚያስተሳስራቸው ወንድሞቻቸው ሞት ይልቅ ዘር የሚያገናኛቸውን የሌላ እምነት ተከታዮች የሚያስቀድሙ ብዙ አይተናል። በመስጂዶች ላይ ሳይቀር የዘር መቧደንና ጥላቻ የታየባቸው ብዙ አጋጣሚዎች አሉ።

ቢሆንም፡

1- እንዲህ አይነት ችግሮችን ስናይ አላህን በመፍራት ላይ በጥብቅ መተዋወስ እንጂ ያለብን ይበልጥ ለመቆራረጥና ለመራራቅ አይደለም ማራገብ ያለብን። አነሰም በዛ ከዘር ይልቅ እምነታቸውን የሚያስቀድሙ ወገኖች በየ ብሄሩ አሉና ቢያንስ ስለነሱ ስንል እንኳ ከጅምላ ፍረጃ ርቀን ችግሩን በጥንቃቄ ማከም ላይ ብናተኩር መልካም ነው።
2- ዘረኝነት አንድን ብሄር ለይቶ የሚያጠቃ ልክፍት አይደለም። መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁሉም ጋር አለ። ጉዳዩን የኛ ሳይሆን የሌሎች አድርጎ መሳሉ ራሱ ራሱን የቻለ ዘረኝነት ነው። ወደራሳችን እንመልከት።

ይልቅ መፈራራታችንንም መፈራረጃችንንም ትተን ችግሩን እንጋፈጠው። እንዲህ እንመን። በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ያለ ሙስሊም አጠቃላይ ሁሉም ወገኔ ነው። ትግሬ ሆነ በርታ፣ ኦሮሞ ሆነ አማራ፣ አፋር ሆነ ሱማሌ፣ ስልጤ ሆነ ጉራጌ፣ አደሬ ሆነ ሃላባ፣ ... ለኔ ልዩነት የለውም። በብሄር ስለሚቀርበኝ የተለየ ቦታ የምሰጠው አካል የለኝም። ሰው ለወጣበት ብሄረሰብ መቆርቆሩን አልኮንንም። ራሱን በወጣበት ዘር መግለፁንም አልነቅፍም፣ ለራሴ ባልመርጠውም። በብሄር አይን ባይሆንም እኔም የወሎ ህዝብ ከልብ ያሳዝነኛል። በተለየ እየተገፋ ያለ ከመሆኑ ጋር ተቆርቋሪ ያጣ፣ የመሰሪ ፖለቲከኞች መጠቀሚያ የሆነ ብኩን ህዝብ እንደሆነ ይሰማኛል። ምናልባት ለወጣሁበት ማህበረሰብ ልበ ስስ ሆኜ ተሳስቼ ከሆነም አላውቅም። ምናልባት!
የሆነ ሆኖ ለአማራ ህዝብ ለመታገል ኦሮሞን፣ ለኦሮሞ ህዝብ ለመታገልም እንዲሁ አማራን መግፋትም መጥላትም አያስፈልግም። ማንም በዘርም በሃይማኖትም ልዩነት መብበደል የለበትም። አባት ያጣው ሙስሊሙ ወገኔ ደግሞ የበለጠ ህመሙ ያመኛል። የኦሮሞው ሙስሊም ወንድሜ ነው። በዘር ልዩነት መገፋቱን አልሻም። የአማራው ሙስሊምም ወገኔ ነው። በማንም መበደሉን አልሻም። እንዲሁ መሻት! እነዚህን ብሄሮች የምጠቅሰው ለኔ ከሌሎች ብሄሮች የተለየ ቦታ ኖሯቸው ሳይሆን መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ የሚናገረው ነገር ስላለ ነው።
ሳጠቃልል ማረጋገጫ የሌለውን ፅሁፍ ሐቂቃውን ለአላህ አሳልፈን ማራገቡን እንተወው እላለሁ። ችግሩ ግን አመንም አላመንም መሬት ላይ አለና ለመዘላለፍና ነጥብ ለማስቆጠር ሳይሆን አላህን ፈርተን ለመመካከር ስንል ትኩረት ሰጥተን እንስራበት።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 5/2016)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
15.6K viewsedited  19:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 20:10:47
ንቃ!
~
የጠላት አጀንዳ አስፈፃሚ የውስጥ ባንዳ ክፋት ያምሃል? እንግዲያው ይህንን ቀብር አምላኪ አንጃ ስሩን በመንቀል ላይ አጥብቀህ ስራ!
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
18.1K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 11:37:21 እንደ ጌታቸው ሽፈራው ያሉ የፋኖ ፕሮፖጋንዲስቶች ዛሬም "ውሃብያ" እያሉ እምነታችን ላይ ማቀርሸታቸውን ቀጥለዋል።
{ قَدۡ بَدَتِ ٱلۡبَغۡضَاۤءُ مِنۡ أَفۡوَ ٰ⁠هِهِمۡ وَمَا تُخۡفِی صُدُورُهُمۡ أَكۡبَرُۚ }
ከዚህ ቡድን ጋር በተያያዘ ጌታዬን ከማመሰግንባቸው ነገሮች አንዱ ቡድኑ ጥላቻውን መደበቅ የማይችል መሆኑ ነው። በዚህ የሚይዘው የሚጨብጠው ባጣበት ጊዜ በዚህ መልኩ ክፋቱን የሚያንፀባርቅና ሙስሊሙን እየለየ የሚገድል ቡድን አገር ቢቆጣጠር የሚያደርገንን ማሰብ ነው። "እባብ ልቡን አይቶ እግር ነሳው" ለመሰሎቻችሁ የተተረተ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
19.7K views08:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 09:59:16 "የሆኑ ሰዎች በረመዷን ዒባዳ ይፈፅማሉ፣ በመልካም ስራዎች ላይ ይተጋሉ። ወሩ ሲጠናቀቅ ግን ይተውታል" የሚል ለቢሽሩል ሓፊ ሲነሳላቸው እንዲህ ሲሉ መለሱ፦
بئس القوم قوم لا يعرفون الله إلا في رمضان
"አላህን በረመዷን እንጂ የማያውቁ ሰዎች ምንኛ ክፉ ሰዎች ናቸው!"
[ሚፍታሑል አፍካር ሊተአሁቢ ሊዳሪል ቀራር፡ 2/283]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
18.7K viewsedited  06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 15:48:22 በአማራ ክልል ሙስሊሞች ላይ ያነጣጠረው ግድያና እገታ እንደቀጠለ ነው። እኔ ባለኝ መረጃ ትላንትና ዛሬ ሞጣ አንድ ሰው፣ ባህርዳር አንድ ሰው የተገደለ ሲሆን ባህርዳር ውስጥ የታጠቁ ሰዎች አንዲትን ሙስሊም ሴት አግተው ወስደዋል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
15.3K views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 14:54:27 ረስቶም ሆነ ተዘናግቶ ዘካተል ፊጥር ያላወጣ ሰው ሊያወጣ ይገባል። ዘካ፡ በሚችል ሰው ላይ ግዴታ የሆነ የድሃዎች ሐቅ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
14.7K viewsedited  11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 21:11:24 ጥያቄ፡- “የረመዳንን ቀዷእ ቀናት ሳያወጣ በፊት የሸዋልን ስድስት መፆም ይቻላልን?”
መልስ፡- “በረመዳን ያፈጠረባቸውን (ያልፆመባቸውን) ቀናት ቀዷእ ካወጣ በኋላ ከዚያም ስድስቱን ከፆመ ይሄ መልካም ነው። ይህንንም ያንንም ማድረግ የማይችል ከሆነ ግን ነብዩ ﷺ “ረመዳንን ፆሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለ ልክ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው” ያሏትን ስድስቷን (አስቀድሞ) ሊፆም ይችላል። ለምን ይህን አልን? ምክንያቱም የቀዷው ጊዜ ከስድስቷ ፆም በተለየ (ወቅቱ) ሰፊ ስለሆነ ነው። (ስድስቷ ግን) ከሸዋል ውጭ ጊዜ የላትም። የቀዷእ ወቅት ግን ከዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንደመጣው እንዲህ ብላለች፡ ‘በሸዕባን (ወር) እንጂ ቀዷየን አላወጣም ነበር።’ ምክንያቱም በአላህ መልእክተኛ ﷺ ጉዳይ ትጠመድ ስለነበር ነው።” https://www.muqbel.net/fatwa.php?fatwa_id=2278#:~:text=%D9%86%D8%B5%20%D8%A7%D9%84%D8%A5%D8%AC%D8%A7%D8%A8%D8%A9%3A,%D9%83%D9%84%D9%87%20%22%20%D8%8C%20%D9%84%D9%85%D8%A7%D8%B0%D8%A7%20%D9%82%D9%84%D9%86%D8%A7%20%D9%87%D8%B0%D8%A7%20%D8%9F
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 25/ 2014)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor
20.7K viewsedited  18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ