Get Mystery Box with random crypto!

ልቤ ሆይ!! ~ ልቤ ሆይ ልብ አድርግ - ለመልካሙ ትጋ - ከክፋት ተገታ ምላሴ ሆይ እረፍ - ጦስህ | Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

ልቤ ሆይ!!
~
ልቤ ሆይ ልብ አድርግ - ለመልካሙ ትጋ - ከክፋት ተገታ
ምላሴ ሆይ እረፍ - ጦስህ ያስፈራኛል - በጧትም በማታ
እጄ ሆይ ተመከር - "እጄን በ’ጄ" እንዳልል - በሚያስጨንቅ ቦታ
እግሬ እግር አታብዛ - ታዋርደኛለህ - በጭንቁ ቀን ለታ
አዋጅ ሰምቻለሁ - እጅግ የሚያስፈራ - ከሰማዩ ጌታ።

(يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ) [النور 24]
"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሰሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡" [አንኑር: 24]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor